ከለውጡ በኋላ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከመመሪያ ውጭ ባክኗል ተባለ
ኢዜጋ ሪፖርተር
September 18, 2020 (Ezega.com) -- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ስልጣን በያዙ ማግስት የሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ካዝና ክፉኛ ተመዝብሮ ባዶ እንደነበር መናገራቸው ይታወሳል። ያም ሆኖ እሳቸው ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከብሔራዊ ባንክ ደንብ እና መመሪያ ውጭ ሲባክን እንደ ነበር ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል። ጣቢያው አገኘሁት ባለው ሰነድ መሰረት ከለውጡ ወዲህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካኝነት ከብሔራዊ ባንክ መመሪያ ውጭ የውጭ ምንዛሪ ለማይፈቀድላቸው አካላት ሲሰጥ ቆይቷል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአቶ በቃሉ ዘለቀ ይመራ በነበረበት በ2010 አመት ከግንቦት እስከ ነሀሴ ከባንኩ በትንሹ ከ69 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ "ከመመሪያ ውጪ ለተለያዩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች" መሰጠቱ ተነግሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ድልድልን አስመልክቶ ከ3 ዓመታት በፊት ያወጣውን መመሪያ ንግድ ባንኩ በከፍተኛ ደረጃ ሲጥስ እንደነበርም የተገኘው ሰነድ ያመለክታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ
|
ኢትዮጵያ የብር ኖት ለውጥ አደረገች
ኢዜጋ ሪፖርተር
September 14, 2020 (Ezega.com) -- በኢትዮጵያ የወረቀት ብር ኖቶች ለውጥ ሊደረግ ነው የሚለው ወሬ መናፈስ ከጀመረ ከሁለት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል። ከእነዚህ ዓመታት በኋላ ቅያሬው እውን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ ይፋ አድርገዋል።ከ 5 ብር ኖት በስተቀር ሁሉም ብሮች ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀየሩ የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ የተደረገው የብር ለውጥ አገሪቱ እያካሄደችው ያለችው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ አንዱ አካል እንደሆነ አስረድተዋል። በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የ200 ብር ኖት መዘጋጀቱም ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የብር ለውጡ ለሕገ ወጥ ተግባራት የሚውለውን ገንዘብ ለማስቀረት፣ ሙስናንና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል ሲሉም ተደምጠዋል። ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የሐሰተኛ የብር ኖት በገበያው ውስጥ በተደጋጋሚ መከሰታቸው አገሪቱን ለማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መዛባት እንዳጋለጣት የምጣኔ ሃብት ባለሞያዎች ይናገራሉ። ያጋጠመውን የዋጋ ንረት የመቆጣጠሩ ተግባርም በሚፈለገው መጠን ውጤት ማምጣት እንዳልቻለ
|
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ተመዘገበ
ኢዜጋ ሪፖርተር
July 22, 2020 (Ezega.com) -- አገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት ቀደም ባሉት ወራት ከነበረበት በማሻቀብ ባሳለፍነው ሰኔ ወር 2012 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ 21.6 በመቶ መድረሱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። የዋጋ ግሽበቱ ለተከታታይ ወራት ሲጨምር የቆየ ቢሆንም አሁን የተመዘገበው ቁጥር ግን ሁኔታው አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመላካች ነው። የፌዴራል መንግሥት በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. በጀመረው አዲሱ የበጀት ዓመት ማጠናቀቂያ ላይ አሁን የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ወደ ነጠላ አኃዝ ወይም ወደ ዘጠኝ በመቶ ለማውረድ እንደሚስራ ከሳምንት በፊት አዲሱን የአገሪቱ በጀት በፓርላማ ባስታወቀበት ወቅት መግለጹ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የበጀት ዓመቱ በተጀመረበት በዚህ ወር ያለውን የዋጋ ግሽበት የሚጠቁመው መረጃ እንደሚያሳየው ፈጣን የሆነ የዋጋ ግሽበት አዝማሚያ ከወዲሁ እየተስተዋለ ይገኛል።
