አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - ህብረተሰብ

ከዓድዋ እስከ ማይጨው… ከካራማራ እስከ ባድመ!

Adwa victory 1896ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

March 8, 2021

“We sleep peaceably in our beds at night only because rough men stand ready to do violence in our behalf!”
(ሰር ዊንስተን ቸርችል)
“ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!”
(ቀኝጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ)

ወግ መያዥያ…

ይህ ያለንበት ወር ከግንቦት ሲለጥቅ በኢትዮጵያችን በርካታ ሁነቶች የተስተናገዱበት ወር ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ተርፎ ለመላው አፍሪካውያንና ይልቁንም ለጥቁሮች ሁሉ የነፃነት ምልክትና ጭቆናን ያለመሸከም ትዕምርት ሆኗል፡፡ ድሉን ድህነታችን ላይ መድገም ቢያቅተንም አንገታችንን በእኩልነት ቀና አድርገን እንድንሄድ ያስቻለ ታሪክም ተከትቦበታል፡፡ ስለዚህም ብዙ ክብርና ምስጋና ስለነፃነታቸውና ነፃነታችን፤ ስለአገራቸውና አገራችን ሲሉ ለተዋደቁ ሁሉ ይሁንና “የድል በዓል!” እንጂ ከቅኝ ግዛት እንደተላቀቁ ወገኖቻችን የምንዘክረውና &l

ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!! (ወግ መቋጫ ሶስት - ስላቀ ምግብ ወልባስ!)

No luckሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

February 4, 2021

“ሀብታሞች ለስጋቸው ሆድ ሲፈልጉ
ድሆች ደግሞ ለሆዳቸው ስጋ ይፈልጋሉ!”
(የሕይወት ተቃርኖ)

“ሱፉን ግጥም አርጎ ተከርክሞ ፀጉሩን
መልዓክ መስሎ ታየኝ ወይ ያለው ማማሩ!”
(አስቴር አወቀ - በህዝብኛ)

አገርህ በንዋዩ በኩል ባትታደልም የበዓላት ሀብታም ነችና በቀደመው ፅሁፌ በተሳልቆ ውኃ ከነቋቆርኩህ በኋላ ተጣፍተን ከረምን፡፡ እንደምን አለህልኝ ወዳጄ ልቤ?! በዓላትን መለዮዋ ባደረገች ቺስታ አገር ላይ በዓሉስ እንዴት አለፈልህ ይሆን?! ያው የገናን ቅንጥብጣቢ ለጥምቀት ከሚያሻግሩት እንጂ ጥምቀትንም ራሱን የቻለ በዓል ከሚያደርጉት ወገን አይደለህም ብዬ ነው…. አልሞላ ያለ ኑሮህስ እንዴት ይዞሃል…?! ለነገሩ የድኃ ነገር ሆኖ ጠግባችሁ የበላችሁና ከርሳችሁ የሞላ ቀን የዓመት ርኃባችሁን ትረሳላችሁና አይዞን! “ያልተፈተነ አያልፍም!” ነው ነገሩ፡፡

በቀደመው ክፍል “ድኃ አይጣላ ከውኃ!” ይሉትን በ

ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!

Poverty-Ethiopiaዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
(ወግ መቋጫ ሁለት - ስላቀ ኑሮ!)

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

January 11, 2021

“I am neither an Optimist nor a Pessimist. But a Possibilist.”
(Hans Rosling)

አገርህ እንዲህ እንደዛሬው የጠቢብ እጥረት ሳያጋጥማት በፊት እንደሳቅ ንጉሡ ቻርሊ ቻፕሊን ሁሉ ድህነቱንና ድህነትህን በምሬት ሳቅ የሚያዋዛልህ ተስፋዬ ካሳ የሚባል ሰው ነበረ… ይህ ቀልዱ ብቻ ሳይሆን ድምፁም ያማረለት ሰው በአንድ የበዓል ጨዋታው ላይ ህፃን ልጅ “እማዬ ፆም ሲፈታ….?!” ብሎ ድኃ እናቱን ይጠይቅና የእናትዬውን ምላሽም ያቀብለናል፡-

“ልጄ! ፆም ሲፈታማ ሌላ ፆም እንይዛለና!”

እነሆ…. አንተም ዕድለ ቢሱ ወዳጄ ፆም ተፈታልህና ሌላ ፆም ይዘሃል... በቀደሙት ክፍሎች ይልቁንም ድህነትን ከፍቅርና ጦርነት ጋር እያሰናሰልን በተሳለቅንበት ክፍ

ዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!

