ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን መስጠታቸውን መንግስት አስታወቀ
December 1, 2020 (Ezega.com) -- የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እጃቸውን ለመንግስት መስጠታቸው ተነገረ፡፡
በፌደራል መንግስት እና በህወሃት መካከል እየተካሄደ በከረመው ጦርነት መካከል መንግስት ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳባቸውና የእስር ትእዛዝ ካወጣባቸው የህወሃት አመራሮች አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ኬርያ በመንግሥት ውስጥም ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት የነበራቸው መሆናቸው ይታወቃል። ወ/ሮ ኬሪያ የሁለቱን አካላት አለመግባባት ተከትሎ በተለይም በትግራይ ክልል ምርጫ መካሄድ አይችልም የሚለውን የመንግስት አቋም በመቃወም የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤነት ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀው ወደ መቀሌ አቅንተዋል። በወቅቱ ወደ መቀሌ ሲሄዱ አድርሷቸው የነበረው ሾፌራቸው ከስፍራው በመሰወር መኪናውን ይዞ ወደ አዲስ አበባ መመለሱን ያስታወሰው የመንግስት መረጃ አሁን ወ/ሮ ኬሪያ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ለመንግስት ሰጥተዋል ሲል አስታውቋል። ያም ሆኖ እጃቸውን መቼ፣ የትና በምን ሁኔታ እንደሰጡ ግን የተሰጠ ማብራሪያ የለም። እስካሁን ስለ ሁኔታው ከህወሃት በኩል የቀረበ ምላ
|
ህወሃት አስመራን በርቀት ሚሳይሎች ደበደበ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 14, 2020 (Ezega.com) -- የኤርትራዋ ርእሰ መዲና አስመራ ማምሻውን ከትግራይ ክልል በተተኮሱ ሚሳኤሎች መመታቷን የተለያዩ ምንጮች እየዘገቡ ይገኛሉ። ታዋቂው የብሪታኒያ እለታዊ ጋዜጣ ዘ ቴሌግራፍ (The Telegraph) ወደ አስመራ የተተኮሱት ሚሳኤሎች ከሁለት የማያንሱ ናቸው ብሏል። ጋዜጣው ከስተቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተከፈተው የእርስበርስ ጦርነት ቀጠናዊ መልክ ይዟል ነው ያለው። ኤርትራን ሀብ (Eritrean Hab) የተሰኘው ጋዜጣ በበኩሉ የተተኮሱት ሶስት ሚሳኤሎች መሆናቸውንና የከተማዋ አየር ማረፊያና የመረጃ ሚኒስቴር ሳይመቱ እንዳልቀረ በውጭ የሚኖሩ ኤርትራውያን ዘመዶቻቸው ጋር ደውለው ማረጋገጣቸውን ጠቅሷል። በጥቃቱ ወቅት በአስመራ ከፍተኛ ድምጽ ያለው ፍንዳታ እንደነበር የከተማዋ ነዋሪዎች መናገራቸውን የዘገበው ሪፖርቱ አንድ የመኖሪያ ህንጻ መመታቱንም ጽፏል። ተኩሱ በከተማዋ መብራት እንዲቋረጥ አድርጓል ያለው ዘገባው ከጥቃቱ ቀደም ብሎ የትግራይ ቴሌቭዥን ኤርትራ ቀጣይዋ ኢላማ ልትሆን ትችላለች ሲል መዘገቡን አስታውሷል።
የተፈጸመው ድርጊት ግጭቱን ወደ አለምአቀፍ ደ
|
ህወሃት በባሕርዳር እና በጎንደር የሮኬት ጥቃት ፈጸመ፣ አስመራን አስጠነቀቀ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 14, 2020 (Ezega.com) -- ህወሃት ትናንትና ምሽት አምስት ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ዋና ከተማ በባህርዳር እና በአቅራቢያው በምትገኘው ጎንደር አውሮፕላን ማረፊያዎች አቅራቢያ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል። በተለይ በትግራይ ክልል የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ተያያዥ መረጃዎች ለህዝብ እንዲሰጥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ የሮኬት ተኩሱ መፈጸሙን አረጋግጧል። ዛሬ ጠዋት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያው የተሰጠው አጭር መግለጫ እንደሚያሳየው በጥቃቱ በአውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ስግብግቡ ጁንታ ብሎ በጠራው ሃይል ጥቃቱ እንደተፈጸመም አስታውቋል። በተጨማሪም "ቡድኑ በእጁ ያሉትን የመጨረሻዎቹን መሣሪያዎች ጠጋግኖ የጥፋት ሙከራውን አድርጓል" ያለው መግለጫው የክስተቱን ዝርዝር መርማሪ ቡድን ተመድቦ እያጣራው መሆኑን ጠቅሶ ሙሉ መረጃው በቀጣይ ለህዝብ የሚገለጽ እንደሆነ ተነግሯል። ኢዜጋ በጎንደር ከሚኖሩ ግለሰቦች እንደሰማው ከም
|
ጠቅላይ ሚንስትሩ ድንገተኛ ሹም ሽር አደረጉ
ኢዜጋ ሪፖርተር
Novmber 8, 2020 (Ezega.com) -- ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዛሬ ቁልፍና ድንገተኛ የተባሉ ሹም ሽሮችን አካሄደዋል። ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደተፈጸሙ የተነገሩት ሹም ሽሮች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል መንግስት ባለስልጣናትን ማእከል ያደረጉ ናቸው በዚህም መሰረት፦
- አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
- ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መርጃና ድህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ
- ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
አዳዲሶቹ ሹመቶች የሀገሪቱን የጸጥታና የደኅንነት ብሎም የውጭ ግንኙነት አካላትን በማጠናከር የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ "በአጭር
|
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ወሰነ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 7, 2020 (Ezega.com) -- የፌዴሬሽን ም/ቤት ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋምና ሌሎች ተያያዥ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡ "ሕገወጡ የትግራይ ክልል መንግስት ወደ ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱ እንዲመለስ የተሰጠውን በቂ እድል መጠቀም ባለመቻሉ በክልሉ በሚገኘው ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አስነዋሪ ጥቃት ፈጽሟል በተጨማሪም በአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም በንፁሃን ዜጎችና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል" ያለው ም/ቤቱ የፌዴራል መንግስት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 359/95 አንቀጽ 12 በአንድ የክልል መንግስት ተሳትፎ ወይም ዕውቅና ሕገመንግስቱን ወይም ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን ባለማክበር የሚደረግ እንቅስቃሴ ወይም ድርጊት በተለይም በትጥቅ የተደገፈ የአመጽ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ከሌላ ክልል ወይም ከሌላ ክልል ብሔር፣ ብሄረሰብ ወይም ሕዝብ ጋር የተፈጠሩ ችግሮችን ሰላማዊ ባልሆነ መን
|
በህወሃት ላይ የተወሰደው የመጀመሪያ ዙር ኦፕሬሽን በስኬት ተጠናቋል - ዐቢይ አሕመድ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 6, 2020 (Ezega.com) -- በህወሓት ውስጥ "የመሸገው ኃይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። የመጀመሪያው የመከላከል እቅድ ሙሉ ለሙሉ በስኬት መጠናቀቁን የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ የእቅዱ ዋነኛ አላማዎች በሁሉም አቅጣጫ "የጥፋት ሃይሉ" ጥቃት እየሰነዘረ በህዝብ፣ በሰራዊቱ፣ በፖሊስ ላይ እና በአንዳንድ ወሳኝ የመሰረተ ልማቶች ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት መግታት፣ የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊት የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ ይህንን ኃይል የመታደግ እና ወሳኝ ሀገራዊ ሀብቶች አና ትጥቆች መታደግ እና "የጠላትን የማድረግ አቅም ማዳከም" ነው ብለዋል። "በተለያየ አካባቢ ይገኝ የነበረ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ወደ ስፍራው በማንቀሳቀስ የጠላትን ጉዞን ሙሉ ለሙሉ በማስቆም ተጨማሪ ጥቃት መሰንዘር ወደማይችልበት ደረጃ ማድረስ ተችሏል" ያሉት አብይ አህመድ በባድመ ግንባር፣ በፆረና እና በዛላንበሳ በዋና ዋ
|
መከላከያ ሠራዊት በሕወሃት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ ታዘዘ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 3, 2020 (Ezega.com) -- ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ የአገር መከላከያ ሠራዊት በህወሃት ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ መሰጠታቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሊቱን በአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው "ይህንን ጡት ነካሽ ኃይል ለማሳፈር እና ለመደምሰስ አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን እገልጻለሁ" በማለት በይፋ ጦርነት መከፈቱን አስታውቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ መከላከያ ሠራዊት አገር የማዳን ግዳጅ እንደተሰጠውም ያስታወቁ ሲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከመቀሌ ጀምሮ በበርካታ ስፍራዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሞበታል ብለዋል፡፡ ይህ ጥቃት በሀገራችን እስካሁን ከደረሱ ጥቃቶች እጅግ አስነዋሪ የሚያደርገው ሠላም ለማስከበር በተሰማራው መከላከያ ሠራዊት በውጭ ሀይሎች ያልደረሰበትን ጥቃት በገዛ ወገኖቹ ከጀርባው እንዲመታ፣ ብዙዎች እንዲሰው ፣እንዲቆስሉ፣ ንብረቶች እንዲወድሙ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ "ሕወሐት በትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሷል፡፡ ሰሜን ዕዝንም ለመዝረፍ
|
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን በኖርዌይ ተቀበሉ
ኢዜጋ ሪፖርተር
December 10, 2019 (Ezega.com) -- ባሳለፍነው መስከረም ወር የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኖርዌይ ኦስሎ በተደረገ ደማቅ ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ በተከናወነው የኖቤል የሰላም ሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ ዘለግ ያለ ንግግርም አድርገዋል። በተለይም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካካል የተካሄደውን ጦርነት በማንሳት እና ስለ ሰላም አስፈላጊነት በማብራራት ንግግራቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ “ሰላም እንደ ዛፍ ችግኝ ነው ችግኝን ተክሎ ለማሳደግ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ሰላምም ጥሩ ልብ እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ዛሬ እዚህ ቆሜ ስለ ሰላም የምናገረው የእድል ጉዳይ ሆኖ ነው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ጦርነት ሲጀመር ወጣት ወታደር ነበርኩ የጦርነትን አስከፊነትን በአካል ተገኝቼ «ወንድም ወንድሙን ሲገድል» ተመልክቻለሁ ያሉት ዶ/ር ዐብይ ጦርነትን ያላዩ በደፈናው ግን የሚያወድ
|
ሲዳማ የሀገሪቱ 10ኛው ክልል መሆኑ ተረጋገጠ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 23, 2019 (Ezega.com) -- ህዳር 10, 2012 ዓ.ም በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ የመጀመሪያ ዙር ውጤት መሰረት ሲዳማ 11ኛው የሪፐብሊኩ ክልል ሆኖ ለመደራጀት የሚያስችለውን 98.51 በመቶ ድምፅ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡ ቦርዱ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳስታወቀው ለህዝበ ውሳኔው ከተመዘገበው 2.3 ሚሊዮን መራጭ ውስጥ 2 ሚሊዮን 277 ሺህ 63 ሰው ድምፁን የሰጠ ሲሆን ይህም ማለት ከተመዘገበው ህዝብ 99.86 በመቶ የሚሆነው ሰው ድምፁን መስጠቱን ያሳያል፡፡
በምርጫ ቦርዱ መረጃ መሰረት ድምፃቸውን ከሰጡት ሰዎች መካከልም 2 ሚሊዮን 225 ሺህ 249 የሚሆኑት ድምጻቸውን ለ ‹ሻፌታ› ሲሰጡ ይህም ከጠቅላላ መራጩ 98.51 በመቶ መሆኑ ታውቋል፡፡ በተቃራኒው ‹ጎጆን› የመረጠው ጠቅላላ ህዝብ ብዛት ደግሞ 33 ሺህ 463 ወይም ከጠቅላላው መራጭ 1.48 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ መሰረት ይፋ በተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ የህዝበ ውሳኔው ውጤት ሲዳማ ክልል ሆኖ ለመደራጀት የሚያስችለውን ድምጽ ማግኘቱን ቦርዱ አስታወቋል።
|
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
December 15, 2018 - የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጠው ፕሬዚዳንቱ ለሊት ማረፋቸውን ሰምቷል፡፡
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነ ስርዓትም የፊታችን ረቡዕ ታህሳስ 10 2011 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈፀመም ተነግሯል።
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ታህሳስ 19 ቀን 1917 ዓ.ም. ነበር በመዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት፡፡
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ርዕሰ ብሔር ሆነው አገልግለዋል።
በጥቅሉ ፕሬዚዳንት ግርማ ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሄርነት ለ12 ዓመታት አገልግለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ የፓርላማ አባል በመሆን ነበር ሀገርንና ህዝብን ማገልገል የጀመሩት፡፡