የአገሪቱ የሰኔ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በ21.6 ከመቶ ለመጨመሩ ቀዳሚ ምክንያት የሆነው በምግብ ሸቀጦች ላይ የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የበለጠ ኣሻቅቦ ወደ 23.1በመቶ ከፍ በ
|
ኢትዮጵያ ከፀሐይ ግርዶሽ የሚገኝ ከፍተኛ የቱሪስት ገቢ አጣች
ኢዜጋ ሪፖርተር
June 19, 2020 (Ezega.com) -- በኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ ሰኔ 14, 2012 ዓ.ም እንደሚታይ ከሚጠበቀው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ጋር በተያያዘ ከዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ይገኝ የነበረ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ በኮቪድ 19 ወረረሽኝ ምክንያት የሚታጣ መሆኑን የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ። የፀሐይ ግርዶሹ በእለቱ እንደ ሀገሪቱ የሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 12፡50 እስከ ረፋዱ 3፡30 ቆይታ ይኖረዋል የተባለ ሲሆን ይህንኑ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ክስተት ለመመልከት ከ20 ሺህ በላይ የተለያዩ ሀገራት ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ተመዝግበው እንደነበርም የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። ከተመዘገቡት ጎብኚዎች በተጨማሪም በርካቶች ክስተቱን ለማየት ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው የሚጠበቅ ነበር።
በተለይም በግርዶሹ ምክንያት 90 በመቶ በጨለማ ይዋጣሉ ተብለው ከሚጠበቁ ስፍራዎች መካከል አንዱ ወደ ሆነው ታሪካዊው የላልይበላ መካነ ቅርስ ለመሄድ ፍላጎት የነበራቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ቢሆንም በኮቪድ 19 ምክንያት ጉዞው መከልከሉን ነው የኢትዮጵያ ስ
|
ኮሮናና የምጣኔ ሀብት ጠባሳ
በሠላም ዓለሙ
March 25, 2020 (Ezega.com) -- ዓለም (ምዕራባዊያኑ) የ2020 አዲስ ዓመታቸውን እንደተመኙት በአዲስ መንፈስና ራዕይ አልተቀበሉትም፡፡ በታህሳስ ወር የምድር የምስቅልቅሏ እጣ ፈንታ ሀ ብሎ ተጀመረ፡፡ የዚህ ክፍለ ዘመን ቀውስ ከወራት በፊት በቻይና ሁቤ ግዛት ሁዋን በተሰኘች ከተማ በተከሰተ ቫይረስ ይሆናል ብሎ የተነበየ አለ ብሎ ደፍሮ መናገር አይቻልም፡፡ በዓለም የጤና ድርጅት ኖቭል ኮሮና (ኮቪድ-19) የሚል ሳይንሳዊ መጠሪያ የተሰጠው ቫይረሱ ወረርሽኝ ሆኗል፡፡ ዛሬ ከ194 በላይ የዓለም አገሮች ላይ የደረሰው ቫይረሱ፤ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው፡፡ ይህ ፅሁፍ እስከወጣበት ድረስ በተገኘ መረጃ 19 ሽህ የሚሆኑ ሠዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ 424 ሽህ ዜጎችም በዓለም የጤና ድርጅት የጤና ቀውስ ሲባል በተፈረጀው ቫይረስ ተይዘዋል፡፡
ቫይረሱ በተቀሰቀሰበት ሰሞን በርካታ አገሮች ከቻይና ጋር ያላቸውን ግንኙነት የቀነሱ ቢሆንም፣ በዚህ ዓለም አንድ በሆነችበት ዘመን ድንበርን ዘግቶ መቀመጥ ከቫይረሱ ስርጭት የሚያስጥል ሆኖ አልተገኘም፡፡ የቫይረሱ ስርጭት ከተርታው ዜጋ አልፎ የተለያዩ አ
|
የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ገመናው ሲገለጥ
በሠላም ዓለሙ
March 2, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት በተለይም ባለፉት ዓመታት በርካታ ይበል የሚያሰኙ ነገሮች ተብለውለታል፡፡ በሁለት አሀዝ አድጓል፤ ተመንድጓል፤ ይህም ሀገሪቷን በፈጣን እድገት ላይ ያለች ቀዳሚ ሀገር አሰኝቷቷል የሚሉ የመንግስት መግለጫዎች ባለፉት ዓመታት ተሰምተዋል፡፡ ይሁን እንጂ እውነታኛ የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት አፈፃፀም መንግስት እንደሚለው አይደልም ሲሉ በጥናታቸው ምርመራ ደረጉ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ እድገትን ከልማት ጋር አንድ አድርጎ የመሳል ጥንውትንም ባለሞያዎቹ ነቅሰው ያወጣሉ፡፡
የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት በጥቅሉ እድገት ቢኖረውም ከዋጋ ግሽበት፣ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ከገቢና ወጪ ንግድ ሚዛን መዛባት እንዲሁም ከውጭ የእዳ ጫና ጋር ሲመረመር እውነታው ከዚህ የራቀ መሆኑ ይነገራል፡፡ ይህም በመሆኑ ምጣኔ ሀብቱ “የተናጋ ነው” ይላሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ፡፡ የጥቅል ምጣኔ ሀብት ፖሊሲ እና “በምጣኔ ሀብቱ ውስጥ የመንግስት ሚና” በሚ