Farmer-Ethiopiaዕድል ከሌለህ…. ድኃ ትሆናለህ!!!
(ወግ መቋጫ አንድ - ስላቀ ፍቅር ወጦርነት!)

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

December 31, 2020

“ድህነት በመስኮት ሲገባ ፍቅር በበር ይወጣል!”
(አገራዊ ብሂል)

“የድሃ ልጅ ነው እየታፈሰ ወደጦርነት የሚጋዘው!”
(የኢትዮጵያ መሪዎች)

ይህንን ፅሁፍ ስንጀምረው በገንዘብ ኖቶች ቅያሪ መነሻነት ነበርና ርዕሰ ጉዳዩ “የገንዘብ ኖቶች ወግ” ቢሆንም ብዙ ነገሮችን ነካክቶ እኔም ፅፌው እርስዎም አንበብውታል…. ማለቴ አንተ ዕድለ ቢሱ ድኃ አንብበኸዋል፡፡ በቀጠሯችን መሠረት እነሆ ፅሁፉ መቋጫ ሊያገኝ ግድ ነውና ፍቅርንና የእርሱም ተቃራኒ የሆነውን ጦርነትን ነካክተን ከድህነት ልናሰናብትዎ ባንችልም ከነድህነትዎ እንሰናበትኋለን…! ድህነትን በደንብ አውቆና ተዋውቆት ያለፈው ሞዛቂ ኃ/ኢየሱስ ፈይሣ “ፍቅር” ይሉት ማራኪና አጓጊ ነገር ላንተ ብጤው ድኃ “ዋጋው

በመተከል በተፈፀመ ዘር-ተኮር ጥቃት ከ90 በላይ ዜጎች ተገደሉ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Metekel Benishangul GumuzDecember 23, 2020 (Ezega.com) -- በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ በተባለ ቀበሌ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ከ90 በላይ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የጀርመን ድምጽ ራዲዮ፣ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅትና ቢቢሲ ከአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አገኘነው ባሉት መረጃ መሰረት ዜጎቹ የተገደሉት ከባድ መሳሪያ ጭምር በታጠቁ ተዋጊዎች ሲሆን በቀስትና በሌሎች መሳሪያዎች የተገደሉና የቆሰሉ በርካቶች መሆናቸውንም አስነብበዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው አንድ የቡለን ወረዳ ነዋሪ ጥቃቱ ትናንት ሌሊት 11 ሰዓት አካባቢ መፈፀም እንደጀመረ ገልፀው እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ቀጥሎ ነበር ብለዋል። በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች ለቅሶ ላይ መሆናቸውን የገለፁት እኝህ ነዋሪ "እስካሁን 100 አስክሬኖች ተገኝተዋል የጠፉ አስክሬኖችም አሉ ወደ ቡለንም 70 አስክሬኖች መጥተው ተመልክቻለሁ" ማለታቸው ተዘግቧል። በጥቃቱ የጓደኛቸው አባት መገደላቸውን የተናገሩት ነዋሪው "ቤት እየጠበቀ እያለ ነው ተኩሰው የገደሉት እርሱ መሳሪያ ቢኖረው

በዓለም የፍልስፍና ቀን “ፍልስፍናችን” ቢፈተሽስ? (ማጠናቀቂያ)

Ethiopian Philosophyሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

December 20, 2020

“እንደኔ እምነት የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ስድስት ኪሎ ሲሞት
አምስት ኪሎም መጠውለጉ አይቀሬ ነው፡፡”
(ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ)

ጋሽ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) የኔ ዘመን ኢትዮጵያውያን ስለፍልስፍና ያላቸውን አመለካከት እንዲያጠይቁ ካደረጉ ጉምቱ የአደባባይ ምሁራን ውስጥ አንዱና በዚህ ዘርፍ ላይም ቀዳሚው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በተከታታይ ቅፆች “ፍልስምና” በሚል ርዕስ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን ምልከታዎች ጨምቆ ከሰጠን ጋዜጠኛና ደራሲ ቴዎድሮስ ተክለ አረጋይ በኩል ተነባቢ በነበረችው “አዲስ ጉዳይ” መፅሄት ስለፍልስናና በቀደመው ክፍል ስላነሳነው 70/30 የትምህርት ሥርዓተ ፖሊሲያችን ተገቢነት ዙሪያ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ነበር፡፡ ለጥያቄዎቹ ከሰጧቸው ምላሾች ውስጥ ይህንን መግቢያ ላደርገው ፈቀድኩ፡፡

ጋሽ ዳኛቸው ጥያቄውን ሲመልሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው የስድስት ኪሎ ግቢ ውስጥ የሚሰጡት የማህበራዊና የሥነ-ሰብዕ (Social Scie

ቀኑን ወይስ “ሰብዓዊ መብቶችን” አክብሮ ማስከበር?

