አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - መንግስት

ታሪኩ እንዳጠየቀው - ማነው እየሄደ እየሞተ ያለው?!

Tariku Gankasi Dishtaginaሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

November 14, 2021

“እኔ የምፅፈው ማንንም ለማስደሰት አይደለም። ማንንም ለማሳዘንም አይደለም። ሙግት ለመፍጠርም አይደለም። ውይይት ለማካሄድ ነው። አተካሮ ለመፍጠር አይደለም። የሰከነ ሀሳብ ማንሸራሸር ቢቻል ብዬ ነው…. በአጭሩ የሰከነ ውይይት ለመፍጠር ነው።”
(ጋሽ አሰፋ ጫቦ - የትዝታ ፈለግ)
 
አገራችን ወደቀውስ ከመግባቷ በፊት ጀምሮ ፖለቲካዊ ችግሮቻችንን በፖለቲካዊ ንግግሮችና በሁሉን አሳታፊ ድርድር በመፍታት በኢትዮጵያ ብልጭ ብሎ በርቶ የተዳፈነውን የለውጥ ተስፋ በሙሉ እንዳናመክነው ይልቁንም ወደትክክለኛው መስመር እንዲመለስ በዚሁ ገፅ እና በአገራችን የህትመት ብዙኃን መገናኛዎች በኩል ስናሳስብ ቆይተናል፡፡

አለመታደል ሆኖ ለውጣችን ከህዝብ ሠላምና ከአገራችን ዘላቂ አንድነት ይልቅ በሥልጣን ወዳዶች የእርስ በእርስ ትንቅንቅ እና በዋነኝነትም በኢህአዴጋውያን በኩል እንዲከሽፍ ሆኗል፡፡ የፌዴራሉ መንግሥት በኢፌዲሪ የመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት

ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ በኋላስ?! (ወግ መቋጫ)

After Abiy Ahmedሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
November 14, 2021

“In peace, sons bury their fathers. In war, fathers bury their sons!”
(ሄርዱተስ፤ ግሪካዊ የታሪክ ሰው)

ሥልጣኔያችን… ቢሰለጥንስ?!

ኢትዮጵያችን የረዥም ጊዜ ሥልጣኔ ያላት አገር ስለመሆኗ ሲነገር መስማት እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ በሸኘናቸው ዓመታት አላስፈላጊና የማይናፀር ፉክክር ውስጥ እየተገባም “እነሱ አገር ከመሆናቸው በፊት እኛ መንግሥት ነበርን!” በማለት አሜሪካንና አውሮጳውያኑ ምሳሌ ሲደረጉም አስተውለናል፡፡ በመሰረቱ ሆኖ በመገኘት፤ በምግብ እህል ራስን በመቻል፤ በፖለቲካ ሥልጣኔና ዴሞክራሲያዊ ዝማኔም የዚያኑ ያህል በመግፋትና በቁሳዊ ብልፅግናም ካልታጀበ “ነበረን” ማለቱ ብቻውን በቂ አይሆንም፡፡ ነበረን ለምንለው ነገር ሁሉ ያለንን ካልደመርንለት ትናንት ላይ ቆሞ-ቀርነታችንን እና የታሪክ ምንጣፍ ላይ ተኝተን መቅረታችንን ከማጋለጥ የተሻገረ ርባና ይኖረዋል ብዬም አላምንም

ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ… በኋላስ?! (ሶስተኛው ክፍል)

After Abiy Ahmed 3ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
October 21, 2021

“Educating the mind without educating the heart is no education at all.”
(አርስቶትል)

ፈር ማስያዥያ…!

በቀደሙት ሁለት ክፍሎች በኪናዊ ስራዎች እያዋዛን የተመለከትነውን የ“ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” ልማዳዊ እንከናችንን ዛሬም መሞገት እንቀጥላለን፡፡ አባባሉም እንደሚል “ንጉሥ ሞተዋል… ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” ሆኖ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሥልጣን ከኢህአዴግ ወደ ኢህአዴግ ቢሆንም ሥልጣንን የመያዣውና የማስቀጠያው መንገድ ከብልፅግና ወይም “ከዓቢይ አህመድ ዓሊ…. በኋላስ?” እንዴት ሊሆን ይችላል ወይም ምን አይነት መሆን ይኖርበታል የሚለው ነጥብ ላይ ዛሬም አለመግባባታችን ለነገ ሌላ ዙር የግጭትና ጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳይዶለን መስጋቱ ተገቢ ይሆናል፡፡

ከእነዚያ ፅሁፎች በኋላ ዘላቂ ሠላምንና መግባባትን እን

ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ… በኋላስ?! (ሁለተኛው ክፍል)

After Abiy Ahmed 2ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
October 21, 2021

“If history repeats itself and the unexpected always happens, how incapable must Man be of learning from Experience?”
(ጆርጅ በርናንድ ሾው)

ጦርነት እና የነባሩ “ባህላችን” አበርክቶ!
 
