ታሪኩ እንዳጠየቀው - ማነው እየሄደ እየሞተ ያለው?!
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
November 14, 2021
“እኔ የምፅፈው ማንንም ለማስደሰት አይደለም። ማንንም ለማሳዘንም አይደለም። ሙግት ለመፍጠርም አይደለም። ውይይት ለማካሄድ ነው። አተካሮ ለመፍጠር አይደለም። የሰከነ ሀሳብ ማንሸራሸር ቢቻል ብዬ ነው…. በአጭሩ የሰከነ ውይይት ለመፍጠር ነው።”
(ጋሽ አሰፋ ጫቦ - የትዝታ ፈለግ)
አገራችን ወደቀውስ ከመግባቷ በፊት ጀምሮ ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን በፖለቲካዊ ንግግሮችና በሁሉን አሳታፊ ድርድር በመፍታት በኢትዮጵያ ብልጭ ብሎ በርቶ የተዳፈነውን የለውጥ ተስፋ በሙሉ እንዳናመክነው ይልቁንም ወደትክክለኛው መስመር እንዲመለስ በዚሁ ገፅ እና በአገራችን የህትመት ብዙኃን መገናኛዎች በኩል ስናሳስብ ቆይተናል፡፡
አለመታደል ሆኖ ለውጣችን ከህዝብ ሠላምና ከአገራችን ዘላቂ አንድነት ይልቅ በሥልጣን ወዳዶች የእርስ በእርስ ትንቅንቅ እና በዋነኝነትም በኢህአዴጋውያን በኩል እንዲከሽፍ ሆኗል፡፡ የፌዴራሉ መንግሥት በኢፌዲሪ የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት
|
ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ በኋላስ?! (ወግ መቋጫ)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
November 14, 2021
“In peace, sons bury their fathers. In war, fathers bury their sons!”
(ሄርዱተስ፤ ግሪካዊ የታሪክ ሰው)
ሥልጣኔያችን… ቢሰለጥንስ?!
ኢትዮጵያችን የረዥም ጊዜ ሥልጣኔ ያላት አገር ስለመሆኗ ሲነገር መስማት እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ በሸኘናቸው ዓመታት አላስፈላጊና የማይናፀር ፉክክር ውስጥ እየተገባም “እነሱ አገር ከመሆናቸው በፊት እኛ መንግሥት ነበርን!” በማለት አሜሪካንና አውሮጳውያኑ ምሳሌ ሲደረጉም አስተውለናል፡፡ በመሰረቱ ሆኖ በመገኘት፤ በምግብ እህል ራስን በመቻል፤ በፖለቲካ ሥልጣኔና ዴሞክራሲያዊ ዝማኔም የዚያኑ ያህል በመግፋትና በቁሳዊ ብልፅግናም ካልታጀበ “ነበረን” ማለቱ ብቻውን በቂ አይሆንም፡፡ ነበረን ለምንለው ነገር ሁሉ ያለንን ካልደመርንለት ትናንት ላይ ቆሞ-ቀርነታችንን እና የታሪክ ምንጣፍ ላይ ተኝተን መቅረታችንን ከማጋለጥ የተሻገረ ርባና ይኖረዋል ብዬም አላምንም
|
ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ… በኋላስ?! (ሶስተኛው ክፍል)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
October 21, 2021
“Educating the mind without educating the heart is no education at all.”
(አርስቶትል)
ፈር ማስያዥያ…!
በቀደሙት ሁለት ክፍሎች በኪናዊ ስራዎች እያዋዛን የተመለከትነውን የ“ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” ልማዳዊ እንከናችንን ዛሬም መሞገት እንቀጥላለን፡፡ አባባሉም እንደሚል “ንጉሥ ሞተዋል… ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” ሆኖ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሥልጣን ከኢህአዴግ ወደ ኢህአዴግ ቢሆንም ሥልጣንን የመያዣውና የማስቀጠያው መንገድ ከብልፅግና ወይም “ከዓቢይ አህመድ ዓሊ…. በኋላስ?” እንዴት ሊሆን ይችላል ወይም ምን አይነት መሆን ይኖርበታል የሚለው ነጥብ ላይ ዛሬም አለመግባባታችን ለነገ ሌላ ዙር የግጭትና ጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳይዶለን መስጋቱ ተገቢ ይሆናል፡፡
ከእነዚያ ፅሁፎች በኋላ ዘላቂ ሠላምንና መግባባትን እን
|
ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ… በኋላስ?! (ሁለተኛው ክፍል)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
October 21, 2021
“If history repeats itself and the unexpected always happens, how incapable must Man be of learning from Experience?”