Respect human rightsሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)
December 10, 2020

“How can you thank a man for giving you
what’s already yours? How then can you thank him
for giving you only part of what is yours?”
(ማልኮልም ኤክስ)

ዓመታትን ወደኃላ….!

እነሆ አስር ዓመታት ሊደፍኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በተቀናጀ መልኩ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለመጠበቅ ያስችለኛል፤ ለጥበቃቸውም ስልትና አቅጣጫን ለመንደፍ ያዘኛል ያለችውን ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ማስፈፀሚያ የድርጊት መርሐ-ግብር (National Human Rights Action Plan 2005-2007) ዝርዝር ጉዳዮችን እንደያዘ ተረቅቀው በሚኒስትሮች ምክር ቤትና የህዝብ መሆን ሳይችል ዘመኑን በፈጀው የተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ፡፡ ሆኖም ተስፋ የተጣለባቸው የሲቪልና ፖለቲካ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚ እንዲሁም ባህላዊ መብቶች ተግባራዊ አፈፃፀምና አስተምህሮ ጉዳይ ባለበት

በዓለም የፍልስፍና ቀን “ፍልስፍናችን” ቢፈተሽስ?! (ቀዳሚው ክፍል)

world-science-day“I Think! Therefor I am”
(Rene Descartes)

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

November 24, 2020

ጋዜጠኛና ደራሲ ኃ/ጊዮርጊስ ማሞ (ጲላጦስ) ለትውልዴ ወጣቶች ሩቅ ይመስል የነበረውን ፍልስፍና ቀረብና ቀለል አድርጎ “ጥበብ” በሚል ርዕስ ንዑሳን አርዕስቶችን እያስከተለ ያስተዋወቀ ባለውለታችን ነው፡፡ ከመፃህፍቱ ቀደም ብሎም ቢሆን እንደ ኔሽን እና ዜን በመሳሰሉት የህትመት ብዙኃን መገናኛዎች በኩል ብዙ የፃፈ ሲሆን አሁንም ፍትህ በተሰኘችው ተነባቢ መፅሄት ላይ ይህንኑ አምድ ይዟል፡፡ በአንድ ወቅት የህንዳዊውን አሰላሳይ ቻንድራ ሞሃን (ኦሾ) መፃህፍት ማንበብ “የአዕምሮ ጤናን ያቃውሳል!” በሚል ስሁት እሳቤ እነዚህ መፃህፍትም አብረው ተመድበዋልና በወቅቱ በአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቃለ-ጭውውት አድርጎ ነበር፡፡

ኃ/ጊዮርጊስ እውነት እንደዚያ አይነት ነገር ተከስቶ ወጣቶች መስመር ስተው ከሆነ እጅግ አድርጎ እንደሚያዝን ሲገልፅ “ፍልስፍና” ግን ለአዕምሮ ጤና መቃወስ

በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ የተዘጋጁ 14 የአልሸባብ እና የአይ ኤስ አባላት ተያዙ

ኢዜጋ ሪፖርተር

ISIS-EthiopiaNovember 14, 2020 (Ezega.com) -- በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ 14የአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ። አልሸባብ እና አይ ኤስ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት በመፈፀም "በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ለማድረስ እንዲሁም የሀገራችንን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ" ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን 14 የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል ተብሏል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው አባላትን በመመለመል፣ የሽብር እቅድ በማውጣትና ኢላማዎችን በመለየት እንዲሁም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጥቃቶችን ለመፈጸም ስምሪት ወስደው እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የነበሩት ተጠርጣሪ የሽብር ቡድኖቹ አባላት በዛሬው እለት እንዲያዙ ተደርጓል። ይሄንን የጥፋት ተግባር ለመፈፀም ሀገር ውስጥ የገባው አንደኛው

