የኢትዮጽያ አዳዲስ ዜናዎች

 • በደቡብ ክልል 12 አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ተገደሉ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Gura-Ferda-EthiopiaOctober 21, 2020 (Ezega.com) -- በደቡብ ክልል ውስጥ በሚገኘው ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ "ማንነታቸው ያልታወቀ" የተባሉ ታጣቂዎች 1 ህጻንን ጨምሮ 12 ንጹሃን ዜጎችን በጥይት መግደላቸው ተሰማ። የወረዳው ባለስልጣናት ለጀርመን ድምጽ እንዳስታወቁት ታጣቂዎቹ ግድያውን የፈጸሙት ባለፈው ሰኞ ምሽት በወረዳው ውስጥ በሚገኘውና ለዩ ስሙ ሹቢ በተባለው የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። እንድ ባለስልጣናቱ መረጃ ከሆነ ታጣቂዎቹ በቀበሌው በሚገኙ መንደሮች ውስጥ ዘልቀው በመግባት በድንገት በከፈቱት የተኩስ እሩምታ አንድ ህጻንን ጨምሮ 12 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 5 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።  የጉራ ፈርዳ ወረዳ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር በቀለ በየነ ለጣቢያው በሰጡት ቃልም ይሄንኑ አረጋግጠዋል። "ጥቃቱ የደረሰባቸው በሙሉ አርሶ አደሮች ናቸው ባልታሰበ ሰዓት ምሽት ላይ በየቤታቸው ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ነው የተገደሉት። አሁን የወረዳ፣ የክልል እና የፌዴራል የፀጥታ ሃላፊዎችና የሰራዊቱ አባላት በስፍራው ደርሰን አካባቢውን እያረጋጋን እንገኛለን። በትናንትናው እለትም የሟቾቹ አስክሬን እንዲቀበርና የቆሰሉትም ወደ ህክምና እንዲወሰዱ አድርገናል " ሲሉም ኢንስፔክተር በቀለ ተናግረዋል።

  የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው አካባቢው እስከ አሁን ሰላማዊ፣ የተረጋጋና የልማት ቀጠና ነበር በማለት ተ

 • በስልጣን ላይ ያለው ሃይል የትግራይ ህዝብ በረሃብ እንዲያልቅ እያሴረ ነው - ዶ/ር ድብረፅዮን

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Debretsion-GebremichaelOctober 20, 2020 (Ezega.com) -- የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ድብረፅዮን ገብረሚካኤል የፌደራሉ መንግስት የትግራይን ህዝብ በረሃብ ለመጨረስ እያሴረ ነው ሲሉ ከሰሱ። ዶ/ር ድብረፅዮን በትግራይ ክልል የልዩ ሃይል ኮማንዶ ምረቃ ስነስርአት ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የፌደራል ስልጣን ይዞ ያለው ሃይል የክልሉ "ህዝብና መንግስት የአምበጣ መንጋን ለመመከት እያደረገ ያለውን ትግል ከመደገፍ ይልቅ ማደናቀፍ፣ መዋሸት፣ ህዝቡ በረሃብ እንዲያልቅ የቻሉትን ሁሉ ለአምበጣ እየደገፉ ነው። ከዚህም አልፈዉ ከሌሎች የሃገራችን ህፃናት ተማሪዎች ለይተዉ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳይቀር ለትግራይ መንግስት አንሰጥም ብለው በህዝባችን ላይ በደል ከመፈፀም ወደ ኃላ የማይሉ ጨካኞች መሆናቸውን አሳይተዋል" በማለት ጠንከር ያለ ወቀሳን ሰንዝረዋል። ለተመራቂ የልዩ ሃይል አባላቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ወላጆቻችሁ ተሰዉተዉና አካላቸዉ ጎድሎ ያረጋገጡትን ራስን በራስ የመወሰንና የማስተዳደር መብት ለማኮላሸትና "አሃዳዊ መንግስት ዳግም ሂወት እንዲዘራ የዉስጥና የውጭ ሃይሎች ተሳስረዉ የትግራይ ህዝብ አንገቱን ደፍቶ እንዲሄድና ከሰው በታች እንዲሆን ሁሉም አይነት ሴራዎችና እርምጃዎች በትግራይ ህዝብ ላይ ለመፈጸምና ህዝባችን ለማንበርከክ  በሚረባረቡበት ወቅት  ወደ ትግራይ የፀጥታ ሃይል መጨምራችሁን" አስተውሉ ሲሉም ተደምጠዋል።

 • ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ ባስቸኳይ ካልተፈቱ ፖሊስ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠነቀቀ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Lidetu-Ayalew-BailOctober 19, 2020 (Ezega.com) -- በተደጋጋሚ የዋስትና መብት በፍርድ ቤቶች ተፈቅዶላቸው በፖሊስ እምቢትኝነት በእስር ላይ የሚገኙትን አቶ ልደቱ አያሌውን የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ በአስቸኳይ እንዲፈታ ካለበለዚያ ግን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማስጠንቀቁ ተሰምቷል። የተጠርጣሪው ጠበቃ አቶ መሐመድ ጅማ ለቢቢሲ እንደገለጹት ከሆነ በጉዳዩ ዙሪያ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ. ም የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት በመቅረብ ምላሽ የሰጡት የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ለቦታው አዲስ መሆናቸውን ያስረዱ ሲሆን የአቶ ልደቱ ክስም ሕገ ወጥ መሣሪያ በመያዝ እንደሆነ እንደማያውቁ ተናግረዋል። ኃላፊው አክለውም ከኦሮሚያ ፖሊስ ጋር ስለዚህ ጉዳይ በስፋት ተነጋግሬ እንድመጣ ሌላ ቀጠሮ ይሰጠኝ በሚል ችሎቱን ጠይቀዋል። ምላሻቸውን ያደመጠው ፍርድ ቤቱም አቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በአስቸኳይ ከእስር የማይለቀቁ ከሆነ በፖሊስ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን ጠበቃ መሐመድ ጨምረው ተናግረዋል። ለወራት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ወጥተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ወስኖ የነበረ ቢሆንም የቢሾፍቱ መምሪያ ፖሊስ ግን ሳይለቃቸው ቆይቷል።

  በወቅቱም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦችና ተቋማትም ጉዳዩን በመቃወም መንግስትን ሲሞግቱ ተሰምተዋል። አቶ ል