(ጆርጅ በርናንድ ሾው)
ጦርነት እና የነባሩ “ባህላችን” አበርክቶ!
በቀደመው ፅሁፍ የነካካነው የ“ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” ነባር “ኢትዮጵያዊ” ባህል ከትውልዳችን ዕሴቶች ጋር መቃረኑ፤ ለፖለቲካዊ ጥያቄዎችና ግቦች ብሎም ለሥልጣን መደላድል ሲባልም የጦር ባህልን ዋነኛ መሳሪያው ማድረጉ ሺህ ዓመታትን እንደተሻገረ የተለያዩ የታሪክ ወፖለቲካ ድርሳናት ይነግሩናል፡፡ የኢህአዴግ ሥርዓት አልባና ህግን ያልተከተለ ፍርሰት ጦሱ ለአገራችንም ተርፎ እነሆ ጦርነትን ቀዳሚው ምርጫችን እንዳደረግን በአዝማናት መካከል ቀጥለናል፡፡
ይህን የጦር ባህልን ያለመግራታችን ብዙ እንደሚያስከፍለን ቢታወቅና በዚህ መ
|
ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ… በኋላስ?! (ቀዳሚው ክፍል)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
October 21, 2021
“Those who cannot remember the past are condemned to repeat it.”
(ጆርጅ ሳንታያና፤ ስፔናዊ አሰላሳይና ደራሲ)
ይሄንን ፅሁፍ ሳሰናዳና ይህንንም ርዕስ ስሰጠው “ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” የማለቱን የጭቆና ቀንበር በወዶ ገብነት የሚጫኑ የሥልጡኑ ዘመን ቆሞ ቀሮችን ማሰቤ አልቀረም፡፡ ብዙዎቹ የዚህ እሳቤ ተጋሪዎች ከዴሞክራሲያዊ እሴቶች ጋር ያላቸው ፀብ ላይ በአመክንዮ ያልታገዘና በምልከታ ችግር የሚሰቃይ ስሁት የአገር ወዳድነት (Patriotism) ይስተዋላልና፡፡ሳያጠይቁ መቀበልን አልወደውም፡፡ በስራ ቀናት ሳይቀር ህዝባዊ አደባባዮችንና አማራጭ ያልተበጀላቸውን መንገዶች እየዘጉ የሚደረጉ “የድጋፍ ሠልፎችን” የማብዛቱ ነባር ባህል ቀየር ተደርጎበአጃቢነት ሲካተት ደግሞ መገረሜ በእጅጉ ይጨምራል፡፡
የኩነቱ መደጋገም ይልቁንም በከተማ አስተዳደሩ መስሪያ ቤቶችና በአስተዳደሩ የወረዳ አደረጃጀቶች በኩል አበል እየተሰፈረና ትራንስፖ
|
ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - ሶስት በሉ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
August 5, 2021
“State sovereignty implies responsibility, and the primary responsibility for the protection of its people lies with the state itself. Where a population is suffering serious harm, as a result of internal war, insurgency, repression, or state failure, and the state in question is unwilling or unable to halt or avert it, the principle of non-intervention yields to the international responsibility to protect.”
(Report of the International Commission on Intervention and State Sovereignty, The Responsibility to Protect: Core Principle one)
ሉዓላዊነት የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች እየጣሱ መደበቂያ ሊሆን እንደማይችል ለማሳየት
|
ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - ሁለት በሉ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
August 5, 2021
"...if Humanitarian Intervention is, indeed, an unacceptable assault on sovereignty, how should we respond to a Rwanda, to a Serbrenica - to gross and systematic violations of Human Rights that affect every precept of our common Humanity?..."