|
ኮንትሮባንድ፤ የኢትዮጵያ እዳ
በሠላም ዓለሙ
February 11, 2020 (Ezega.com) -- ኮንትሮባንድ በገቢና በወጪ ምርቶች ላይ በመሰራፋት ኢትዮጵያን በዙሪያ መላስ እየጎዳት ነው፡፡ የወጪ ንግዷ ማሽቆልቆል ከጀመረ ዓመታት ያስቆጠረችው ኢትዮጵያ፤ ለዚህም ፊት ተጠቃሽ ምክንያት የኮንትሮባንድ ንግድ ነው፡፡ ለአብነት የ2011 በጀት ዓመት የግምሽ ዓመት አፈፃፀም ብንመለከት፤ የወጪ ንግድ ከ2010 ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ10 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስድስት ወራት አፈፃፀሙን ለህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ሲያቀርብ አስታውቋል፡፡ ሀገሪቱ በ2010 በጀት ዓመት ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግዷ ብታገኝም፤ ይህ አሀዝ ታዲያ ከዓመት ዓመት እያሽቆለቆለ የመጣውን የወጪ ንግድ አሳሳቢነትና አስጊነት አመላካች ነው፡፡
ለወጪ ንግድ ማሽቆልቆል ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ውስጥ ቀዳሚው በተለይም የግብርና ምርቶችን በጥራትና በስፋት ለገበያ አለማቅረብ ይሁን እንጂ፤ የኮንትሮባንድ ንግድ ለንግዱ ማነቆ የሆነ ቀንደኛና ሁለተኛው ምክንያት ሆኖ ይነገራል፡፡ ከሀገሪቱ የወጪ ምርቶች የኮንትሮባንድ ንግድ የማይነካካው
|
በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በእጅጉ አሽቆልቁሏል - የተመድ ሪፖርት
ኢዜጋ ሪፖርተር
January 29, 2020 (Ezega.com) -- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድ እና ልማት ጉባዔ ይፋ ያደረገው ‹‹ኢንቨስትመንት ትሬንድስ ሞኒተር›› የተሰኘው ዓመታዊ ሪፖርት በኢትዮጵያ ከአራት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ቅናሽ መመዝገቡን ይፋ አድርጓል፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ እየቀነሰ የመጣው የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰት መጠን ከ3.2 ቢሊዮን ዶላር ወደ 2.5 ቢሊዮን ዶላር መውረዱን የተመድ ሪፖርት አስታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2016 4.2 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በማስመዝገብ ኢትዮጵያ ከዓለም ትልልቅ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሀገራት መካከል አንዷ እንደነበረች ያስታወሰው ሪፖርቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ዘርፉ እየተዳከመ መጥቷል ብሏል፡፡
ምንም እንኳን 2016 በፊት በኢትዮጵያ ሲመዘገብ የቆየው የውጭ ቀጥተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት ከ2.2 ቢሊዮን ዶላር ያነሰ የነበረ ቢሆንም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ግን በአስደናቂ ሁኔታ እያደገ በመምጣት ከአህጉሪቱ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሚባል መጠ
|
ቱሪዝም፤ ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ - ስር የሰደዱ ችግሮቹና የተሰጠው ትኩረት
በሠላም ዓለሙ
መግቢያ
January 19, 2020 (Ezega.com) -- የተባበሩት መንግስታት ድርጅትየትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ረቡዕ ታህሳስ አንድ ቀን 2012 ዓ/ም ይፋ ያደረገው መረጃ ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ሀሴት ነው፡፡ ተቋሙ ይፋ ባደረገው መረጃው፣ ጥምቀትን ጨምሮ አምስት የአለም ባህላዊ ቅርሶችን በማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች ዘርፍ፣ ‹‹በሠው ልጆች ወካይ ቅርስነት›› መመዝገቡን አስታውቋል፡፡
ከአንድ ሽህ አምስት መቶ ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ዘንድ በየአመቱ ጥር 11 የሚከበረው የጥምቀት በዓል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት መመዝገቡ ታውቋል፡፡ የዓለም ቅርሶችን እያጠና በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ዘርፎች መዝግቦ እውቅና የሚሰጠው ዩኔስኮ ጥምቀትን በዓል በማይዳሰሱ ቅርሶች መመዝገቡ ለቱሪዝም ፍሰቱ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው እሙን ነው፡፡
ከዳሎል እስከ ራስ ዳሸን፣ ከሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ እስከ ነጭ ሳር ፣ ከወጥ አለት ከተፈለፈሉት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክር
|
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ግዙፉን አየር ማረፊያ ሊገነባ ነው
ኢዜጋ ሪፖርተር
January 19, 2020 (Ezega.com) -- በአፍሪካ ቁጥር አንድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዓመት ዓመት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣውን የደንበኞች ቁጥር ታሳቢ በማድረግ በአህጉሪቱ በግዝፈቱ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ አየር ማረፊያ ግንባታ ሊጀምር ነው፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም ለኢዜአ እንደገለጹት ግንባታው በተያዘው ዓመት የሚጀመረው አዲሱ ፕሮጀክት 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግለት ይሆናል፡፡ በእዚህም የህዳሴውን ግድብ ጨምሮ በኢትዮጵያ ካሉ ማናቸውም ፕሮጀክቶች የበለጠ በጀት የተመደበለት መሆኑ ተነግሯል፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው እንደተናገሩት ‹‹በቅርቡ አስደናቂ የደንበኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ማስፋፊያ በቦሌ አየር መንገድ አከናውነናል ይህም አየር ማረፊያውን በጣም ውብ እና ሰፊ አድርጎታል፡፡ ያም ሆኖ አሁን እያደግን ያለንበትን ፍጥነት ከግምት ስናስገባ ከ 3 ወይም ከ 4 ዓመታት በኃላ አየር ማረፊያው ሙሉ በሙሉ ይሞላል ለእዚህ ነው አዲሱን ፕሮጀክት ማንቀሳቀስ የጀመርነው›› ብለዋል፡፡
አየር መንገ
|
ከአይኤምኤፍ ብድር ጀርባ
በሠላም ዓለሙ
January 11, 2020 (Ezega.com) -- ባለፈው ወር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ለኢትዮጵያ የሦስት ቢሊዮን ዶላር ብድር ማፅደቁ አይዘነጋም፡፡ የህዝብ ቁጥሯ አንድ መቶ አስር ሚሊዮን ይጠጋል የምትባለው ኢትዮጵያ፤ ባለፉት ሁለትና ሦስት አስርት ዓመታት ዓለም ባንክን እና አይኤምኤፍን ከመሰሉ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት እንዲሁም ከባለፀጋ ሀገራት ረብጣ ቢሊዮን ዶላሮችን በተለይም ለትላልቅ ፕሮጀክቶች ስትበደር ኖራለች፡፡ የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ለማድረግ ላይ ታች እያለች ያለችው ኢትዮጵያ ግቧን ለማሳካት የገንዘብ ፈሰስን ከተለያዩ አካላት እያማተረች ነው፡፡ ከሣምንታት በፊትም ሀገሪቱ የተዛባውን ጥቅል ምጣኔ ሀብት ለማስተካከል ሲባል ለተነደፈው የሀገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ የሦስት ቢሊዮን ዶላር ብድር አፅድቋል፡፡
እስካሁን የ26 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ ናላዋ ላይ የሚዞረው ኢትዮጵያ የአይኤምኤፍ ብድር በሸክም ላይ ሸክም እንዳይሆ በስጋት የሚያዩት ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ብድሩ በአወንታዊ ጎኑ ሀገሪቱ በሚቀጥሉት ሦስ
|
መንግስትና የአለም ባንክ በሀገሪቱ የዕድገት ትንበያ ላይ አልተስማሙም
ኢዜጋ ሪፖርተር
January 11, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተያዘው 2020 የሁለት አሀዝ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ በመንግስት የቀረበው ትንበያ የተጋነነ ነው ሲል የዓለም ባንክ አስታወቀ፡፡ ባንኩ ባስቀመጠው የዓመቱ ትንበያ መሰረት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሊያድግ የሚችለው በ6.3 በመቶ ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ትንበያ በ2020 የሀገሪቱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት 10.8 በመቶ ይደርሳል ብሎ ያስቀመጠ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር በ1 በመቶ ብልጫ እንደሚያሳይ ተገልጾ ነበር፡፡ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና ለማበረታታት በመንግስት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ለትንበያው መሰረት መሆናቸውን ቢገልጽም የዓለም ባንክ ትንበያ ግን መንግስት ካስቀመጠው ጋር ሲነጻጸር ሰፊ ልዩነት የታየበት ሆኗል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዓለም ባንክ አዲሱ የዕድገት ትንበያ ከአንድ ወር በፊት ይፋ አድርጎት ከነበረው የ 9.0 በመቶ ዕድገትም ያነሰ ሊሆን ችሏል፡፡ በአሁኑ የተቋሙ ሪፖርት መሰረት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመጪው 2021