በአዲስ አበባ በዜጎችና መሰረተ ልማቶች ላይ የፈንጂ ጥቃት ለመፈጸም የተንቀሳቀሰ ቡድን ተያዘ - ብሄራዊ መረጃና ደህንነት

ኢዜጋ ሪፖርተር

NISS-EthiopiaNovember 6, 2020 (Ezega.com) -- ከህወሃት ተልእኮ ተሰጥቷቸው በአዲስ አበባ በሚኖሩ ንጹሃን ዜጎችና መሰረተ ልማቶች ላይ በተለይም በለገዳዲና ገፈርሳ የሚገኙ የውሃ ግድቦች እንዲሁም በለገጣፎ የሚያልፍ ከፍተኛ የውሃ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የፈንጂ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት ሲያደርጉ የቆዩ የኦነግ ሸኔ አባላት ለጥፋት ተልዕኳቸው ካዘጋጇቸው ተቀጣጣይ ፈንጂዎችና ሌሎች ቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብሄራዊ መረጀና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡ የጥፋት ተልዕኮቸው "ባይከሽፍ ኖሮ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ሰብኣዊ ቀውስ" ያስከትል እንደነበር በመግለጫው ያስታወቀው ተቋሙ የጥፋት ተልእኳቸውን ሳይፈጽሙ የተያዙት ቶሎሳ አብዲሳ፣ ደጀኔ ፍቃዱ፣ ሀብታሙ፣ ተስፋየ መርጋ፤ ንጉሴ አሰፋና ፈልማት ታከለ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን አመልክቷል፡፡ በሌላም በኩል ጋዲሳ ሞሲሳ ባይሳ የተባለው የጥፋት ቡድኑ አባልና ግብርአበሮቹ ደግሞ በአዲስ አበባ በንጹሃን ዜጎች ላይ የቦንብ ጥቃት ለመፈጸም ካዘጋጇቸው ቦንቦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስተውቋል፡፡<

ጠቅላይ ሚንስትሩ በጅምላ ግድያው ዙሪያ በፓርላማ ተገኝተው ማብራሪያ እንዲሰጡ ም/ቤቱ አሳሳበ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Parliament-EthiopiaNovember 3, 2020 (Ezega.com) -- የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 5ኛ ዘመን 6ኛ አመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ለማካሄድ ነበር በዛሬው እለት የተሰየመው ያም ሆኖ ም/ቤቱ ለዛሬ እንዲወያይባቸው በአፈ ጉባኤው በኩል የቀረቡለትን አጀንዳዎች በተመለከተ ዜጎች ማንነታቸውን መሰረት ባደረገ ጥቃት እየተጨፈጨፉ በሌላ አጀንዳ ላይ አንወያይም በማለት አቋም የያዙ አባላት ምሬት አዘል ተቃውሞ ያቀረቡበት ሆኗል፡፡ በእምቢተኝነታቸው በፅናትም ለዕለቱ በተያዘውን አጀንዳ ዙሪያ ውይይት ከመጀመራቸው በፊት ከ2 ሰዓት በላይ ስለዚሁ ጉዳይ በእንባ ጭምር ሀሳባቸውን በስሜት ሲገልጹ በሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጭምር ታይተዋል፡፡ "በመግለጫ ጋጋታ መፍትሄ አይመጣም፣ ድርጊትና እርምጃ ያስፈልጋል፣ ዛሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እየተጨፈጨፉ ዝም ካልን ነገ በሺዎች የሚቆጠሩ እንዲጨፈጨፉ መፍቀድ ነው" ሲሉ የሞገቱት አባላቱ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በተፈጸመው "አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ዙሪያ" ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ብሔራዊ የመረጃ ደህንነት፣ ሰላም