(የኮፊ አናን ጥያቄ)
በቀደሙት ሁለት ክፍሎች “ታለ በአገር ሉዓላዊነት ስም!” በሚል ርዕስ የጀመርነው መጣጥፍ በቀናቶች ልዩነት በብዙ በሚቀያየረው ፖለቲካችን ሳቢያ እነሆ እንደቀጠለ አለ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እስከጥግ ድረስ ሄዶ ችግራችንን በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ ስንወተውት ቆይተናል፡፡ ግጭትና ጦርነት አይቀሬ ሲሆን ደግሞ ባልታጠቁና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት በሌላቸው ዜጎች ላይ የትኛውም አይነት ሰቆቃ እንዳይፈፀም ጮኸናል፡፡ ይህንን የጦርነት ህግ እየተላለፉ “ሉዓላዊነት” ላይ ሙጭጭ ማለት ከ
|
ኢትዮጵያ - “የሚወድቁ አገራት” ዝርዝር ውስጥ?!
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
June 18, 2021
“It’s dangerous to be right when the Government is wrong.”
(ቮልቴር)
ከድህነቷ ጋር እየተንገታገተች ዘመናትን የፀናቸው አገራችን ኢትዮጵያ በየወቅቱ የጦርነትና ረኃብ ችግር ውስጥ ትገባለች፡፡ በየጊዜውም የህልውና ጥያቄዎችን ትጋፈጣለች፡፡ ችጋርና ድህነት በሰፊው ከተንሰራፋው ጦር ወዳድ ድንቁርናችን ጋር እየተሰናሰሉ የህልውና ውጥረታችን ደልዳላ መሠረትና ምቹ ቀጠና ሆነዋል፡፡ ከህልውና ትግል ለመውጣት ድንቁርናን እና ድህነትን ድል መንሳት አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታ ቢሆንም በየወቅቱ “የድህነት ዘበኛ” እየሆኑ ከአገረ መንግሥቷ መንበር ላይ የሚደላደሉ ግለሰቦችና ቡድኖች የቁስለቷ ድነት ላይ የሥልጣናቸውን ዕድሜ መራዘም ይመሰርታሉና ሰቆቃችን እንደቀጠለ አለን፡፡
ስለዚህም መንግሥታቱ በሽታችንን ሳይሆን የበሽታውን ምልክቶች በማስታገሻ ማቆየት እንጂ ማከሙን አይፈልጉትም፡፡ አገራችንን ኢትዮጵያን እጅግ አድርገን ለምንወድ ዜጎቿ ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ልንንደረ
|
ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - አንድ በሉ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
June 18, 2021
“There are two kinds of Injustice: the first is found in those who do an injury; the second in those who fail to protect another from injury when they can.”
(Cicero, a Roman Jurist)
በቀደመውና “ታለ በሉዓላዊነት ስም!” የሚል ርዕስ በሰጠነው መጣጥፍ “ሉዓላዊነት” ምን ማለት እንደሆነና እንዳልሆነ ጭምር በማሳየት የአህጉረ አፍሪካችን ገዢዎች “በሉዓላዊነት ስም” ዜጎቻቸው ላይ እያደረሱት ያለውን ዘርፈ ብዙ በደል ለመመልከትና ዘመኑ እያለፈበት ስለመምጣቱም ተጠቋቁመናል፡፡ የሉዓላዊነትን ተራማጅ ፍቺ መነሻ በማድረግ አገራችንን ጨምሮ ወንበሯን ያገኙ አምባገነን መንግሥታትን ክሽፈት እየነቃቀስን ዛሬም እንቀጥላለን፡፡ በዚህም የ“ዓለማቀፉ ማህበረሰብ” ሚናና የጣልቃ-ገብነቱን ሁኔታ እናወሳሳለን - መልካም ንባብ!
“ሉዓ
|
ታለ “በሉዓላዊነት” ስም! (አንደኛው ክፍል)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
June 18, 2021
“Sovereignty implies responsibility not just power!”