|
የልማት ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ማዘዋወር (ፕራይቬታይዜሽን)፤ ምንነቱና ውዝግቦቹ
በሠላም ዓለሙ
December 21, 2019 (Ezega.com) -- የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደር ወደ ኃላፊነቱ ብቅ ሲል አሳካለሁ ብሎ ከወጠናቸው ስራዎች መካከል ፊት ተጠቃሽ ነው፤ ፕራይቬታይዜሽን፡፡ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግሉ ክፍለ ምጣኔ ሀብት ማዞር ወይም ፕራይቬታይዜሽን ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ወዲህ መንግስት መውሰድ የጀመረው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ አካልና ቀዳውሚውም ነው፡፡ ሆኖም ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት መንግስት በበላይነት የያዛቸውን የልማት ድርጅቶቹን ለምን ለመሸጥ ገለገ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ በተለይም የፕራይቬታይዜሽኑ አካሄድ እንደ ዓለም ባንክ ባሉ ተቋማት የቀረበ የርዕዮተ ዓለም ተፅዕኖ ውጤት ነው የሚቃወሙት የዘርፉ ተንታኞች አልጠፉም፡፡ መንግስት በበኩሉም ድርጅቶቹን ሙሉ በሙሉና በከፊል ለማዘዋር ሲወስጥን ጥቂት የማይባሉ ምክንያቶች እጁን እንደጠመዘዙት ይናገራል፡፡ ያም ሆነ ይህ መንግስት በውሳኔው ፀንቶ በእስካሁን ሂደቱ፤ የቴሌ ኮሚኒኬሽን ዘርፉን የሚያስተዳድር የህግ ማዕቀፍና ባለስልጣን መ/ቤትም አቋቁሟል፤ ዘርፉንም ሁለት ተፎካካሪ ኩባንያዎች እንዲቀላቀሉት ውሳኔ
|
ኢትዮጵያ የአይ ኤም ኤፍን ድጋፍ ለማግኘት የምንዛሬ ተመኗ በገበያ እንዲወሰን ለማድረግ ተስማምታለች
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 13, 2019 (Ezega.com) -- ዋዜማ ራዲዮ- በሶናሊ ጄን ቻንድራ የተመራው የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የልዑካን ቡድን አመታዊውን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በተለምዶ ”article 4 consultation” የሚባለውን ምክክር ከፈረንጆቹ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 8 በአዲስ አበባ ካደረገ በሁዋላ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት 2.9 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለቀጣይ ሶስት አመታት መንግስት ”የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ” ብሎ ለሰየመው መርሀ ግብር ለማቅረብ ቅድመ ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል። የአለማቀፉ ገንዘብ ተቋም ቦርድ ጥር ወር ላይ ተሰባስቦም ብድርና ፈንዱን ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ከውሳኔ እንደሚደርስ ሰፊ ግምት እንዳለም ዋዜማ ራዲዮ ሰምታለች።
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋምና የኢትዮጵያ መንግስት የደረሱት ስምምነት በኢትዮጵያ በብዙ መልኩ በኢኮኖሚው ላይ ብርቱ ተፅዕኖ የሚፈጥር ውሳኔ መሆኑ በባለሙያዎች እየተነገረ ነው። የገንዘብ ተቋሙ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ ለሶስት አመታት
|
በተቋማቱ ውዝግብ የታገተው የባቡር ፕሮጀክት በጠ/ሚንስትሩ መፍተሄ አገኘ
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 13, 2019 (Ezega.com) -- በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እና በኤሌክትሪክ ኃይል አቅራቢው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል በተፈጠረ ውዝግብ አገልግሎት መጀመር የተሳነው ግዙፉ የአዋሽ- ኮምቦልቻ- ሃራ -ገበያ የባቡር ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ጣልቃ ገብነት ውሳኔ ማግኘቱ ተሰምቷል፡፡ በኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫዎች ከ5 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የባቡር መስመር ለመዘርጋት በጠቀመጠው የዕድገት እና ትራንስፎረሜሽን ዕቅድ መሰረት ግንባታዉ ከ 4 ዓመታት በፊት የተጀመረዉ የአዋሽ-ወልድያ-ሃራ ገበያ የባቡር መስመር ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ተጠናቋል፡፡