በአፋር ክልል 10 ሰዎች 'በአሸባሪዎች' ተገደሉ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Afar-EthiopiaOctober 28, 2020 (Ezega.com) -- ባለፉት ሁለት ቀናት በአፋር ክልል  ገዳማይቱ በመባል በሚታወቀው አካባቢና በክልሉ ዞን ሶስት በሚገኘው ገለአሎ ወረዳ ሰርከሞና ቴሌ ቀበሌ መንደር ውስጥ 10 ንጹሃን ዜጎች በአሸባሪዎች መገደላቸውን የአፋር ክልል ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አህመድ ካሎይታ አስታውቀዋል። ሃላፊው ለቢቢሲ እንደተናገሩት በተለይ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሁኔታ ለመቆጣጠር የተሰማሩ አቶ ሙላት ፀጋዩ እና አቶ አበባው አያልነህ የተባሉ ሁለት የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በትምህርት ቤት ውስጥ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት በገለአሎ ወረዳ ሰርከሞና ቴሌ ቀበሌ መንደር ውስጥ በሚገኙ የአርብቶ አደር ማሕበረሰብ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ስምንት ሰዎች "አሸባሪ በሚባሉ ሃይሎች ተገድለዋል" ሲሉ አቶ አህመድ አረጋግጠዋል። 'የሽብር ጥቃቱ' በሴቶችና ህፃናት ላይ እንዳነጣጠረ የጠቀሱት የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ በክልሉ የተለያዩ ግጭቶች የሚያ

በደቡብ ክልል 12 አርሶ አደሮች በታጣቂዎች ተገደሉ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Gura-Ferda-EthiopiaOctober 21, 2020 (Ezega.com) -- በደቡብ ክልል ውስጥ በሚገኘው ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ "ማንነታቸው ያልታወቀ" የተባሉ ታጣቂዎች 1 ህጻንን ጨምሮ 12 ንጹሃን ዜጎችን በጥይት መግደላቸው ተሰማ። የወረዳው ባለስልጣናት ለጀርመን ድምጽ እንዳስታወቁት ታጣቂዎቹ ግድያውን የፈጸሙት ባለፈው ሰኞ ምሽት በወረዳው ውስጥ በሚገኘውና ለዩ ስሙ ሹቢ በተባለው የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። እንድ ባለስልጣናቱ መረጃ ከሆነ ታጣቂዎቹ በቀበሌው በሚገኙ መንደሮች ውስጥ ዘልቀው በመግባት በድንገት በከፈቱት የተኩስ እሩምታ አንድ ህጻንን ጨምሮ 12 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 5 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።  የጉራ ፈርዳ ወረዳ ፖሊስ ዋና አዛዥ ኢንስፔክተር በቀለ በየነ ለጣቢያው በሰጡት ቃልም ይሄንኑ አረጋግጠዋል። "ጥቃቱ የደረሰባቸው በሙሉ አርሶ አደሮች ናቸው ባልታሰበ ሰዓት ምሽት ላይ በየቤታቸው ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ነው የተገደሉት። አሁን የወረዳ፣ የክልል እና የፌዴራል የፀጥታ ሃላፊዎችና የሰራዊቱ አባላት በስፍራው ደርሰን አካባቢውን እያ

ሰቆቃወ ልደቱ - በአዳማ በቢሾፍቱ (ሶስት በሉ!)

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

Lidetu-CourtOctober 20, 2020

“የአቶ ልደቱ እስርና መንግስት የፍርድ ቤት ትዕዛዝን በተደጋጋሚ አለማክበርና መጣስ የፍትህ ሥርዓቱ አደጋ ላይ መውደቁን፣ የወይዘሮ መዓዛ ጥረት መክሸፉን፣ የሹሞቹ ባህሪ ዛሬም አለመቀየሩን፣ ፍትህ ዛሬም በጉልበተኞች ጫማ ስር መውደቋን የሚያሳይ መጥፎ ምልክት ነው። ከዚህ በኋላ ፀቡ ከአቶ ልደቱ ሳይሆን ከፍትህና ለፍትህ ከሚወግኑ ሁሉ ጋር ነው።”
(አቶ ያሬድ ኃ/ማርያም - የሠብዓዊ መብቶች ተሟጋች)

የደውሉ “ድምፅ” ለሁላችንም ነው!

በቀደሙት ሁለት ክፍሎች የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ብሔራዊ ምክር ቤት አባልና አመራር አባል ስለሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው ፍትህ ማጣትና ሰቆቃአንስተን መሰል የህገ-ወጥ አያያዝ ሰለባዎችን ጉዳይ ካወሳሳን በኋላ በተፈጠሩ ተያያዥ ጉዳዮች መግቢያዬን ላደርግና በዚህ ክፍልም ርዕሱን ልቋጨው ወደድኩ፡፡ ከነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በቀር ስለሁላችንም ነፃነትና የሰብዓዊ መብቶቻችን መከበር እንዲሁም ስለፍትህ ቆመናል ከሚ