(Koffi Annan, 26 June 1998)
ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ከሚታወቅባቸው ስራዎች የቅርቦቹ ርዕስ “ታለ” የሰኘውን ገፀ-ባህሪ ስያሜ በማስቀደም ተፈታሹን ጭብጥ እያስከተለ “በፍቅር ስም” እንዲሁም ሐሰተኛውን “በእምነት ስም” በሚሉት ስራዎቹ እጅግ ተነባቢነትን አትርፏል፡፡ ዓለማየሁ በእውነትና “በአንድነት ስም” ወይም “በሉዓላዊነት ስም” እያለ ስለመቀጠል አለመቀጠሉ እርግጠኛ ባልሆንም እነዚህ ታለዎች የሰው ልጆች ህይወትን በየፈርጁ እንድንፈትሽ ገፍተውናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ትናንት በአገር አንድነት ስም ሲፈፀሙ የነበሩ ሰቆቃዎች በሙሉ ዛሬ በአገር ሉዓላዊነት ስም በእኔና በእናንተ ዘመን ሲፈፀሙ እየታደምን ነው፡፡
በተወሰነ መልኩም ቢሆን ዛሬም ስለመኖራቸው ታሪክ ምስክር ሆኗልና መፃህፍትን ጨምሮ በተለያዩ ሰነዶች ተጠርዞ እያነበ
|
አንዳንድ ነጥቦች - ስለሰሞንኛው ፖለቲካችን
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
April 1, 2021
የዳያስፖራው ፖለቲካ - እንደግመል ሽንት?!
የኢትዮጵያች ፖለቲካ በብዙዎች እንደተተሰፈው ሳይሆን በጥቂት ሩቅ ተመልካቾች ቀድሞም እንደተፈራው “ከድጡ ወደማጡ” እየገባ ስለመሆኑ በድጋፍም ተቃውሞውም ጎራ የተሰለፉ ወገኖቻችን ልቦና የሚረዳው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ለእኩልነትና ነፃነት፤ ለሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና ለአካታች አገራዊ አንድነት የተደረገውን ትግል በመጥለፍ “የለውጥ ኃይል” ነኝ ብሎ ብቅ ያለውና በኋላ ላይ በኮ/ል ዓብይ አህመድ አሊ የአምባገነንነት ፍላጎትና የንግሥና ምኞተ ፈቃድ ስር ያደረው ኢህአዴጋዊ ስብስብ ከአመራር ክህሎት እጦት ባልተናነሰ በሥልጣን ሽኩቻውና ባደረ የቂም መንገዱ አገራችንን ቁልቁል ይዟት መንደርደር ከጀመረ ሰንብቷል፡፡
አለመታደል ሆኖ ትናንት በዚያ ክፉ የሰቆቃ ዘመን ሽፋን ያልቀየረውን ኢህአዴግ በብርቱ ሲተቹና የተሻለ አገራዊ ፍቅርን ሲያሳዩ የነበሩ ሰዎች፤ ትናንት የበቁ፤ የነቁና ያወቁ ይመስሉ የነበሩ ሰዎች ይልቁንም በምሁሩ አካባቢ
|
ከዓድዋ እስከ ማይጨው… ከካራማራ እስከ ባድመ!
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
March 8, 2021
“We sleep peaceably in our beds at night only because rough men stand ready to do violence in our behalf!”
(ሰር ዊንስተን ቸርችል)
“ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!”
(ቀኝጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ)
ወግ መያዥያ…
ይህ ያለንበት ወር ከግንቦት ሲለጥቅ በኢትዮጵያችን በርካታ ሁነቶች የተስተናገዱበት ወር ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ተርፎ ለመላው አፍሪካውያንና ይልቁንም ለጥቁሮች ሁሉ የነፃነት ምልክትና ጭቆናን ያለመሸከም ትዕምርት ሆኗል፡፡ ድሉን ድህነታችን ላይ መድገም ቢያቅተንም አንገታችንን በእኩልነት ቀና አድርገን እንድንሄድ ያስቻለ ታሪክም ተከትቦበታል፡፡ ስለዚህም ብዙ ክብርና ምስጋና ስለነፃነታቸውና ነፃነታችን፤ ስለአገራቸውና አገራችን ሲሉ ለተዋደቁ ሁሉ ይሁንና “የድል በዓል!” እንጂ ከቅኝ ግዛት እንደተላቀቁ ወገኖቻችን የምንዘክረውና &l
|
ሃያ ሰባት ሲደመር - ስንት?!