 • የቤንሻንጉሉን ተደጋጋሚ ግድያ በመምራት የተጠረጠሩ 504 ሰዎች ተያዙ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Benishangul-GumuzOctober 16, 2020 (Ezega.com) -- በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን በርካታ ንፁኃን ዜጎች እንዲገደሉ በማስተባበርና በመምራት የተጠረጠሩ 504 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ገለጹ፡፡ የአማራና የቤንሻንጉል ክልሎች ርእሳነ መሥተዳድሮች አቶ ተመስገን ጥሩነህና አቶ አሻድሊ ሐሰን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በተገኙበት በክስተቱ ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም በተደጋጋሚ በክልሉ መተከል ዞን በንፁኃን ላይ በሚፈፀመው ጥቃት ውስጥ የህወሃት እጅ እንዳለበት ደርሰንበታል ብለዋል። "ለውጡን ተከትሎ ያኮረፉት እነዚህ አካላት ከሚፈጥሩት የፀረ ሰላም ኃይሎች እንቅስቃሴ" በተጨማሪ ከመሬት ይዞታ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውንም አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡ በተለይ አቶ አሻድሊ ሃሰን ህወሃት ይህን ድርጊት ለማስፈፀም ወጣቶችን በመመልመልና አንዳንድ በኢንቨስትመንት የገቡ ባለሀብቶችን በመጠቀም ችግሮቹ እንዲባባስ ሲሠራ ከርሟል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ በክልሉ ተዋቅሮ ያለውን የኮማንድ ፖስት አፈፃፀም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር በመሆን መገምገማቸውንም ነው አቶ አሻድሊ የተናገሩት፡፡የመከላከያ ኃይሉ በአካባቢው የመሸጉ ታጣቂ ቡድኖችንና ሽፍቶችን "የመደምሰስ ሥራ እንደቀጠለ" መሆኑን የገለጹት ርእሰ መስተዳደሩ የዜጎች

 • ሰቆቃወ ልደቱ - በአዳማ በቢሾፍቱ (አንድ በሉ!)

  ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
   
  October 12, 2020 (Ezega.com)

  Lidetu-Ayalew-court“ክቡር ፍርድ ቤት የዋስ መብቴን ስላከበራችሁልኝ ከልብ አመሰግናለሁ። ሆኖም የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ በማያከብር የህግ አስፈፃሚ ቁጥጥር ስር ስለምገኝ ይህ ውሳኔ የመፈፀም እድል የለውም። ስለሆነም የክቡር ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይከበር ዘንድ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሳልመለስ ከዚሁ ከችሎቱ ፊት እንድለቀቅ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲሰጥልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ!”
  (አቶ ልደቱ አያሌው በችሎት)

  ስለልደቱስ - ዳኛው ማነው?!

  ደጋግመን ከምንጠቅሳቸው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ የኔታጋ ፖለቲካዊ የሃሳብ ልዩነቶች ቢኖሩኝም “ማህበረሰባችን በሌሎች ላይ የሚፈፀሙ መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደራሱ የሚመለከትበት የመንፈስ ልዕልና ላይ ገና አልደረሰም!” ማለታቸውን የምወድላቸው ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም “እንጉርጉሮ” በሰኙት የግጥም መድብላቸው በእንደዚህ አይነት የመብት ጥሰቶች ላይ የማይጣላውን ህሊና የተሸከመ “ሰው” ምንኛ የታደለ ነው ሲሉ ይፎትታሉና ይህንን ሲያንጎራጉሩ እናነባለን፡-

  “የነብሱን ኡኡታ - የህሊናውን ድምፅ
  አፍኖ ሸንግሎ - እንቅልፍ የሚወስደው
  ዓይንና ጆሮውን….
  ከአዕምሮው ገንጥሎ - ቅሬታ ማይገባው

 • የፌደራሉ መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት አቋረጠ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Federal-Government-EthiopiaOctober 6, 2020 (Ezega.com) -- የፌደራል መንግስት ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው በትግራይ ክልል መንግስት ላይ ሶስት ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቋል፡፡ የምክር ቤቱ የህገመንግስት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ አቶ ወርቁ አዳሙ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የተላለፉትን ውሳኔዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በእዚህም መሰረት የመጀመሪያው ውሳኔ የትግራይ ክልል ያካሄደውን "ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ ተከትሎ ከተመሰረቱ የትግራይ ክልል ምክር ቤትና ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካላት ጋር የፌዴራል መንግስት ምንም አይነት ግንኙነት እንዳያደርግ፣ ሁለተኛው የፌደራል መንግስት የትግራይ ህዝብን የልማትና መሰረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ማዕከል በማድረግ "የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ህጋዊ ተቋማት ጋር ብቻ" የስራ ግንኙነት እንዲያደርግ በሶስተኛ ደረጃ የውሳኔውን አፈጻጸም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴ ክትትል መደረግ እንዳለበት ውሳኔ ተላልፏል፡፡

  ይህ ውሳኔ ሊተላለፍ የቻለው ባሳለፍነው ነሃሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ እንዳልተደረገ፣ እንዳልተፈጸመ እና እንደማይጸ

 • ዕድል ከሌለህ…..ድሃ ትሆናለህ!!! የገንዘብ ኖቶች ወግ - ስላቀ ህይወት

  ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

  October 5, 2020
   
  Ethiopian-New-Bank-Notes-“ከሀብታም ቤት ጥብስ፤ ከድሃ ቤት ጥቅስ አይጠፋም!”
  (የታክሲው ጠቃሽ፤ ብሩክ)

  “ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ!”
  (አገራዊ ብሂል)

  “Poverty is like punishment for a crime you didn’t commit.”
  (Eli Khamarov, Author)

  እንደምን ሰንብተሃል ዕድለ ቢሱ ወዳጄ?….በዓሉንስ እንዴት አሳለፍከው ይሆን?! ያ ጉድ የማያልቅበት ተስፋዬ ካሳ ድሆች ፆም ሲፈታ “ሌላ ፆም ከመያዝ በቀር” በዓልን እንደማይዙ ሲቀልድ ሰምተሃልና ይቅር…..መቅድሙን በተከተለው ስላቅ መሰንበቻችንን “በደሳሳ ጎጆ እምኖር የሞራል ባለፀጋ ነኝ!” ሲል ነገሩን በገደለው ገጣሚ ነበር የተሰናበትኩህ፡፡ ያው ድሃ ብሆንም ከነሞራሌ ነኝና ያለሁት “አለሁ አልሞትኩም!” አይነት ብስጭት ስላበዛህብኝ ነበር ያንን መጋበዜ….በእርግጥ የእኛን መደብ በቅርቡ የተቀላቀለውና የመደባችሁን “ቁስሎች” በመነካካት እንዴት በአንድ ጊዜ ውዴታንም ገንዘብንም አጣምሮ መስራት እንደሚቻል የተካነው ከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን ዘ-አፍሮ ባንድ “ባዶ” የ