የዜጎች አመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ 1 ሺህ ዶላር በላይ ደርሷል - ጠ/ሚ ዐብይ

ኢዜጋ ሪፖርተር

PM-Abiy-AhmedOctober 19, 2020 (Ezega.com) -- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ በዛሬው እለት ተካሂዷል። በስብሰባው ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። አነጋጋሪ ሆነው ከዋሉት የጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሾች መካከል የሀገሪቱን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሁኔታ በተመለከተ የቀረበው ይገኝበታል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በተጠናቀቀው የበጀት በኢትዮጵያ የ6 ነጥብ 1 በመቶ ኢኮኖሚያዊ እድገት መመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡ የታሰበውን ያህል ባይሆንም ከወቅታዊው የኮቪድ 19 ወረርሺኝ አንጻር በበጀት አመቱ ተስፋ ሰጭ የምጣኔ ሀብት እድገት መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ በመንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች ለእድገቱ አይነተኛ ሚና ነበራቸው ብለዋል፡፡ ያም ሆኖ የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ ከሳምንት በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ወቅት ሀገሪቱ ያስመዘገበችው እድገት 7 በመቶ ነው ብለው መናገራቸው ሲታሰብ የጠቅላይ ሚንስትሩ ማብራሪያ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።

ባለፈው በጀት አ

የቤንሻንጉሉን ተደጋጋሚ ግድያ በመምራት የተጠረጠሩ 504 ሰዎች ተያዙ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Benishangul-GumuzOctober 16, 2020 (Ezega.com) -- በቤንሻንጉል ክልል መተከል ዞን በርካታ ንፁኃን ዜጎች እንዲገደሉ በማስተባበርና በመምራት የተጠረጠሩ 504 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ገለጹ፡፡ የአማራና የቤንሻንጉል ክልሎች ርእሳነ መሥተዳድሮች አቶ ተመስገን ጥሩነህና አቶ አሻድሊ ሐሰን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በተገኙበት በክስተቱ ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም በተደጋጋሚ በክልሉ መተከል ዞን በንፁኃን ላይ በሚፈፀመው ጥቃት ውስጥ የህወሃት እጅ እንዳለበት ደርሰንበታል ብለዋል። "ለውጡን ተከትሎ ያኮረፉት እነዚህ አካላት ከሚፈጥሩት የፀረ ሰላም ኃይሎች እንቅስቃሴ" በተጨማሪ ከመሬት ይዞታ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውንም አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡ በተለይ አቶ አሻድሊ ሃሰን ህወሃት ይህን ድርጊት ለማስፈፀም ወጣቶችን በመመልመልና አንዳንድ በኢንቨስትመንት የገቡ ባለሀብቶችን በመጠቀም ችግሮቹ እንዲባባስ ሲሠራ ከርሟል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ የክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለ

የ“ሰንደቅ ዓላማ”ው ተወዛጋቢዎች

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

October 12, 2020 (Ezega.com)

Ethiopian-Flag“ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር
የመጀመሪያ ሰኞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡”
(የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ -ማሻሻያ)

መንደርደሪያ….

ባንዲራ (Bandiera) የሚለውን ቃል ባለማስተዋል ብንጠቀምበትም ቃሉን ጣሊያኖች ሰንደቅ ዓላማን ለመግለፅ የሚጠቀሙበት በመሆኑ ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ በያዙበት ወቅት ያስተዋወቁት በመሆኑ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የምንግባባው “ሰንደቅ ዓላማ” በሚለው ቃል ይሆናል፡፡ የሰንደቅ ዓላማው ጫፍ (ልሣን) የጦር ምልክት እንዲሆን የሚጠበቅበት፣ መጠሪያው “ሰንደቅ” እና “ዓላማ” ከሚሉት የሁለት ቃላት ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን ሰንደቅ ማለት “ምሰሶ ወይም ቋሚ ዘንግ” “ዓላማ” ማለት ደግሞ ምልክት ወይም መለዮ እንደማለት ነው ይሉናል ፈታሄ ቃላቶቻችን፡፡

እንግዲህ የሁለቱ ቃላት ጥምረት ነው&

መስፍናዊው ስንብት!