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
February 16, 2021
“በታሪክ የሚታወስ መሪ ለመሆን ከፈለግክ ራስህን ሁን - አታስመስል!”
(አቶ ልደቱ አያሌው - ለኮ/ል ዐቢይ አህመድ እንደፃፉላቸው)
የአቶ ልደቱ አያሌው ምህረቱን ፖለቲካዊ እስር መነሻ አድርገን “ሰቆቃወ ልደቱ በአዳማ በቢሾፍቱ!” በሚል ርዕስ በሶስት ክፍል ያስነበብናችሁ መጣጥፍ እንደተጠበቀ ሆኖ እዚሁ ገፃችን ላይ የተነበቡ ሌሎች ፅሁፎች የአቶ ልደቱንም ሆነ የሌሎች አያሌ ኢትዮጵያውያን የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን እስራት ስንቃወም፣ ሰብዓዊ መብታቸውን ያከበረ አያያዝ እንዲደረግላቸው ስንወተውት፣ አቅማችን በፈቀደ ሁሉ ኢ-ሰብዓዊነትንና ጭፍን ወገንተኝነትን ስንተች እንደቆየን ማሳያ ይሆናሉ ብለን እናምናለን፡፡
የነገ ከነገ ወዲያ መንገዳችንም ይኸው ነው፡፡ ለተበደሉትና ለተገፉት ሁሉ ድምፅ መሆንና ለሁሉም እኩል ተቆርቋሪነትን በማሳየት በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እግሩን እንዲተክል መትጋት፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው የፍትህ ሥርዓቱን ተቋማዊ የውድቀት ልክ አስመልክተውንም
|
ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!! (ወግ መቋጫ ሶስት - ስላቀ ምግብ ወልባስ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
February 4, 2021
“ሀብታሞች ለስጋቸው ሆድ ሲፈልጉ
ድሆች ደግሞ ለሆዳቸው ስጋ ይፈልጋሉ!”
(የሕይወት ተቃርኖ)
“ሱፉን ግጥም አርጎ ተከርክሞ ፀጉሩን
መልዓክ መስሎ ታየኝ ወይ ያለው ማማሩ!”
(አስቴር አወቀ - በህዝብኛ)
አገርህ በንዋዩ በኩል ባትታደልም የበዓላት ሀብታም ነችና በቀደመው ፅሁፌ በተሳልቆ ውኃ ከነቋቆርኩህ በኋላ ተጣፍተን ከረምን፡፡ እንደምን አለህልኝ ወዳጄ ልቤ?! በዓላትን መለዮዋ ባደረገች ቺስታ አገር ላይ በዓሉስ እንዴት አለፈልህ ይሆን?! ያው የገናን ቅንጥብጣቢ ለጥምቀት ከሚያሻግሩት እንጂ ጥምቀትንም ራሱን የቻለ በዓል ከሚያደርጉት ወገን አይደለህም ብዬ ነው…. አልሞላ ያለ ኑሮህስ እንዴት ይዞሃል…?! ለነገሩ የድኃ ነገር ሆኖ ጠግባችሁ የበላችሁና ከርሳችሁ የሞላ ቀን የዓመት ርኃባችሁን ትረሳላችሁና አይዞን! “ያልተፈተነ አያልፍም!” ነው ነገሩ፡፡
በቀደመው ክፍል “ድኃ አይጣላ ከውኃ!” ይሉትን በ
|
ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
(ወግ መቋጫ ሁለት - ስላቀ ኑሮ!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
January 11, 2021
“I am neither an Optimist nor a Pessimist. But a Possibilist.”