 • ግብጽ የህዳሴውን ግድብ ታፈነዳዋለች - ዶናልድ ትራምፕ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Donald-Trump-GERDOctober 23, 2020 (Ezega.com) -- የአሜሪካው አወዛጋቢ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ስምምነትን ጥላ መውጣት አልነበረባትም፣ ያንን በማድረጓ ከባድ ስህተት ሰርታለች ግብጽ በዚህ ሁኔታ መኖር ስለማትችል "ግድቡን ታፈነዳዋላች" ሲሉ በይፋ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱል ሃምዶክ እና ከእስራኤሉ አቻቸው ቤንያሚን ኔይተናሁ ጋር በቀጥታ የስልክ ውይይት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ነው። የቀጥታ የስልክ ውይይቱ ሲካሄድ ጋዜጠኞች ተገኝተው የነበረ ሲሆን የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው ግድቡን በሚመለከት በቅርቡ በሶስቱ አገራት መካከል ስምምነት ይደረሳል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሁለቱ መሪዎች ጋር የተወያዩት ሱዳንና እስራኤል በቅርቡ ግንኑነታቸውን ለማሻሻል መስማማታቸውን በማስመልከት ነበር። ምንም እንኳን የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር "በቅርቡ ስምምነት ላይ እንደርሳለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን" ቢሉም በርካታ ጋዜጠኞች በተሰበሰቡበት ሁለቱን መሪዎች የሚያናግሩት ትራምፕ ግን ለግብጽም ተመሳሳይ ነገር መናገራቸውን በመጥቀስ ሁኔታው አደገኛ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ግብጽም "ግድቡን ታፈነዳዋለች" ብለዋል።

  የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሃውስ በነበረው የስልክ ውይይት ወቅት ሲናገሩ እንደተደመጡት ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ወደ ስምምነቱ መመለስ አለባት በኢት

 • የትግራይ ተወካዮች ወደ ምክር ቤት እንዲመለሱ እየተሰራ ነው - አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Ethiopian-ParliamentOctober 21, 2020 (Ezega.com) -- በትግራይ ህዝብ ተወክለው ነገር ግን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ በማይገኙ የምክር ቤቱ አባላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ። ባለፉት ሁለት የምክር ቤቱ ስብሰባዎች ላይ ከአንድ ተወካይ በስተቀር ከትግራይ ክልል የተወከሉት የምክር ቤት አባላት በሙሉ አለመገኘታቸውን ያስታወቁት አፈ-ጉባኤው በምክር ቤቱ በኩል የወጡት የትግራይ ተወካዮች ተመልሰው በምክር ቤት አባልነታቸው እንዲቀጥሉና በስብሰባዎች ላይም እንዲገኙ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል። ያም ሆኖ ጥረቶቹ ፍሬ የማያፈሩ ሆኖ ተወካዮቹ በምክር ቤቱ ስብሰባዎች ላይ ባለመገኘታቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ግን አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤው አቶ ታገሰ ጫፎ አስታውቀዋል። በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት አቶ ታገሰ "ማንኛውንም ችግር በውይይት፣ በህግ እና አሰራር መፍታት እንጂ ሃገርን የማፍረስ እና ህግን የመተላለፍ ተግባር መፈጸም" እንደሌለበትም ተናግረዋል።

  ዘንድሮ የሚካሄደውን ምርጫ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽም ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከ90 በመቶ በላይ የምርጫ ቁሳቁስ አቅርቦቱን እንዳጠናቀቀ መረጋገጡን ጠቅሰው በምርጫ ሂደቱ ለሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች እኩል የውድድር ሜዳ እንዲፈጠር መሰራት እንዳለበትም ገ

 • ሰቆቃወ ልደቱ - በአዳማ በቢሾፍቱ (ሶስት በሉ!)

  ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

  Lidetu-CourtOctober 20, 2020

  “የአቶ ልደቱ እስርና መንግስት የፍርድ ቤት ትዕዛዝን በተደጋጋሚ አለማክበርና መጣስ የፍትህ ሥርዓቱ አደጋ ላይ መውደቁን፣ የወይዘሮ መዓዛ ጥረት መክሸፉን፣ የሹሞቹ ባህሪ ዛሬም አለመቀየሩን፣ ፍትህ ዛሬም በጉልበተኞች ጫማ ስር መውደቋን የሚያሳይ መጥፎ ምልክት ነው። ከዚህ በኋላ ፀቡ ከአቶ ልደቱ ሳይሆን ከፍትህና ለፍትህ ከሚወግኑ ሁሉ ጋር ነው።”
  (አቶ ያሬድ ኃ/ማርያም - የሠብዓዊ መብቶች ተሟጋች)

  የደውሉ “ድምፅ” ለሁላችንም ነው!

  በቀደሙት ሁለት ክፍሎች የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ብሔራዊ ምክር ቤት አባልና አመራር አባል ስለሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው ፍትህ ማጣትና ሰቆቃአንስተን መሰል የህገ-ወጥ አያያዝ ሰለባዎችን ጉዳይ ካወሳሳን በኋላ በተፈጠሩ ተያያዥ ጉዳዮች መግቢያዬን ላደርግና በዚህ ክፍልም ርዕሱን ልቋጨው ወደድኩ፡፡ ከነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በቀር ስለሁላችንም ነፃነትና የሰብዓዊ መብቶቻችን መከበር እንዲሁም ስለፍትህ ቆመናል ከሚሉት የፖለቲካ ማህበራት በኩልም ቢሆን አንድም የአጋርነት መግለጫ አለመሰጠቱና እንዲያውም “ይበለው!” ማለታቸውን ታዝበናል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔን (ሰመጉ) ዝምታን መውቀሳችንም አይዘነጋም፡፡