የቀድሞ ፕ
|
ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ተይዘው አዲስ አበባ ገቡ
November 13, 2018 - ሁመራ ላይ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በፖሊስ ተይዘው አዲስ አበባ ገቡ።
ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን ሀብት በመመዝበር ተጠርጥረው የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸው ቆይተዋል።
በዚህም በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል ወደ ሱዳን ሊኮበልሉ ሲሉ ሁመራ አካባቢ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የፌዴራል አቃቤ ሕግ ኮርፖሬሽኑ ከ2004-2010 ዓ.ም ድረስ ከ37 ቢሊዮን ብር በላይ የውጭ አገር ግዥ ያለጨረታ መፈጸሙን ትናንት መግለጹ ይታወቃል።
ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት አስራርና ሕግ በመተላለፍ ትላልቅ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዥዎችን ሲፈጽም ቆይቷል።
ከተጠርጣሪዎች መካከል ከአራት ግለሰቦች በስተቀር ቀሪዎቹ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ ያገለገሉ ናቸው።
Source: ENA
|
መአዛ አሸናፊ የመጀመርያዋ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆኑ
November 1, 2018 - ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመርያዋ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ዳኜ መላኩ በፈቃዳቸው የሥራ መልቀቂያ በማቅረባቸው ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊን በዕጩ ፕሬዚዳንትነት አቅርበው አሹመዋል፡፡
ወ/ሮ መአዛ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የተወለዱ ሲሆን፤ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ በሕግ ትምህርት አግኝተዋል፡፡ በአሜሪካ ኬንታኪ ዩንቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ግለ ታሪካቸው ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ መዓዛ በንግድ ሚኒስቴር የሕግ ባለሙያነት፣ በከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት እንዳገለገሉ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበርን በመመሥረትና በመምራት ለሴቶችና ለሕፃናት መብትና ፍትሕ መታገላቸውንም ገልጸዋል፡፡ በንግድ ዓለምም ውጤታማ እንደሆኑ
|
ትልቅ አገር ለመገንባት ሠላም ወሳኝ ነው – ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ
October 25, 2018 - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ዛሬ ባካሄዱት አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በሙሉ ድምጽ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
″ትልቅ አገር ለመገንባት ከሠላም ውጪ አማራጭም አቋራጭም የለም” አሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ።
አዲሷ ፕሬዝዳንት በበዓለ-ሲመታቸው ላይ እንደተናገሩት፤ “ትልቅ አገር ለመገንባት ከሠላም ውጪ ምንም አማራጭ አልያም አቋራጭ የለም” ብለዋል።
ኢትዮጵያ የኋላቀር አገር ምልክት ሆኖ የቆየችው በዋንኛነት በሠላም እጦት እንደሆነና በተጀመረው ለውጥም ለሠላም እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ማስወገድ ይገባዋል ነው ያሉት።
ስለዚህም “ሠላም ከራሳችን፣ ከቤተሰብ፣ ከጎረቤቶቻችን፣ በመንደራችን፣ በወረዳዎች መካከል፣ በክልሎች መካከል፣ ከጎረቤት አገራት ጋርና በዲያስፖራም ሊኖር ይገባል” ብለዋል።
መንግሥትም ሆነ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንድ የጋ
|
አብዲ ሞሐመድ ዑመር ከእስር ቤት ለማምለጥ ሞክረዋል - ፖሊስ
October 19, 2018 - የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ከእስር ቤት ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤት ተናገረ።
አቶ አብዲ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀጠሯቸው መሰረት በቀረቡበት ወቅት ፖሊስ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና የጥበቃ አባልን በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።