(Hans Rosling)
አገርህ እንዲህ እንደዛሬው የጠቢብ እጥረት ሳያጋጥማት በፊት እንደሳቅ ንጉሡ ቻርሊ ቻፕሊን ሁሉ ድህነቱንና ድህነትህን በምሬት ሳቅ የሚያዋዛልህ ተስፋዬ ካሳ የሚባል ሰው ነበረ… ይህ ቀልዱ ብቻ ሳይሆን ድምፁም ያማረለት ሰው በአንድ የበዓል ጨዋታው ላይ ህፃን ልጅ “እማዬ ፆም ሲፈታ….?!” ብሎ ድኃ እናቱን ይጠይቅና የእናትዬውን ምላሽም ያቀብለናል፡-
“ልጄ! ፆም ሲፈታማ ሌላ ፆም እንይዛለና!”
እነሆ…. አንተም ዕድለ ቢሱ ወዳጄ ፆም ተፈታልህና ሌላ ፆም ይዘሃል... በቀደሙት ክፍሎች ይልቁንም ድህነትን ከፍቅርና ጦርነት ጋር እያሰናሰልን በተሳለቅንበት ክፍ
|
ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
(ወግ መቋጫ አንድ - ስላቀ ፍቅር ወጦርነት!)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
December 31, 2020
“ድህነት በመስኮት ሲገባ ፍቅር በበር ይወጣል!”
(አገራዊ ብሂል)
“የድሃ ልጅ ነው እየታፈሰ ወደጦርነት የሚጋዘው!”
(የኢትዮጵያ መሪዎች)
ይህንን ፅሁፍ ስንጀምረው በገንዘብ ኖቶች ቅያሪ መነሻነት ነበርና ርዕሰ ጉዳዩ “የገንዘብ ኖቶች ወግ” ቢሆንም ብዙ ነገሮችን ነካክቶ እኔም ፅፌው እርስዎም አንበብውታል…. ማለቴ አንተ ዕድለ ቢሱ ድኃ አንብበኸዋል፡፡ በቀጠሯችን መሠረት እነሆ ፅሁፉ መቋጫ ሊያገኝ ግድ ነውና ፍቅርንና የእርሱም ተቃራኒ የሆነውን ጦርነትን ነካክተን ከድህነት ልናሰናብትዎ ባንችልም ከነድህነትዎ እንሰናበትኋለን…! ድህነትን በደንብ አውቆና ተዋውቆት ያለፈው ሞዛቂ ኃ/ኢየሱስ ፈይሣ “ፍቅር” ይሉት ማራኪና አጓጊ ነገር ላንተ ብጤው ድኃ “ዋጋው
|
በመተከል በተፈፀመ ዘር-ተኮር ጥቃት ከ90 በላይ ዜጎች ተገደሉ
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 23, 2020 (Ezega.com) -- በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ በተባለ ቀበሌ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ከ90 በላይ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የጀርመን ድምጽ ራዲዮ፣ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅትና ቢቢሲ ከአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አገኘነው ባሉት መረጃ መሰረት ዜጎቹ የተገደሉት ከባድ መሳሪያ ጭምር በታጠቁ ተዋጊዎች ሲሆን በቀስትና በሌሎች መሳሪያዎች የተገደሉና የቆሰሉ በርካቶች መሆናቸውንም አስነብበዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንድ የቡለን ወረዳ ነዋሪ ጥቃቱ ትናንት ሌሊት 11 ሰዓት አካባቢ መፈፀም እንደጀመረ ገልፀው እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ቀጥሎ ነበር ብለዋል። በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ለቅሶ ላይ መሆናቸውን የገለፁት እኝህ ነዋሪ "እስካሁን 100 አስክሬኖች ተገኝተዋል የጠፉ አስክሬኖችም አሉ ወደ ቡለንም 70 አስክሬኖች መጥተው ተመልክቻለሁ" ማለታቸው ተዘግቧል። በጥቃቱ የጓደኛቸው አባት መገደላቸውን የተናገሩት ነዋሪው "ቤት እየጠበቀ እያለ ነው ተኩሰው የገደሉት እርሱ መሳሪያ ቢኖረው
|
ልጄ በምን ምክኒያት እንደታሰረች ማወቅ አልቻልኩም - ወ/ሮ አዜብ መስፍን
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 22, 2020 (Ezega.com) --- የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰምሃል መለስ መቀሌ ከተማ ውስጥ ተይዛ እንደታሰረች እናቷ ወይዘሮ አዜብ መሰፍን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ያም ሆኖ ልጃቸው ሰምሃል በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ወ/ሮ አዜብ ለቢቢሲ ተናገረው ወደ መቀለ የሄደችው ወታደራዊ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል። አዲስ አበባ የሚገኙት ወ/ሮ አዜብ እንደሚሉት ከሆነ ሰምሃል ወደ መቀለ ያቀናችው በአባቷ የህይወት ታሪክ ላይ የተጻፈ መጽሐፍ ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀን ቲያትር ለማስመረቅ ሲሆን አካሄዷም በርካታ ሰዎች ካሉበት ቡድን ጋር በመጣመር ነው ብለዋል። ሰምሃል "የፖለቲካ አቋም ሊኖራት ይችላል ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲ አመራርም፣ አባልም፣ ደጋፊም አልነበረችም" የሚሉት እናቷ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የልጃቸው እስር ምክንያት ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ነው ለቢቢሲ የተናገሩት። ወ/ሮ አዜብ ከቀናት በፊት ልጃቸው ሰምሃል እየተፈለገች እንደሆነ በመስማታቸው አርብ ዕለት ወደ መቀሌ ለመሄድ ፈልገው የነበረ ቢሆንም ፈቃድ ባለማግኘታቸው እ
|
በዓለም የፍልስፍና ቀን “ፍልስፍናችን” ቢፈተሽስ? (ማጠናቀቂያ)
ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
December 20, 2020
“እንደኔ እምነት የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ስድስት ኪሎ ሲሞት
አምስት ኪሎም መጠውለጉ አይቀሬ ነው፡፡”
(ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)
ጋሽ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) የኔ ዘመን ኢትዮጵያውያን ስለፍልስፍና ያላቸውን አመለካከት እንዲያጠይቁ ካደረጉ ጉምቱ የአደባባይ ምሁራን ውስጥ አንዱና በዚህ ዘርፍ ላይም ቀዳሚው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በተከታታይ ቅፆች “ፍልስምና” በሚል ርዕስ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን ምልከታዎች ጨምቆ ከሰጠን ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ በኩል ተነባቢ በነበረችው “አዲስ ጉዳይ” መፅሄት ስለፍልስናና በቀደመው ክፍል ስላነሳነው 70/30 የትምህርት ሥርዓተ ፖሊሲያችን ተገቢነት ዙሪያ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ነበር፡፡ ለጥያቄዎቹ ከሰጧቸው ምላሾች ውስጥ ይህንን መግቢያ ላደርገው ፈቀድኩ፡፡
ጋሽ ዳኛቸው ጥያቄውን ሲመልሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው የስድስት ኪሎ ግቢ ውስጥ የሚሰጡት የማህበራዊና የሥነ-ሰብዕ (Social Scie
|
ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማና የአቶ ስዩም መስፍን ቤተሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 10, 2020 (Ezega.com) -- መንግሥት በበርካታ ከባድ ወንጀሎች ውስጥ ተሳትፈዋል በማለት ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳባቸው ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ ዛሬ ሐሙስ ታኅሳስ 01/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዚህም በትግራይ ክልል ውስጥ ከተካሄደው ወታደራዊ ግጭት በኋላ ፍርድ ቤት በመቅረብ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር አዲስአለም የመጀመሪያው ሆነዋል። በትግራይ ክልልም ሆነ በፌደራል መንግሥት ደረጃ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉትን የአዲስዓለም ባሌማን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ከአንድ ወር በፊት በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የእስር ትዕዛዝ ከወጣባቸው የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት አዲስዓለም በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት። ፖሊስ ሰውዬውን የጠረጠረበትን የወንጀል ዝርዝር ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈ
|
|