  በሸኘነው ሳምንት “የኢትዮጵያ

 • የዜጎች አመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ 1 ሺህ ዶላር በላይ ደርሷል - ጠ/ሚ ዐብይ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  PM-Abiy-AhmedOctober 19, 2020 (Ezega.com) -- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ በዛሬው እለት ተካሂዷል። በስብሰባው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። አነጋጋሪ ሆነው ከዋሉት የጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሾች መካከል የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሁኔታ በተመለከተ የቀረበው ይገኝበታል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በተጠናቀቀው የበጀት በኢትዮጵያ የ6 ነጥብ 1 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት መመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡ የታሰበውን ያህል ባይሆንም ከወቅታዊው የኮቪድ 19 ወረርሺኝ አንጻር በበጀት አመቱ ተስፋ ሰጭ የምጣኔ ሀብት እድገት መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በመንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች ለእድገቱ አይነተኛ ሚና ነበራቸው ብለዋል፡፡ ያም ሆኖ የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ ከሳምንት በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ወቅት ሀገሪቱ ያስመዘገበችው እድገት 7 በመቶ ነው ብለው መናገራቸው ሲታሰብ የጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።

  ባለፈው በጀት አመት በኢንዱስትሪው ዘርፍ 9 በመቶ፣ በአገልግሎት 5 ነጥብ 3 እንዲሁም በማዕድን ዘርፍ 91 በመቶ እድገት ተመዝግቧል ይህም ከፍተኛው ሆኗል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር  ዐብይ በ2012 የበጀት ዓመት 3 ነጥብ 375 ትሪሊየን ብር ጠቅላላ ሃገራዊ ምርት መመዝገብ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡ በተያያዘም የኢትዮጵያውያ

 • ሰቆቃወ ልደቱ - በአዳማ በቢሾፍቱ (ሁለት በሉ!)

  ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

  October 14, 2020

  Lidetu-Ayalew-court"በተደጋጋሚ….ዋስትናን በተመለከተ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመፈፀሙ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ በሙሉ አስሮ፣ ፍርድ ቤት ዋስትና ፈቅዶለት ፓሊስ አልፈታውም እንዳለው ይቆጠራል። በፍትሐ ብሄር ህጉ ላይ በግልፅ ተቀምጧል። ሰው ዕቃ አይደለም፣ በአደራ አይቀመጥም። ሰውን በአደራ አስቀምጥልኝ አይባልም። ቃሉ በራሱ ነውር፣ ፀያፍና ግብረ ገብነት የጎደለው ነው። ሰውን በአደራ አስቀምጫለሁ ማለት፣ ያለአግባብ እስሬዋለሁ ብሎ ማመን ነው።”
  (የህግ ባለሙያና ጠበቃው አቶ ተማም አባቡልጉ)

  ደጋግመን ከምንጠቅሳቸውና በሞት ከተነጠቅናቸው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቹ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ለያዝነው ርዕ ጉዳይ ማስመልከቻ የሚሆን ሃሳብ በመዋስ እንጀምር፡፡ ፐሮፌሰሩ “አድፋጭነት” ይሉትን ፅንሰ ሃሳብ ሲያስተዋውቁን የምንበረክተው ኢትዮጵያውያን አምባ-ገነኖችን እንጂ አምባ-ገነንነትን እንደማንቃወመው ይልቁንም የተስማማን እንደሚመስል ነው፡፡ ለመርህና ሰብዓዊ መብቶች ክብረት፤ ለሰው ልጆችም ነፃነት የምንቆም ብንሆን ለአማራውም ሆነ ለትግሬው ጨቋኝ፣ ለኦሮሞውም ሆነ ለሶማሌው አምባ-ገነን አልያም ለሌሎቹ ሁሉ ውግንናችንን በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ባልገለፅን ነበር፡፡

  አንድ ዓቢይ አህመድ (ዶ/ር?) የተባለ ሰው ተቀናቃኞቹን በፖለቲካዊ ክሶች ሲያስርና ሲያንገላታ ትክክል

 • የ“ሰንደቅ ዓላማ”ው ተወዛጋቢዎች

  ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

  October 12, 2020 (Ezega.com)

  Ethiopian-Flag“ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር
  የመጀመሪያ ሰኞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡”
  (የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ -ማሻሻያ)

  መንደርደሪያ….

  ባንዲራ (Bandiera) የሚለውን ቃል ባለማስተዋል ብንጠቀምበትም ቃሉን ጣሊያኖች ሰንደቅ ዓላማን ለመግለፅ የሚጠቀሙበት በመሆኑ ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ በያዙበት ወቅት ያስተዋወቁት በመሆኑ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የምንግባባው “ሰንደቅ ዓላማ” በሚለው ቃል ይሆናል፡፡ የሰንደቅ ዓላማው ጫፍ (ልሣን) የጦር ምልክት እንዲሆን የሚጠበቅበት፣ መጠሪያው “ሰንደቅ” እና “ዓላማ” ከሚሉት የሁለት ቃላት ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን ሰንደቅ ማለት “ምሰሶ ወይም ቋሚ ዘንግ” “ዓላማ” ማለት ደግሞ ምልክት ወይም መለዮ እንደማለት ነው ይሉናል ፈታሄ ቃላቶቻችን፡፡

  እንግዲህ የሁለቱ ቃላት ጥምረት ነው  “ሰንደቅ ዓላማ” የሚለውን ቃል በአንድ ሐረግ አስሮ “በአብዛኛው የተወሰኑና የተለያዩ ቀለማት ካሏቸው ጨርቆች የሚዘጋጅ የአንድ አገር የነፃነት ምልክትና መለያ፡፡” የአንድ ሀገርና ህዝብ የሉዓላዊነቱ ምልክት ወይም ትዕምርት ተደርጎ የሚወሰደው በማለትም በአዲስ አበባ ዩኒቨ