ያም ሆኖ ለርክክብ እና ለአገልግሎት የተዘጋጀው ይህ የ 1.7 ቢሊዮን ዶላር ፕሮጀክት በዋናነት በኤሌክትሪክ ኃይል አለመኖር የተነሳ እስካሁን ድረስ አገልግሎት መስጠት ሳይችል ቀርቷል፡፡ የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ችግሩ የተፈጠረው ኃይል አቅራቢው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተደጋጋሚ ጥያቄያችን ምላሽ መስጠት ስላልቸለ ነው በማለት ይከሳል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌ
|
ለኢኮኖሚ ማሻሻያው ከሚያስፈልገው ገንዘብ 60 በመቶው ከዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ተገኝቷል - ገንዘብ ሚኒስቴር
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 12, 2019 (Ezega.com) -- ኢትዮጵያ ለቀረጸችው የሶስት ዓመት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ማስፈጸሚያ ከሚያስፈልጋት 10 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ለመሸፈን መስማማታቸው ተነገረ። የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ እንዳስታወቁት ለአጠቃላይ ሀገር በቀሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራው ትግበራ በሶስት ዓመታት ውስጥ 10 ቢሊየን ዶላር የሚያስፈልግ ሲሆን ከዚህ ውስጥ የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ትልቁን ድርሻ ማለትም ከ6 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነውን ለመሸፈን ተስማምተዋል፡፡ ‹‹ከሁለቱ ተቋማት ጋር ተግባብተን የሀገር በቀሉን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በተለየ ሁኔታ የሀብት ማሰባሰብ ስራ ተሰርቶ ይሄንን ለመደገፍ ተስማምተው ነው ያሉት ነገር ግን የመጨረሻው ‹አፕሩቫል› በሚቀጥለው ሳምንት ወይም ሁለት ሳምንት ውስጥ የሚያልቅ ይሆናል ለቦርድ ቀርቦ›› በማለት ሚንስትር ዲኤታው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ይህንን ከፍ
|
የሀገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 4, 2019 (Ezega.com) -- በኢትዮጲያ በተለይ ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ጋራ በተያያዘ የኑሮ ውድነቱ ከእለት ወደ እለት በከፍተኛ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ነዋሪዎች በምሬት ያነሳሉ፡፡ የሚመለከታቸው የፌደራል መንግሰት እና የክልል መስተዳድር አካላት ለችግሩ እልባት ለመስጠት እየሰራን ነው የሚል ተደጋጋሚ ምላሽ ሲሰጡ ቢቆዩም ነገሮች እየተባባሱ መምጣታቸው እየታየ ነው፡፡ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ዛሬ ይፋ ያደረገው መረጃም ይህንኑ ያረጋጋጠ ሆኗል፡፡ በተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊ የሆኑት አቶ አማረ ለገሰ በሀገሪቱ ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ቀርበው እንደተናገሩት በኢትዮጲያ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በተለይ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቶ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ 18.6 በመቶ ደርሷል፡፡ እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ጭማሪው አጠቃላይ የምርት እና የአገልግሎት የዋጋ ግሽበት ያስከተለ ቢሆንም የዋጋ ንረቱ በከፍተኛ ደረጃ ያየለው ግን በተለይ ምግብ ነክ በሆኑ ምርቶች ላይ ነው፡፡
በዚህም መሰረት ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ምግብ ነክ የሆኑ ምርቶች የዋጋ
|
የቻይናው አሊባባ በኢትዮጲያ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሊጀምር ነው
