የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኸን - በቅሎን ሲያታልሏት አስረዝመው አሰሯት
በህይወት ዳምጤ
እግር ከወርች የታሰረው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኸን ምን አይነት ማሻሻያ ያስፈልገዋል?
April 30, 2019 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኸን ታሪክ ጅማሮ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ምኅዳሩን በተቀላቀለችው አእምሮ ጋዜጣ መበሰሩን የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡ ታዲያ አንድ ምዕተ ዓመትን የተሻገረው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ኢንዱስትሪ ምን ያህል ርቀትን ተጓዘ ለሚለው በመንግስት የበላይነት ተጠፍንጎ ስለመጓዙና እስካሁንም እንደሚገኝ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ከቀዳማዊ አፄ ኃይለ ስላሴ መንግስት ጀምሮ እስከ ዛሬው መንግስት ድረስ የመገናኛ ብዙኸን ነፃነት ከገዢ መንግስታት መዳፍ መላቀቅ አለመቻሉንም የዘርፉ ምሁራን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡
ከሳምንታት በፊት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ (ECA) በሲዊድን ኤምባሲ አዘጋጅነት በመገናኛ ብዙኸን ዙሪያ የመከረ ጉባኤ ለሁለት ቀናት ተካሂዷል፡፡ በዚህ መድረክ ንግግር ካደረጉት ሙህራን ውስጥ አንዱ የሆኑት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርና የመገናኛ ብዙኸን ህግ ሙህር ፕሮፌሰር ዘካሪስ ቀና፤ የ
|