አቶ አብዲ በበኩላቸው ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ እና ሆን ተብሎ ስማቸውን ለማጥፋት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል።
አቶ አብዲ ጨምረውም ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታራሚ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነቴ ላይ ስጋት ፈጥሮብኛል በማለት ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱ ኢቲቪ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ፖሊስ በአቶ አብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ የም
|
የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች ክስ ተመሠረተባቸው
September 28, 2018 - በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ፣ የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡
በቦምብ ጥቃቱ ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች አቶ ጌቱ ግርማ፣ አቶ ብርሃኑ ጃፋር፣ አቶ ጥላሁን ጌታቸው፣ አቶ ባህሩ ቶሎሳና አቶ ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው፡፡
ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክስ እንደገለጸው፣ ተከሳሾቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ላይ ግድያ ለመፈጸም ያነሳሳቸው በእሳቸው የሚመራ መንግሥት መኖር ስለሌለበት ነው፡፡ የአገሪቱ መንግሥት መመራት ያለበት ቀድሞ በተመሠረተው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው የሚል ዓላማ ተከሳሾቹ እንዳላቸው ዓቃቤ ሕግ በመሠረተው ክስ ጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም በማለትም
|
በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሠልፍ አምስት ሰዎች ሞቱ
September 17, 2018 - በአዲስ አበባ ብሔር ተኮር ጥቃቶችን በመቃወም ሠልፍ ከወጡ ሰዎች መካከል አምስት ሰዎች መሞታቸውንና ሌሎችም መቁሰላቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለመንግሥት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹የተወሰኑ በቡድን ተደራጅተው የፀጥታ ኃይሎችን መሣሪያ ለመቀማት ሞክረዋል፡፡ አከፖሊስ ጋር ግብግብ የገጠሙትን በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች የማያዳግም ዕርምጃ ወስደው የተወሰኑ ሰዎች መሞታቸውና መቁሰላቸው ታውቋል፤›› ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሠልፉ ውስጥ ቦምብ ይዘው የወጡ ግለሰቦች መገኘታቸውንና በሰላማዊ ሠልፉ ተሳታፊዎች ጥቆማ መያዛቸውን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡
በቡራዩና አካባቢውም ሆነ በአዲስ አበባ የተከሰቱትን ግጭቶች አስመልክተው የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ ግርግሩ ሆን ተብሎ የተጀመረውን ለውጥ እንዳይሳካ ለማድረግ ሰፊ የሆነ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የተካሄደ ነበር ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ገንዘብ ተሰጥቷቸው የተሰማሩ ግለሰቦች ብሔር ተኮር ስድብ የታከለበት እን
|
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን አጠፉ - ፖሊስ
September 7, 2018 - ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በሰው በደረሰባቸው ጉዳት ህይወታቸው እንዳላለፈና ራሳቸውን እንዳጠፉ የምርመራ ውጤቱ እንደሚያመላክት ፖሊስ ገለፀ።
ፖሊስ የኢንጂነር ስመኘውን አሟሟት በተመለከተ በሰጠው መግለጫ፥ ኢንጅነር ስመኘው ራሳቸውን ማጥፋታቸውን የተደረገው የምርመራ ውጤት ያመላክታል ብሏል።
ፖሊስ በመግለጫው ሞተው የተገኙበት መኪና ውስጥ የተገኘው ሽጉጥም በእርሳቸው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል።
በፎረንሲክ ምርመራ በተገኘው ውጤት መሰረትም የሽጉጡ ቀልሃና የተገኘው እርሳስም የዚሁ ሽጉጥ መሆኑን ፖሊስ እንዳረጋገጠ አስታውቋል።