በቀደመው ፅሁፍ የነካካነው የ“ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” ነባር “ኢትዮጵያዊ” ባህል ከትውልዳችን ዕሴቶች ጋር መቃረኑ፤ ለፖለቲካዊ ጥያቄዎችና ግቦች ብሎም ለሥልጣን መደላድል ሲባልም የጦር ባህልን ዋነኛ መሳሪያው ማድረጉ ሺህ ዓመታትን እንደተሻገረ የተለያዩ የታሪክ ወፖለቲካ ድርሳናት ይነግሩናል፡፡ የኢህአዴግ ሥርዓት አልባና ህግን ያልተከተለ ፍርሰት ጦሱ ለአገራችንም ተርፎ እነሆ ጦርነትን ቀዳሚው ምርጫችን እንዳደረግን በአዝማናት መካከል ቀጥለናል፡፡

ይህን የጦር ባህልን ያለመግራታችን ብዙ እንደሚያስከፍለን ቢታወቅና በዚህ መ

ኢትዮጵያ ከዓቢይ አህመድ ዓሊ… በኋላስ?! (ቀዳሚው ክፍል)

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
October 21, 2021

“Those who cannot remember the past are condemned to repeat it.”
(ጆርጅ ሳንታያና፤ ስፔናዊ አሰላሳይና ደራሲ)

After Abiy Ahmedይሄንን ፅሁፍ ሳሰናዳና ይህንንም ርዕስ ስሰጠው “ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ!” የማለቱን የጭቆና ቀንበር በወዶ ገብነት የሚጫኑ የሥልጡኑ ዘመን ቆሞ ቀሮችን ማሰቤ አልቀረም፡፡ ብዙዎቹ የዚህ እሳቤ ተጋሪዎች ከዴሞክራሲያዊ እሴቶች ጋር ያላቸው ፀብ ላይ በአመክንዮ ያልታገዘና በምልከታ ችግር የሚሰቃይ ስሁት የአገር ወዳድነት (Patriotism) ይስተዋላልና፡፡ሳያጠይቁ መቀበልን አልወደውም፡፡ በስራ ቀናት ሳይቀር ህዝባዊ አደባባዮችንና አማራጭ ያልተበጀላቸውን መንገዶች እየዘጉ የሚደረጉ “የድጋፍ ሠልፎችን” የማብዛቱ ነባር ባህል ቀየር ተደርጎበአጃቢነት ሲካተት ደግሞ መገረሜ በእጅጉ ይጨምራል፡፡

የኩነቱ መደጋገም ይልቁንም በከተማ አስተዳደሩ መስሪያ ቤቶችና በአስተዳደሩ የወረዳ አደረጃጀቶች በኩል አበል እየተሰፈረና ትራንስፖ

ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - ሶስት በሉ!)

Tigray warሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

August 5, 2021

“State sovereignty implies responsibility, and the primary responsibility for the protection of its people lies with the state itself. Where a population is suffering serious harm, as a result of internal war, insurgency, repression, or state failure, and the state in question is unwilling or unable to halt or avert it, the principle of non-intervention yields to the international responsibility to protect.”
(Report of the International Commission on Intervention and State Sovereignty, The Responsibility to Protect: Core Principle one)

ሉዓላዊነት የዜጎችን መሠረታዊ መብቶች እየጣሱ መደበቂያ ሊሆን እንደማይችል ለማሳየት

ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - ሁለት በሉ!)