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 27, 2019 (Ezega.com) -- የቻይናው ቁጥር አንድ ቢሊየነር እና የአሊባባ መስራች ጃክ ማ ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ በቀረበለት ግብዣ መሰረት በኢትዮጲያ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡ ኩባንያው ካለው እጅግ የገነነ ዓለም አቀፍ እውቅና እና ስኬት አንጻር ጉብኝቱ በተለይ ሀገሪቱ የናፈቀችውን ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ለማስፋፋት አቋራጭ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ተስፋ አድርገዋል፡፡
ተስፋውን ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየር ያስችላል የተባለለት ስምምነትም በኢትዮጲያ እና በአሊባባ ኩባንያ መካከል በአዲስ አበባ ተፈርሟል፡፡ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንሰትሩ ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና በአሊባባ ኩባንያ ተወካይ አማካኝነት የተፈረመው ስምምነት ዓለም አቀፍ የኤሊክትሮኒክ ግብይትን በኢትዮጲያ ለመጀመር የሚያስችል መሆኑ በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ በመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ የፊርማ ስነስረዓት ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ እንዳሉት የተደረሰው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትብብር ስምምነት ኢትዮጲያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ከአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ 5 ግዙፍ ኢ
|
35 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ የዳያስፖራ አባላት የንግድና ኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስዱ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 18, 2019 (Ezega.com) -- በተያዘው 2012 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺህ 32 በላይ ዳያስፖራዎች ከ 35 ቢሊዮን ብር የሚልቅ የካፒታል መጠን አስመዝግበው የንግድና ኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ይህንን ያለው ከፌዴራልና ከሁሉም ክልሎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ ባደረገው ውይይት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት እና የቀጣይ ጊዜያት እቅዶች ላይ ለተሰብሳቢው ማብራሪያ ሰጥተዋል። እንዲሁም የኤጀንሲው የክልል ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች እና የዳያስፖራ ማህበራት የበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል። በኤጀንሲው የዳያስፖራ ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ማስሬ እንዳብራሩት በተያዘው ዓመት በቁጥር በርካታ የሆኑ ዳያስፖራዎች በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፎች የጎላ ተሳትፎ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማ
|
የአንበጣ መንጋው ሀገራዊ ስጋት እየሆነ ነው - የግብርና ሚኒስቴር
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 5, 2019 (Ezega.com) -- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጲያ አድማሱን በፍጥነት እያሰፋ የመጣው የበረሃ አንበጣ በሀገሪቱ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ሶማሌ ክልሎች በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል ጋንታሞ እንዳስታወቁት የበርሃ አንበጣውን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉት ስራዎች እምብዛም ውጤታማ እየሆኑ አይደሉም፡፡ ለእዚህም በተለይ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆን ዋነኛ ምክኒያት እየሆነ ነው።
ወረርሽኙ አሁንም በተለይ በአራቱ ክልሎች አስጊነቱ እንደቀጠለ ነው ያሉት ዳሬክተሩ ከባለፉት ሳምንታት አንስቶ የአንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች በባሕላዊ መንገድ፣ በሰው ኃይል እና በማሽን በመታገዝ የመከላከል ሥራ እየተሰራ እንደሆነ አስታወቀዋል፡፡
ምንም እንኳን ይህንን የመሳሰሉ የመከላከል ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም የአንበጣ መንጋው አየተዛመተ ካለበት ፍጥነት ጋር ሲነጻጸር ግን ችግሩ ለሀገር የሚያሰጋበት ደረጃ ላይ እየደረሰ
|
|