 • ሕውሓትና ብልፅግና፤ የዝሆኖች ፀብ

  ሠላም ዓለሙ

  TPLF-PP-disputeOctober 8, 2020

  መቅድም

  የኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደ ፍየል ቆዳ ተወጥሮ አላወላዳ ካለ ውሎ አድሯል፡፡ የፌደራል መንግስቱና የትግራይ ክልል መካረር ደግሞ እንካ ሰላንትያን ተንተርሶ ቁንጮ ላይ ደርሷል ቢባል ማሟረት አይደለም፡፡ ሠሞነኛው የፌደሬሽን ም/ቤት ውሳኔ ገመዱ ሳስቶ ሊበጠስ ሰበብ ብቻ እንደሚፈልግ ያረጋገጠ ነው፡፡ በፌደራል መንግስቱና በትግራይ ክል መሀል ያለው ውዝግብ የመንግስታት ፍልሚያ ይምሰል እንጅ የፓርቲዎች ግብግብ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ለሽምግልናም እጅ ያልሰጠው ቅራኔ መዘዙ ተነግሮ የሚያልቅ አይመስልም፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ መንበረ ስልጣኑን ሲቆናጠጡ ከየትኛውን የኢትዪያ ክፍል ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር፡፡ እንደራሴዎች ም/ቤት ፊት ቀርበው ማር የሚያዘንብ በሚመስል አፋቸው የበላንን አከኩ፤ ችግራችንን ተጋሩ፤ ለበሽታችንም መድሀኒት አለኝ አሉ፡፡ ከአጥናፍ አጥናፍ እልል ተባለላቸው፡፡ ጊዜ ምን ታቅፎ እንደሚመጣ ማን አወቀ? ማንስ ተነበዬ? ቢተነበይስ አማኝ አልነበረ፡፡ ነገርን ከስሩ፤ ውሃን ከምንጩ ነውና በሕውሓትና ብልፅግና (ፌደራልና ትግራይ መንግስት) መካከል  መቃቃሩ እንዴት ተጀመረ? መቼስ ተጋጋለ? ማነው ትንኮሳውን ያጋለው? ብለን በዙሪያ መለለስ መዳሰሰስ ያሻል፡፡

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በወርሃ መጋቢት 2010 ዓ.ም. ስልጣን በያዙ ሳምንት ሳይሞላቸው ከምስራቋ ጅግጅጋ

 • ህወሓት በፌደራል መንግሥት ውስጥ የሚገኙ አባላቱ ሃላፊነታቸውን እንዲለቁ አዘዘ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  TPLF-quiting-federal-positionsOctober 5, 2020 (Ezega.com) -- በቅርቡ በትግራይ ክልል የተካሄደውን ምርጫ ያሸነፈው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሓት) የፖለቲካ ሹመት ተሰጥቷቸው  በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ የሚገኙ አባላቱ ሃላፊነታቸውን እንዲለቁ ማዘዙን አስታወቀ፡፡ ሃላፊነታቸውን ትተው ለድርጅቱ ሪፖርት እንዲደርጉ የተጠሩት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሉ የክልሉ እና ብሄረሰቡ ተወካዮች፣ በካቢኔ እና ሌሎች ተቋማት ውስጥ ያሉ ተሹዋሚዎችና አመራሮቸ ናቸው፡፡ ድርጅቱ ውሳኔውን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ "በፌደራል የሚገኘው ጥገኛና አምባገነናዊ ቡድን ህገ መንግስቱን በመጣስ ስልጣኑን ማራዘሙን ተከትሎ ድርጅታችን ህወሓት የእዚሁ ኢ- ህገ መንግስታዊነት ተግባር አካል አይደለም" በሚል ውሳኔውን ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡ "ከመስከረም 25/2013 ዓ/ም ጀምሮ በፌደራል ደረጃ ምርጫን በማሸነፍ የሚያዙ ሀላፊነቶችና ውክልና የነበራችሁ የድርጅታችን አመራርና የፌደራል ፓርላማ አባላት ሀላፊነታችሁን በማቆም ወደ ድርጅታችሁ ህወሓት ሪፖርት እንድታደርጉ" ይሁን ያለው ህወሓት በእዚሁ መሰረት ጥሪው ይመለከታቸዋል ያላቸውን ከ40 ያላነሱ ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ ከእነዚህ የድርጅቱ አባላት መካከልም አምባሳደር ደ/ር ኣዲስኣለም ባሌማ፣ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ፣ አቶ አባይ ወልዱና ወ/ሮ ሮማን ገብረስላሴ ይገኙበታል፡፡

 • በትግራይ ለፌዴራል መንግስቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ መንግስት ሊቋቋም ይችላል - ፌዴሬሽን ም/ቤት

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  House-Federaion-EthiopiaOctober 3, 2020 (Ezega.com) -- የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ በሚጥሉ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል በቂ ሕገ-መንግስታዊ መሰረት እንዳለ በአፈ ጉባኤው በኩል በሰጠው ማብራሪያ አስታወቋል። ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች መደበኛ ስራቸውን እንደሚቀጥሉም ምክር ቤቱ ግልጿል። በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉት \የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤው አደም ፋራህ በፌዴራል ደረጃ ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ በኮቪድ 19 ወረርሺኝ ምክንያት መራዘሙን አስታውሰው ይሁን እንጂ የተወሰኑ ቡድኖች በሕዝብ ተወካዮችና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተወሰነውን ውሳኔ በመቃወም በተለያየ መልኩ ሕገ-መንግስታዊ ጥሰት እየፈጸሙ ይገኛሉ ብለዋል። አፈ-ጉባኤው እንደሚሉት ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገ-መንግስታዊ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ ምርጫውን አራዝሟል ሆኖም ለሕገ-መንግስቱ ተገዥ ያልሆኑና ሰላም የማይፈልጉ ቡድኖች ሕዝቡን የማወናበድ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።

  ከእነዚህ አካላት መካከል አንዱ የትግራይ ክልል መሆኑን የገለጹት አቶ አደም ፋራህ "በእስካሁኑ እንቅስቃሴ ክልሉ ሕገ-መንግስቱን አደጋ ላይ ጥሏል" ብለዋል። ለእዚህም ማሳያ ይሆናሉ ብለው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ምርጫ ማስፈ