ኢንጅነሩ ከመሞታቸው ቀደም ብሎ ባለው ቀን ባደረጉት የስልክ ልውውጥ፥ በአብዛኛው የስንብት ይዘት ያለው መልዕክትን ከልጃቸውና ፀሃፊያቸው ጋር ተለዋውጠዋልም ነው ያለው ፖሊስ።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ለፀሃፊያቸው ልጄን አደራ የሚል መልክዕክት ማስተላለፋቸውን የፌደራል ፖሊስ ጀ
|
የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ከሥልጣናቸው ለቀቁ
August 6, 2018 - የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶሕዴፓ) ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንደለቀቁ የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ እድሪስ እስማኤል ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡
እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ አቶ አብዲ ከክልሉ ፕሬዚዳንትነት ቢነሱም የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆነው ያገለግላሉ፡፡
በምትካቸውም የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንትና የውኃ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አህመድ አብዲ የክልሉ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት በመሆን ተመርጠዋል ሲሉም አቶ እድሪስ አስታውቀዋል፡፡
በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ በተነሳ አመጽ በርካቶች የሞቱ ሲሆን፣ ንብረቶች መዘረፋቸውን፣ የመኖሪያና ቤቶች፣ የንግድና የእምነት ተቋማት መቃጠላቸውም ታውቋል፡፡
ማምሻውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በሰጡት መግለጫ፣ የክልሉን ሰላምና ደኅንነት ወደነበረበት ለመመለስ የመከላከያ ኃይል ጣልቃ መግባቱን ገልጸው፣ የክልሉም ፖሊስ እንዲተባበርም ጥሪ አቅርበዋል፡
|
በሶማሌ ክልል ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ
August 4, 2018 - በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ ኢትዮጵያ የህዝቦቿን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ በለውጥ ሂደት ውስጥ እንደሆነች አንስቷል።
ለውጡም መላ የኢትየጵያ ህዝቦችን ባሳተፈ እና ባለቤት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል ያለው ሚኒስቴሩ፥ እየተካሄደ ካለው የለውጥ እንቅስቃሴም መላው የሀገሪቱ ህዝቦች ተጠቃሚ በመሆናቸው ተሳትፏቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ ብሏል።
ሆኖም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች አልፎ አልፎ የብጥብጥና የሁከት ድርጊቶች እንደሚስተዋሉ አስታውቋል።
እነዚህ ህገወጥ ድርጊቶች በሚስተዋሉባቸው አካባቢዎች የጸጥታ ሃይሉ ከህዝቡ ጋር ሆኖ የማረጋጋት ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ነው የገለፀው።
በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጂግጂጋ ከተማ የተከሰተው ብጥብጥ፣ ቀጥሎም ወደ ሌሎች አንዳንድ የክልሉ ከተሞች የተዛመተው ሁከት በምንም መልኩ ተቀባይ
|
በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ድጋፍ ሰልፍ ላይ በፈነዳው ቦምብ ምክንያት ዘጠኝ የፀጥታ አባላት ታሰሩ
June 23, 2018 - በመስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ለመደገፍ የተደረገው ሰልፍ ላይ ከደረሰው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ ዘጠኝ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
በሰልፉ ላይ በተወረወረ ቦምብ 154 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸውና አንድ ግለሰብ መሞቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመሆን በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን በሆስፒታሎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በተካሄደው ሰልፍ ላይ የደረሰው የቦምብ ፍንዳታ የተጠናና በሙያተኛ የታገዘ ነበር አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቂት የሞቱና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ለለውጥ ሲባል የተከፈለ መስዋዕትነት ነው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ባደረጉ ሰዎች ላይ ማዘናቸውንና የሞቱት ነፍሳቸው እንዲማር፣ የቆሰሉት እንዲታከሙ፣ ቤተሰቦች እንዲ
|
|