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

Mesfin-Woldemariam-tributeOctober 5, 2020 (Ezega.com) -- በገፃችን ከስራዎቻቸው እየሰበዝን በአስረጅነት ስንጠቅስ የቀዳሚነቱን ቦታ የያዙት ጉምቱው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ናቸው፡፡ እኚህ አንጋፋ የአደባባይ ምሁርና አሰላሳይ በርካታ ወጣቶችን አስከትለዋልና ስለፖለቲካዊ ድፍረታቸው ያደንቋቸዋል፡፡ አደባባይ ለመውጣት ፍርሃት እጅና እግረ-ሙቅ የሆነባቸው የዕድሜና ዕውቀት ቀራቢዎቻቸው “ምሁራን” ደግሞ በአንድ ጎኑ ስለእርሳቸው ሲሰጉ በሌላው በኩል ደግሞ አድር ባይነትንና እበላ ባይነትን ስለሚጠየፈው ደፋር ብዕራቸው ለየኔታ መስፍን እጅ ይነሳሉ - ባርኔጣ ከፍ እያደረጉ፡፡

ዕድሜ ዘመናቸውን ሁሉ ስላመኑበት እውነት ሲሟገቱና ሲፅፉ፤ ኢትዮጵያዊነትን ከእምቢ ባይነት ጋር ሲያመዝኑና ብቻቸውን ብዙ ሆነው ሲደክሙ ኖረዋል፡፡ የያዝነውን “አዲስ ዓመት” ግባት ተከትሎ በመስከረም ጅማሮ ላይ “ተጠየቅ መስከረም!” ያሉትን ቆየት ያለ ግጥም በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አጋርተውት ነበር፡፡ በግጥሙ መግያ ስንኞች ላይ “ም

ዕድል ከሌለህ…..ድሃ ትሆናለህ!!! የገንዘብ ኖቶች ወግ - ስላቀ ህይወት

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

October 5, 2020
 
Ethiopian-New-Bank-Notes-“ከሀብታም ቤት ጥብስ፤ ከድሃ ቤት ጥቅስ አይጠፋም!”
(የታክሲው ጠቃሽ፤ ብሩክ)

“ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ!”
(አገራዊ ብሂል)

“Poverty is like punishment for a crime you didn’t commit.”
(Eli Khamarov, Author)

እንደምን ሰንብተሃል ዕድለ ቢሱ ወዳጄ?….በዓሉንስ እንዴት አሳለፍከው ይሆን?! ያ ጉድ የማያልቅበት ተስፋዬ ካሳ ድሆች ፆም ሲፈታ “ሌላ ፆም ከመያዝ በቀር” በዓልን እንደማይዙ ሲቀልድ ሰምተሃልና ይቅር…..መቅድሙን በተከተለው ስላቅ መሰንበቻችንን “በደሳሳ ጎጆ እምኖር የሞራል ባለፀጋ ነኝ!” ሲል ነገሩን በገደለው ገጣሚ ነበር የተሰናበትኩህ፡፡ ያው ድሃ ብሆንም ከነሞራሌ ነኝና ያለሁት “አለሁ አልሞትኩም!&r

በኢሬቻ በአል ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በህወሓት የተደራጀ ቡድን መያዙን ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አስታወቀ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Irreecha-Celebration-TPLFOctober 1, 2020 (Ezega.com) -- በቢሾፍቱና በአዲስ አበባ ከተማ ከሚከበረው የኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃቶች ለመፈጸም፣ አመጽ ለማቀጣጠልና ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ከትግራይ ክልል የጸጥታ ቢሮ ሃላፊና ከህወሓት የጥፋት ቡድኖች ተልዕኮ ተቀብሎ በህቡዕ ሲያስተባብርና ሲመራ የነበረ የኦነግ ሸኔ ቡድን ከእነ ግብረአበሮቹ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ማድረጉን የበሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታውቋል።አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ማምሻውን ለመገናኛ ብዙሃን ባሰራጨው መግለጫ ላይ እንደገለጸው ከኢሬቻ በዓል ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ፣ በቢሾፍቱና በሌሎቹም የአገሪቱ አካባቢዎች በጦር መሳሪያ የተደገፈ የሽብር ጥቃት፣ አመጽ ፣ ግጭትና ትርምስ ለመፍጠር ተልዕኮ ለተሰጠው በህቡዕ የተደራጀ አንድ ታጣቂ ቡድን የሚውል 10 ክላሺንኮቭ የጦር መሳሪያ ከ 280 ጥይቶች ጋር ከመቀሌ ወደ ባቲ ሲጓዝ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም ቀን በ

12345678910...

Archived News

No News to show