 • በኢሬቻ በአል ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህወሓት የተደራጀ ቡድን መያዙን ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አስታወቀ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Irreecha-Celebration-TPLFOctober 1, 2020 (Ezega.com) -- በቢሾፍቱና በአዲስ አበባ ከተማ ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶች ለመፈጸም፣ አመጽ ለማቀጣጠልና ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ከትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ሃላፊና ከህወሓት የጥፋት ቡድኖች ተልዕኮ ተቀብሎ በህቡዕ ሲያስተባብርና ሲመራ የነበረ የኦነግ ሸኔ ቡድን ከእነ ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ማድረጉን የበሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ማምሻውን ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው መግለጫ ላይ እንደገለጸው ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ፣ በቢሾፍቱና በሌሎቹም የአገሪቱ አካባቢዎች በጦር መሳሪያ የተደገፈ የሽብር ጥቃት፣ አመጽ ፣ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ተልዕኮ ለተሰጠው በህቡዕ የተደራጀ አንድ ታጣቂ ቡድን የሚውል 10 ክላሺንኮቭ የጦር መሳሪያ ከ 280 ጥይቶች ጋር ከመቀሌ ወደ ባቲ ሲጓዝ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም ቀን በደቡብ ወሎ ዞን ሃይቅ ከተማ ከእነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ሥር ውሏል። በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ አመጽ እንዲነሳ በማድረግ ይህን እንቅስቃሴ ለማሳካት ከተመለመሉት መካከል አንዱ የሆነው እንድሪስ እያሱ መሃመድ የተባለ የኦነግ ሸኔ አባል ከትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊና ከሌሎች ጥቂት የህወሓት የጥፋት ቡድኖች

 • የምርጫ ቦርድ አባላት ክፍፍል አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Getahun-Kassa-NEBESeptember 30, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከባድ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንደተጋረጡበት ተሰምቷል። ከአምስቱ የቦርዱ አባላት መካከል አንዱ የነበሩት ዶ/ር ጌታሁን ካሳ የሥራ መልቀቂያ ማቅረባቸው ለውስጣዊ ፈተናዎቹ ትልቁ ማሳያ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል ሲል ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል። ዶ/ር ጌታሁን ሰኞ መስከረም 18 ቀን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሥራ መልቀቂያቸውን ከማስገባታቸው በፊት ከአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ጋራ ከረር ያለ ውይይት አድርገው እንደነበር ከታማኝ ምንጮች መረጋገጡም ታውቋል። ዶ/ር ጌታሁን አባል በሆኑበት ቦርድ ውስጥ እየጎለበተ የመጣው የዓላማና የአመለካከት ልዩነት ለሰውዬው ውሳኔ አንዱና ዋናው ምክኒያት እንደሆነም ተሰምቷል። የሕግ ባለሞያው ዶ/ር ጌታሁን ቦርዱ እንደ አዲስ ሲዋቀር ከተሰየሙት አምስት አባላት አንዱ ሲሆኑ ከዚያ በፊት በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች መምህርና ዲን፣ የትግራይ ክልል የፍትሕ ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሥራታቸው ተነግሯል። የዶ/ር ጌታሁን የህወሃት አባልነት ጉዳይ ለቦርዱ አባላት እጩዎች በሚመለመሉበት ወቅት በጥያቄ መልክ ተነሥቶ እንደነበር ሆኖም 'አሁን አባል አይደሉም' በሚል መታለፉን በሒደቱ የታሰተፉ ግለሰብ መናገራቸውም ታውቋል። ዶ/ር ጌታሁን የቦርዱ አባል ከሆኑ በኋላ 'ከህወሃት በኩል ጫና ይደርግብኛል' ሲሉ መደመጣቸውንም ዘገባው አስነብቧል

 • በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተጨማሪ 15 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Benishangul-Gumuz-killingsSeptember 26, 2020 (Ezega.com) -- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በንገዝ በተባለ ቀበሌ አርብ መስከረም 15/2013 ከንጋቱ 11 ላይ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች በጥይት መገደላቸው ተነገረ። ጥቃቱ የተፈጸመበት የበንገዝ ቀበሌ የመንግስት ባለስልጣናት እስካሁን 15 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን አረጋግጠዋል። የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ባወጣው መረጃ ደግሞ "በጥቃቱ የተገደሉት ንጹሃን ሰዎች ቁጥር ከ20 በላይ"ይሆናል። የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደምለው እንዳሉት ከሰለባዎቹ መካከልም ወንድማቸው ይገኝበታል። "ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልንም የጥይት ተኩስ ብቻ ነበር በአካባቢው የሚሰማው ብዙ ሰው ነው ያለቀው" በማለት ለቢቢሲ ያስረዱት ዋና አስተዳዳሪው "የእኔ ወንድምም በጥቃቱ ተገድሏል" ነገር ግን ወቅቱ ጨለማ ስለነበር ጥቃት ፈጻሚዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል። እስካሁን በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ የሚያጋጥመውን ጥቃት ማን እንደሚፈጽመው በግልጽ የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ማብቂያ ጀምሮ በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች እንደተገደሉ የሚታወቅ ነው።

  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ በየነ አርብ ሌሊት የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ የተጠናቀረ መረጃ እንደሌላቸው ጠቅሰው ጥቃት መፈፀሙMost Read


 • መስፍናዊው ስንብት!

  ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

  Mesfin-Woldemariam-tributeOctober 5, 2020 (Ezega.com) -- በገፃችን ከስራዎቻቸው እየሰበዝን በአስረጅነት ስንጠቅስ የቀዳሚነቱን ቦታ የያዙት ጉምቱው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ናቸው፡፡ እኚህ አንጋፋ የአደባባይ ምሁርና አሰላሳይ በርካታ ወጣቶችን አስከትለዋልና ስለፖለቲካዊ ድፍረታቸው ያደንቋቸዋል፡፡ አደባባይ ለመውጣት ፍርሃት እጅና እግረ-ሙቅ የሆነባቸው የዕድሜና ዕውቀት ቀራቢዎቻቸው “ምሁራን” ደግሞ በአንድ ጎኑ ስለእርሳቸው ሲሰጉ በሌላው በኩል ደግሞ አድር ባይነትንና እበላ ባይነትን ስለሚጠየፈው ደፋር ብዕራቸው ለየኔታ መስፍን እጅ ይነሳሉ - ባርኔጣ ከፍ እያደረጉ፡፡

  ዕድሜ ዘመናቸውን ሁሉ ስላመኑበት እውነት ሲሟገቱና ሲፅፉ፤ ኢትዮጵያዊነትን ከእምቢ ባይነት ጋር ሲያመዝኑና ብቻቸውን ብዙ ሆነው ሲደክሙ ኖረዋል፡፡ የያዝነውን “አዲስ ዓመት” ግባት ተከትሎ በመስከረም ጅማሮ ላይ “ተጠየቅ መስከረም!” ያሉትን ቆየት ያለ ግጥም በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አጋርተውት ነበር፡፡ በግጥሙ መግያ ስንኞች ላይ “ምን ሰራህ?!” የሚል ሹፈታዊ ጥያቄ ለሚያቀርብላቸው ወርሃ መስከረም ምንም ባይነግሩትም ዕድሜያቸውን ጥንቅቅ አድርገው የሰሩና የኖሩበት ጋሽ መስፍን እስከመጨረሻይቱ ህቅታ ድረስ ሲፅፉና ሲናገሩ፤ ሲያነቡና ሲያስነብቡን መኖራቸው አይታበልም፡፡

  “ተጠየቅ መስከረም - ዛሬስ ዋ ዛየለም!

 • የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት መንግሥትንና ህወሓትን እንዲያሸማግሉ ክራይስስ ግሩፕ ጠየቀ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  ICG-TigrayAugust 16, 2020 (Ezega.com) -- አለም አቀፉ የግጭቶች ቡድን (ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ) የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በገመገመበት ባለ 14 ገጽ ሰነድ ላይ በተለይ የትግራይንና የፌደራሉን መንግሥት ፍጥጫ ትኩረት ሰጥቶ ተንትኖታል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የሠላም ኖቤል ተሸላሚው ዐቢይ አሕመድ አስታራቂና የሚያቀራርቡ ንግግሮቻቸውን ወደ ተግባር እንዲለውጧቸው የጠየቀው ቡድኑ በመንግሥትና በህወሓት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ የአፍሪካ ሕብረት ወይም የአፍሪካ መሪዎች በማሸማገሉ በኩል ተሳትፎ ሊያደርጉ ይችላሉ ብሏል። ከእዚህ በተጨማሪ ግን በተለይ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ ሲልም ቡድኑ አክሏል። አለበለዚያ ግን ተስፋ የተጣለበት ፖለቲካዊ ሽግግር እንቅፋት ሊገጥመው ይችላል ሲል ክራይስስ ግሩፕ ስጋቱን አንጸባርቋል።

  ሪፖርቱ የትግራይ ክልል ልሂቃን ክልላዊ ራስን የማስተዳደር መብት በክልልላችን ምርጫ ማካሄድ ሙሉ መብት ያጎናጽፈናል የሚል አቋም እንደያዙና የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ ሕገ መንግሥቱ ይህን እንደማይፈቅድ በመግለጹ ፍጥጫው መከሰቱን ካብራራ በኋላ ሁለቱም ወገኖች ፖለቲካዊ ጡዘቶችን እንዲያረግቡም ተማጽኗል። ሁለቱም ወገኖች የያዙትን አቋም ያስቀመጠው ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ማዕከላዊ መንግሥት በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ላይ ተጸእኖ ለማሳደር እየሞከረ እንደሆነ የጠቀሰው ሆኖም እንደ ክራይስስ ግሩፕ በብልጽግናና

 • ኢትዮጵያ በግድቡ ጉዳይ ከስምምነት ለመድረስ ጊዜ እያለቀባት ነው - የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  US-State-DepartmentAugust 5, 2020 (Ezega.com) -- ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብጽና ሱዳን ጋራ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜው እያለቀባት ነው ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስጠንቀቁን ብሉምበርግ አስንብቧል። ሚኒስቴሩ ለጋዜጣው በኢሜል በላከው መልእክት እንዳሰፈረው ጊዜው አጭር ነው በግድቡ ጉዳይ እየተካሄደ ያለው ድርድር ግን በሚፈለገው ፍጥነት እየተጓዘ አይደለም ከዚህ አንጻር በሀገራቱ መካከል አንዳች ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለው እድል እየጠበበ ነው ብሏል። በሶስቱ አገራት መካከል የሚደረግን ገንቢና ፍሬያማ ንግግር እናበረታታለን የሚለው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሉም አገራት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት ማሳየት ከቻሉ ግን ሶስቱንም ያማከለና አገራዊ ጥቅሞቻቸውን ከግምት ያስገባ ስምምነት ላይ መድረስ የሚቻልበት እድል መኖሩን ጠቁሟል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው አመት በግብጽ ጥያቄ መሰረት ሶስቱን አገራት ለማደራደር ወስነው ድርድሩ መካሄዱን ያስታወሰው ብሉምበርግ እርሱም ሆነ በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ታዛቢነት የተጀመረው ድርድር ውጤት አላስገኘም ይላል። ያም ሆኖ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ጊዜ እያለቀባት ነው ከማለት ውጭ ድርድሩ ባይሳካ አሜሪካ ልትወስድ ስለምትችለው እርምጃ ያለው ነገር ስለመኖሩ የተሰጠ መረጃ የለም።

  በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሶስቱ አገራት መካከል እየተደረገ ባለው ድርድር ላይ የበኩሏን የግድብ ሙሌት ደንብ ማቅረቧ ተሰ

 • ግብጽ በቀጠናው የጦር ሰፈር እንዳታቋቁም ኢትዮጵያ አስጠነቀቀች

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Egypt-militaryJuly 29, 2020 (Ezega.com) -- ግብጽ በምስራቅ አፍሪካ የጦር ሰፈር በማቋቋም የቀጠናውን ሰላም ለማደፍረስ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንድታቆም ኢትዮጵያ እንዳስጠነቀቀች ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል፡፡ ከ4 ቀናት በፊት ከፍተኛ ባለስልጣናትን የያዘ የግብጽ የልዑካን ቡድን ከሶማሌላንድ ግዛት አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ ጋራ በሀርጌሳ ተገናኝቶ መወያያቱ ይታወሳል፡፡ ዋናው የውይይቱ ማጠንጠኛም ግብጽ በራስ ገዟ አስተዳደር ክልል ውስጥ የጦር ሰፈር ለማቋቋም በምትችልበት ሁኔታ ዙሪያ እንደነበርም ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን የግብጽን እቅድ ተከትሎ ነው ማስጠንቀቂያውን ያወጣችው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኔሽን እንደተናገሩት ምንም እንኳን ግብጽ እንደ አንድ ሉዐላዊ አገር ከየትኛውም የቀጠናው አገር ጋር ግንኙነት የመመስረት መብት ቢኖራትም ይሄንን ስታደርግ ግን ሌሎች አገራትን በሚጎዳ መልኩ መሆን የለበትም ያ ሳይሆን ቀርቶ የግብጽ ድርጊት ሌላ 3ኛ አገር ላይ ስጋት ከፈጠረ ተቀባይነት የለውም፡፡  