Ethiopia at warሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

August 5, 2021

"...if Humanitarian Intervention is, indeed, an unacceptable assault on sovereignty, how should we respond to a Rwanda, to a Serbrenica - to gross and systematic violations of Human Rights that affect every precept of our common Humanity?..."
 (የኮፊ አናን ጥያቄ)

በቀደሙት ሁለት ክፍሎች “ታለ በአገር ሉዓላዊነት ስም!” በሚል ርዕስ የጀመርነው መጣጥፍ በቀናቶች ልዩነት በብዙ በሚቀያየረው ፖለቲካችን ሳቢያ እነሆ እንደቀጠለ አለ፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት እስከጥግ ድረስ ሄዶ ችግራችንን በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ ስንወተውት ቆይተናል፡፡ ግጭትና ጦርነት አይቀሬ ሲሆን ደግሞ ባልታጠቁና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት በሌላቸው ዜጎች ላይ የትኛውም አይነት ሰቆቃ እንዳይፈፀም ጮኸናል፡፡ ይህንን የጦርነት ህግ እየተላለፉ “ሉዓላዊነት” ላይ ሙጭጭ ማለት ከ

ኢትዮጵያ - “የሚወድቁ አገራት” ዝርዝር ውስጥ?!

Failed Statesሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

June 18, 2021

“It’s dangerous to be right when the Government is wrong.”
(ቮልቴር)

ከድህነቷ ጋር እየተንገታገተች ዘመናትን የፀናቸው አገራችን ኢትዮጵያ በየወቅቱ የጦርነትና ረኃብ ችግር ውስጥ ትገባለች፡፡ በየጊዜውም የህልውና ጥያቄዎችን ትጋፈጣለች፡፡ ችጋርና ድህነት በሰፊው ከተንሰራፋው ጦር ወዳድ ድንቁርናችን ጋር እየተሰናሰሉ የህልውና ውጥረታችን ደልዳላ መሠረትና ምቹ ቀጠና ሆነዋል፡፡ ከህልውና ትግል ለመውጣት ድንቁርናን እና ድህነትን ድል መንሳት አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታ ቢሆንም በየወቅቱ “የድህነት ዘበኛ” እየሆኑ ከአገረ መንግሥቷ መንበር ላይ የሚደላደሉ ግለሰቦችና ቡድኖች የቁስለቷ ድነት ላይ የሥልጣናቸውን ዕድሜ መራዘም ይመሰርታሉና ሰቆቃችን እንደቀጠለ አለን፡፡

ስለዚህም መንግሥታቱ በሽታችንን ሳይሆን የበሽታውን ምልክቶች በማስታገሻ ማቆየት እንጂ ማከሙን አይፈልጉትም፡፡ አገራችንን ኢትዮጵያን እጅግ አድርገን ለምንወድ ዜጎቿ ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ ልንንደረ

ታለ “በአገር ሉዓላዊነት” ስም! (ማጠናቀቂያ - አንድ በሉ!)

Failed Statesሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

June 18, 2021

“There are two kinds of Injustice: the first is found in those who do an injury; the second in those who fail to protect another from injury when they can.”
(Cicero, a Roman Jurist)

በቀደመውና “ታለ በሉዓላዊነት ስም!” የሚል ርዕስ በሰጠነው መጣጥፍ “ሉዓላዊነት” ምን ማለት እንደሆነና እንዳልሆነ ጭምር በማሳየት የአህጉረ አፍሪካችን ገዢዎች “በሉዓላዊነት ስም” ዜጎቻቸው ላይ እያደረሱት ያለውን ዘርፈ ብዙ በደል ለመመልከትና ዘመኑ እያለፈበት ስለመምጣቱም ተጠቋቁመናል፡፡ የሉዓላዊነትን ተራማጅ ፍቺ መነሻ በማድረግ አገራችንን ጨምሮ ወንበሯን ያገኙ አምባገነን መንግሥታትን ክሽፈት እየነቃቀስን ዛሬም እንቀጥላለን፡፡ በዚህም የ“ዓለማቀፉ ማህበረሰብ” ሚናና የጣልቃ-ገብነቱን ሁኔታ እናወሳሳለን - መልካም ንባብ!

“ሉዓ

ታለ “በሉዓላዊነት” ስም! (አንደኛው ክፍል)

Sovereigntyሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

June 18, 2021

“Sovereignty implies responsibility not just power!”
(Koffi Annan, 26 June 1998)

ደራሲና ሀያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ ከሚታወቅባቸው ስራዎች የቅርቦቹ ርዕስ “ታለ” የሰኘውን ገፀ-ባህሪ ስያሜ በማስቀደም ተፈታሹን ጭብጥ እያስከተለ “በፍቅር ስም” እንዲሁም ሐሰተኛውን “በእምነት ስም” በሚሉት ስራዎቹ እጅግ ተነባቢነትን አትርፏል፡፡ ዓለማየሁ በእውነትና “በአንድነት ስም” ወይም “በሉዓላዊነት ስም” እያለ ስለመቀጠል አለመቀጠሉ እርግጠኛ ባልሆንም እነዚህ ታለዎች የሰው ልጆች ህይወትን በየፈርጁ እንድንፈትሽ ገፍተውናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ትናንት በአገር አንድነት ስም ሲፈፀሙ የነበሩ ሰቆቃዎች በሙሉ ዛሬ በአገር ሉዓላዊነት ስም በእኔና በእናንተ ዘመን ሲፈፀሙ እየታደምን ነው፡፡

በተወሰነ መልኩም ቢሆን ዛሬም ስለመኖራቸው ታሪክ ምስክር ሆኗልና መፃህፍትን ጨምሮ በተለያዩ ሰነዶች ተጠርዞ እያነበ

አንዳንድ ነጥቦች - ስለሰሞንኛው ፖለቲካችን

Why we hate each otherሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

April 1, 2021

የዳያስፖራው ፖለቲካ - እንደግመል ሽንት?!

የኢትዮጵያች ፖለቲካ በብዙዎች እንደተተሰፈው ሳይሆን በጥቂት ሩቅ ተመልካቾች ቀድሞም እንደተፈራው “ከድጡ ወደማጡ” እየገባ ስለመሆኑ በድጋፍም ተቃውሞውም ጎራ የተሰለፉ ወገኖቻችን ልቦና የሚረዳው ነው፡፡ በኢትዮጵያ ለእኩልነትና ነፃነት፤ ለሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና ለአካታች አገራዊ አንድነት የተደረገውን ትግል በመጥለፍ “የለውጥ ኃይል” ነኝ ብሎ ብቅ ያለውና በኋላ ላይ በኮ/ል ዓብይ አህመድ አሊ የአምባገነንነት ፍላጎትና የንግሥና ምኞተ ፈቃድ ስር ያደረው ኢህአዴጋዊ ስብስብ ከአመራር ክህሎት እጦት ባልተናነሰ በሥልጣን ሽኩቻውና ባደረ የቂም መንገዱ አገራችንን ቁልቁል ይዟት መንደርደር ከጀመረ ሰንብቷል፡፡

አለመታደል ሆኖ ትናንት በዚያ ክፉ የሰቆቃ ዘመን ሽፋን ያልቀየረውን ኢህአዴግ በብርቱ ሲተቹና የተሻለ አገራዊ ፍቅርን ሲያሳዩ የነበሩ ሰዎች፤ ትናንት የበቁ፤ የነቁና ያወቁ ይመስሉ የነበሩ ሰዎች ይልቁንም በምሁሩ አካባቢ

ሃያ ሰባት ሲደመር - ስንት?!

Lidetu Ayalew bookሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

February 16, 2021

“በታሪክ የሚታወስ መሪ ለመሆን ከፈለግክ ራስህን ሁን - አታስመስል!”
(አቶ ልደቱ አያሌው - ለኮ/ል ዐቢይ አህመድ እንደፃፉላቸው)

የአቶ ልደቱ አያሌው ምህረቱን ፖለቲካዊ እስር መነሻ አድርገን “ሰቆቃወ ልደቱ በአዳማ በቢሾፍቱ!” በሚል ርዕስ በሶስት ክፍል ያስነበብናችሁ መጣጥፍ እንደተጠበቀ ሆኖ እዚሁ ገፃችን ላይ የተነበቡ ሌሎች ፅሁፎች የአቶ ልደቱንም ሆነ የሌሎች አያሌ ኢትዮጵያውያን የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን እስራት ስንቃወም፣ ሰብዓዊ መብታቸውን ያከበረ አያያዝ እንዲደረግላቸው ስንወተውት፣ አቅማችን በፈቀደ ሁሉ ኢ-ሰብዓዊነትንና ጭፍን ወገንተኝነትን ስንተች እንደቆየን ማሳያ ይሆናሉ ብለን እናምናለን፡፡