  ሶማሌላንድ የግብጽን ጥያቄ መቀበል አለመቀበሏን በተመለከተ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም ያም ሆኖ ተወያዮቹ በካይሮና ሃርጌሳ አገናኝ ቢሮዎችን ለመክፈት ተስማምተዋል የሚሉ ሪፖርቶች ወጥተዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት አምባሳደር ዲና ታዲያ በውይይቱ ስለተደረሰባቸው ስምምነቶች ጠንካራ መረጃዎች አለማግኘታቸውን ጠቅሰው ግንኙነቱ ኢትዮጵያንና

 • የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውኃ ሙሌት ተጠናቀቀ

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  GERD-first-fillingJuly 22, 2020 (Ezega.com) -- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ታሪካዊ ምእራፍ በመሸጋገር ለመጀመሪያ ዙር የታቀደለትን 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ሙሉ ለሙሉ መያዙ ተነገረ። ምንም እንኳን በአጠቃላይ ግድቡ ከሚያስፈልገው ከ74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ አንጻር ሲታይ ሙሌቱ እጅግ ብዙ የሚቀረው ቢሆንም ለመጪዎቹ የውሃ ሙሌት ተግባራት ወሳኝ ኩነት መሆኑን በርካቶች ይስማሙበታል። የጠቅላይ ሚንሰትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንደተገለጸው በዚህ ክረምት ባለው መልካም የዝናብ ሁኔታ ታግዞ በመጀመሪያው ዓመት ለመያዝ የታቀደው የውሃ መጠን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ተጠናቆ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል። ይህንኑ የሚያሳየው የተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መታየቱን ተከትሎም በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና የመንግስት ባለስልጣናትም የደስታ መግለጫ መልእክቶችን ሲያስተላልፉ ውለዋል።

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ‘እንኳን ደስ አላችሁ’ መልዕክታቸው "ስኬቱ ኢትዮጵያውያን ዳግም ሀገር ተኮር ስራ ሰርቶ እንዴት ማሳካት እንደሚቻል ያረጋገጡበት መሆኑን ገልጸው "ይበልጥ የሚያስደስተው ማንም ባልተማመነብን ወቅት በራሳችን ዐቅም ላይ ዕምነት ኖሮን ማሳካት መቻላችን ነው ሕዳሴ ግድባችን የዚህ ትውልድ መለያ ማኅተምና ሰርቶ የማሳካት ትእምርት ነው

 • ጭንብል ገላጩ - የአምነስቲ ሪፖርት! (ሶስተኛውና የመጨረሻው ክፍል)

  Prof-Mesfin-Woldemariam “ማህበረሰባችን በሌሎች ላይ የሚፈፀሙ መሰረታዊ የመብት ጥሰቶችን እንደራሱ የሚመለከትበት የመንፈስ ልዕልና ላይ ገና አልደረሰም፡፡”
  (ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም)

  ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

  June 25, 2020 (Ezega.com) -- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔና ሰኞው በገጠሙበት 3ኛ ልዩ ስብሰባው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ቀርበውለት ማብራሪያ በሚሹ ጉዳዮች ላይ አባላቱ “ጥያቄዎችን” ለክቡርነታቸው አቅርበው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በመንግሥታዊ አስተዳደራቸው ላይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችና መጠነኛ ትችቶች መልሳቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ በያዝነው የአምነስቲ ሪፖርት ርዕሰ ጉዳይ ላይ የጀመርነውን ፅሁፍ ለመቋጨት ያንን ማድመጡ የግድ አስፈላጊ ነበር፡፡

  ሆኖም ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጧቸው ምላሾች የተድፈነፈኑና የመብት ጥሰቶቹን ሪፖርትም በ “ድርሰትና ደራሲ” መስለው የተሳለቁበት ሆኖ አልፏል፡፡ ጠቅላዩ የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን ሪፖርት በተመለከተ ከምክር ቤቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “የኢትዮጵያን ሕዝብ በተመለከተ ለዚያውም ሕዝብን አትግደሉ የሚል ሪፖርት ወጥቶ አንሰማም ልንል አንችልም፡፡” ሲሉ ቢደመጡም እዚያው በዚያው በሌላ አገላለፅ ሽረውታል፡፡

  ጠቅላያችን ከበድ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት

 • ኢትዮጵያ ከግብፅ የተሰነዘሩ ከባድ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፏን አስታወቀች

  ኢዜጋ ሪፖርተር

  Egypt-Ethiopia-CyberattackJune 24, 2020 (Ezega.com) -- በተለያዩ መቀመጫቸዉን ግብፅ ባደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ ላይ የተቃጡ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታውቋል። ጥቃቱ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በማስተጓጎል ከፍተኛ ጫና ለመፍጠር ታስቦ ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14/2012 ዓ.ም በተከታታይ እንደተሰነዘረ ኤጀንሲው አብራርቷል። የሳይበር ጥቃት ሙከራው በተለይ በተጠቀሱት ቀናት በተቀናጀ መልኩ የተቃጣው ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከር እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ በተባሉ የግብጽ የሳይበር አጥቂዎች ቡድን አማካይነት መሆኑን ኤጀንሲው ጨምሮ ገልጿል። ወንጀለኞቹ በጉዳዩ ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጁ የቆዩ እና ኤጀንሲው ሲከታተላችው የነበሩ መሆኑን የሚያስረዳው መረጃው ተቋማቱ በይበልጥ አርብ ሰኔ 12/2012 እና ቅዳሜ ሰኔ 13/2012 ዓ.ም ከፍተኛ የሚባል የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ማድረጋቸውን በመጥቀስ ይከስሳል።

  የሳይበር ጥቃት ሙከራው በሀገሪቱ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የደህንነት መስሪያ ቤቶች እና የግል ድርጅቶች ድረ-ገጾች ላይ ያነጣጠረ ነበር ያለው ኤጀንሲው ወንጀለኞቹ በተለይ በእነዚህ 2 ቀናት ጊዜ ዉስጥ የ13 የኢትዮጵያ መንግስት ተቋማት እና የ4 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የድረ-ገጽን እንቅስቃሴ በመከታተል ከፍተኛ የማስተጓጎል ሙከራ ማድረጋቸውን ጠቅሷል። በተጨማሪም የሳይበር ጥቃቱ