የነገ ከነገ ወዲያ መንገዳችንም ይኸው ነው፡፡ ለተበደሉትና ለተገፉት ሁሉ ድምፅ መሆንና ለሁሉም እኩል ተቆርቋሪነትን በማሳየት በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እግሩን እንዲተክል መትጋት፡፡ አቶ ልደቱ አያሌው የፍትህ ሥርዓቱን ተቋማዊ የውድቀት ልክ አስመልክተውንም

ልጄ በምን ምክኒያት እንደታሰረች ማወቅ አልቻልኩም - ወ/ሮ አዜብ መስፍን

ኢዜጋ ሪፖርተር

Semhal MelesDecember 22, 2020 (Ezega.com) --- የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሴት ልጅ ሰምሃል መለስ መቀሌ ከተማ ውስጥ ተይዛ እንደታሰረች እናቷ ወይዘሮ አዜብ መሰፍን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። ያም ሆኖ ልጃቸው ሰምሃል በምን ምክንያት ለእስር እንደተዳረገች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ወ/ሮ አዜብ ለቢቢሲ ተናገረው ወደ መቀለ የሄደችው ወታደራዊ ግጭቱ ከመጀመሩ በፊት እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል። አዲስ አበባ የሚገኙት ወ/ሮ አዜብ እንደሚሉት ከሆነ ሰምሃል ወደ መቀለ ያቀናችው በአባቷ የህይወት ታሪክ ላይ የተጻፈ መጽሐፍ ላይ ተንተርሶ የተዘጋጀን ቲያትር ለማስመረቅ ሲሆን አካሄዷም በርካታ ሰዎች ካሉበት ቡድን ጋር በመጣመር ነው ብለዋል። ሰምሃል "የፖለቲካ አቋም ሊኖራት ይችላል ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲ አመራርም፣ አባልም፣ ደጋፊም አልነበረችም" የሚሉት እናቷ ወ/ሮ አዜብ መስፍን የልጃቸው እስር ምክንያት ምን እንደሆነ እንደማያውቁ ነው ለቢቢሲ የተናገሩት። ወ/ሮ አዜብ ከቀናት በፊት ልጃቸው ሰምሃል እየተፈለገች እንደሆነ በመስማታቸው አርብ ዕለት ወደ መቀሌ ለመሄድ ፈልገው የነበረ ቢሆንም ፈቃድ ባለማግኘታቸው እ

ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማና የአቶ ስዩም መስፍን ቤተሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ኢዜጋ ሪፖርተር

AddisAlem Balema in CourtDecember 10, 2020 (Ezega.com) -- መንግሥት በበርካታ ከባድ ወንጀሎች ውስጥ ተሳትፈዋል በማለት ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳባቸው ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት  ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ ዛሬ ሐሙስ ታኅሳስ 01/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዚህም በትግራይ ክልል ውስጥ ከተካሄደው ወታደራዊ ግጭት በኋላ ፍርድ ቤት በመቅረብ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር አዲስአለም የመጀመሪያው ሆነዋል። በትግራይ ክልልም ሆነ በፌደራል መንግሥት ደረጃ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉትን የአዲስዓለም ባሌማን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። ከአንድ ወር በፊት በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የእስር ትዕዛዝ ከወጣባቸው የህወሓት አመራሮች መካከል አንዱ የነበሩት አዲስዓለም በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት። ፖሊስ ሰውዬውን የጠረጠረበትን የወንጀል ዝርዝር ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈ

የሁለት “ጁንታዎች” ወግ - የስግብግቡ እና የግብስብሱ!

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

PP-TPLFDecember 8, 2020

“ከእናንተ ኃጥያት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት!”
(ቅዱስ መፅሃፍ)

ከሳምንት በፊት “የሁለት “ጁንታዎች” ወግ” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ አስነብበናችሁ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ፅሁፍ ከተነበበ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንዱ በትግራይ ክልል ሌላው በፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ስርና በሌሎች ክልሎች ታጅቦ ያለውን ጁንታ የበለጠ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች መፈጠራቸውን በማስተዋሌ በዚሁ ርዕስና ሁለቱን በስግብግብ እና በግብስብስ ባህሪያቸው ነጣጥዬ እንዳሳያችሁ ምክንያት ሆኖኛል፡፡ ይልቁንም ሁለቱም አካላት በጠቢቡ “ቢገድሉት ቢገድሉት የማያልቅ” የሚል ትርጓሜ ለተሰጠው ለሰፊው ህዝብ ሠላምና የመንግሥትም ቀዳሚው ኃላፊነት የሆነውን የዜጎች ደህንነት ማስጠበቁ ላይ ከመጨነቅ ይልቅ ስለሥልጣን ያላቸው ቅጥ ያጣ ቀናዒነትን እንመለከታለን - መልካም ንባብ፡፡

ስግብግቡ - የህወኃት ጁንታ!

የህዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወኃት) በሌላ

የሁለት “ጁንታዎች” ወግ!

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

Ethnic-war-EthiopiaNovember 17, 2020 (Ezega.com) -- ኢትዮጵያን የዘር ሐረግ እየቆጠረ ለረጅም ጊዜ ከተንፈላሰሰባት የዘውዳዊ ሥርዓት ወደ ወታደራዊው የጁንታ አገዛዝ ትሸጋገር በነበረችበት ወቅት ላይ ነበር የኤርትራና የትግራይ በረሃዎችን መነሻቸው ያደረጉና ሥርዓታቱ ያነበሩት ዘርፈ ብዙ ጭቆናዎች ላይ ያበዩ የነፃነት ሸማቂዎች የመጀመሪያዋን የዓመፃ ጥይት ያጮሁት፡፡ እነሆ ያ የበረሃ ትግል የወቅቱን ወታደራዊ ጁንታ ገርስሶና በመሃል አገር ከቤተ-መንግሥት ደጃፍ አድርሶ የያኔዎቹን አማፂዎች በህጋዊ የፖለቲካ ድርጅትነት አስመዘገበ፡፡ የመንግሥትነት በትረ ሥልጣንንም አስቀበለ፡፡

ምንም እንኳን ሥልጣኑ የተገኘው በወታደራዊ ድል ቢሆንም የ“ጁንታ”ነት ስያሜውን ለማስቀየርና ቅቡልነትን ለመቀዳጀት የይስሙላ ምርጫዎች ተካሂደውም ፍፃሜውን ሳያሳምሩ ቀሩ፡፡ ትግሉ በመረብ ምላሸዋ አገረ ኤርትራ “ህግደፍ” የተባለ የአንድ ፖለቲካ ማህበርን ይልቁንም የአንድን ግለሰብ የፈላጭ ቆራጭነት ሥርዓት ሲያዋልድ በኢትዮጵያችን ደግሞ የከሸፈ ዴሞክራሲያዊና ፌዴራላዊ አስ

ከሰልፉ ክልከላ ማግስት የታወጀው - የወገን ጦርነት!

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

Ethnic-war-EthiopiaNovember 17, 2020 (Ezega.com) -- “ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሳሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ ሠላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጪ የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሠላማዊ ሰልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በህዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሄድ ላይ ያለ ስብሰባ ወይም ሠላማዊ ሰልፍ ሠላምን፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶችንና የህዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብነት ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ፡፡”
(የኢፌዲሪ ህገ-መንግሥት አንቀፅ-30)

ስለ መብቱ!

በኢትዮጵያ ህገ-መንግሥት ውስጥ መብቶች በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ ክፍፍል ውስጥ መውደቃቸውን፣ በተለየ ሁኔታ ደግሞ የሃሳብና ንግግር ነፃነትም ሆነ የዚሁ መብት ተቀፅላ የሆነውንና ይህንኑ መብት የሚከተለውን የመሰብሰብ፣ በሰላማዊ መልኩ ሃሳብንና ተቃውሞን የመግለፅ መብትም ከአነጋጋሪዎቹ ምድብተኖች ውስጥ ሆኗል፡፡ አቤት-ኡኡታዎችንም ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል

በመቀሌና በአዲግራት ሰላማዊ ዜጎች በአውሮፕላን ድብደባ ተገድለዋል - ደብረ ጺዮን ገ/ሚካኤል

ኢዜጋ ሪፖርተር

Ethiopia-Fighter-JetsNovember 12, 2020 (Ezega.com) -- የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረ ጺዮን ገ/ሚካኤል በመንግስት ተዋጊ አውሮፕላኖች ጥቃት በክልሉ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ ለሮይተርስ ተናገሩ፡፡ ርእሰ መስተዳደሩ በስልክና በአጭር የስልክ ጽሁፍ መልእክት ከሮይተርስ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ እንዳሉት ሰላማዊ ሰዎቹ በአየር ጥቃት የተገደሉት በተለይ በአዲግራት እና በርእሰ መዲናዋ መቀሌ ከተሞች ነው። ደብረጺዮን ጥቃቱ የተፈጸመው መቼ ነው? እና ስንት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ? የሚል ጥያቄ ቅርቦላቸው ዝርዝሩን መናገር አልፍልግም ማለታቸው ተዘግቧል። ርእሰ መስተዳድሩ ለክሱ ማስረጃ አላቀረቡም ያለው ሮይተርስ ጉዳዩን ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አለመቻሉንም አስታውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአየር ጥቃቶቹ የተመረጡ የህወሃት የጦር ሰፈሮች ላይ ብቻ እየተፈጸሙ ነው ማለታቸውን ያስታወሰው ዘገባው ከትግራይ ክልል በኩል የቀረበውን ክስ ከመንግስት በኩል ለማጣራት ሞክሮ እንዳልተሳካለት አስነብቧል። በተጨማሪም ደብረ ጺዮን በመንግስት በኩል የቀረበው ውንጀላ ሀሰት ነው ራሳችን ከጥቃት ተከላከልን እንጂ

ፌደራል ፖሊስ ለበርካታ የህወሃት ሲቪልና ወታደራዊ አመራሮችና የእስር ማዘዣ አወጣ

ኢዜጋ ሪፖርተር

November 12, 2020 (Ezega.com) -- የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን "የአገር ክህደት ወንጀል በፈፀሙ የጁንታው ሕወሓት ቡድን አባላት" ላይ የፍርድ ቤት የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው አስታወቀ። የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤልን ጨምሮ በ64 የፓርቲው አባላት ላይ የእስር ማዘዣ የወጣባቸው "በትግራይ ክልል በሚገኘው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀምና ከኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ፀረ-ሰላም ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ከተለያዩ ክልሎች አገርን የማፍረስ ተልዕኮ ያለቸውን ኃይሎች በመመልመል ትግራይ ክልል ድረስ በመውሰድ ለእኩይ ተልዕኮቸው ስኬት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ብሄርን ከብሄር በማጋጨት እና በሃይማኖት ሽፋን ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ በርካታ ንፅሁን ዜጎች እንዲገደሉ፣ በአካልና በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት እንዲደርስ በማድረጋቸው በፈጸሙት ከባድ የአገር ክህደት ወንጀል ምክኒያት መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግላጫ አስታውቋል። ከእነ

ህወሃት በማይካድራ በንፁኃን ዜጎች ላይ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ፈፀሟል - ደመቀ መኮንን

ኢዜጋ ሪፖርተር

Demeke-MekonnenNovember 11, 2020 (Ezega.com) -- በትግራይ ክልል ማይካድራ አካባቢ "በንፁኃን ዜጎቻችን ላይ የደረሰው እጅግ ልብ ሰባሪ፣ ኢሰብዓዊ እና ፍፁም አሳዛኝ ዘር-ተኮር ጭፍጨፋ በከሃዲው ቡድን አስተባባሪነት የተፈፀመ ይቅር የማይባል ወንጀል ነው" ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡ አቶ ደመቀ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት "ይህ ጭፍጨፋ እጅግ ሰው መሆንን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ዘግናኝ ድርጊት ነው።" አክለውም በምድር ላይ ያሉ የመጨረሻ የክፋት መገለጫዎችን ከመፈፀም ወደ ኋላ የማይመለሰው ይህ "ከሃዲ ቡድን በተለያዩ ክልሎች ፅንፈኞች እና አሸባሪዎችን እያስተባበረ ስምሪት እየሰጠ እና በፋይናንስ እየደገፈ በማንነት ላይ ያነጣጠረ ጭፍጨፋ መፈፀሙን ቀጥሎበታል" ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ከሃዲው ቡድን ከቀናት በፊት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታችን አባላት ላይ የፈፀመው አሳዛኝ ጭፍጨፋ ሳይበቃው አሁንም በንፁኃን ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ ገፍቶበታል ይህን እኩ

12345678910...

Archived News

No News to show