አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - አፍሪቃ

ሱዳን በድንበር አካባቢ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ባስቸኳይ እንድታቆም ኢትዮጵያ አሳሰበች

ኢዜጋ ሪፖርተር

Ethiopia Sudan conflictDecember 23, 2020 (Ezega.com) -- በኢትዮጵያና ሱዳን የጋራ ድንበር አካባቢ በሱዳን በኩል እየተደረጉ ያሉ አዳዲስ ለውጦች እና እንቅስቃሴዎች የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ በመሆናቸው በአስቸኳይ እንዲቆሙ ኢትዮጵያ አሳሰበች። ማሳሰቢያው የተሰጠው በሱዳን ካርቱም ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳዮች ከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ውይይት በተጠናቀቀበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅትም ሁለቱ ወገኖች በጋራ የድንበር አካባቢ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሃሳብ የተለዋወጡ መሆኑን የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ በጋራ ድንበር አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለውጦች እና እንቅስቃሴዎች የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ መሆናቸው በመድረኩ ላይ ተነስቷል ብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ድርጊቶቹ መሬት ላይ ያለውን እውነታ የሚለውጡ በመሆናቸው በአስቸኳይ እንዲቆሙና ወደቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ ኢትዮጵያ አሳስባለች ተብሏል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ በገበሬዎች እና ባለሃብቶች ንብረት ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጉ

በኢትዮጵያና ሱዳን ሃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Ethiopia Sudan conflictDecember 20, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ ሚሊሻና ወታደሮች ወደ ሱዳን ግዛት ገብተው ጥቃት ፈጽመዋል ሲል የሱዳን መንግስት ጦር ከሰሰ። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክም ከሀገሪቱ ጦር ጋር ተመሳሳይነት ያለው መግለጫ በማውጣት በጥቃቱ የሰዎች ህይወት ማለፉን እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች በሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብደላ ሃምዶክ በመግለጫቸው "ሀገራችን ምስራቃዊ ድንበሯን አቋርጠው የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ተቀብላለች ህዝባችንም በአስቸጋሪ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም በሚታወቅ ልግስናው አስተናግዷቸዋል" ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ማክሰኞ ታህሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ የሱዳን ወታደሮች በ 'ጃባል አቡጢዩር' አካባቢ ቅኝት አድርገው ሲመለሱ "ወደ ሱዳን ግዛት ገብተው አድፍጠው በነበሩ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ሚሊሺያዎች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል" ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ፡፡ በዚህም ጥቃት የሰዎች ህይወት መጥፋት እና የንብረት ጉዳት መድረሱን ነው

አሜሪካ በትግራዩ ጦርነት የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፈዋል ብላ እንደምታምን ተነገረ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Eritrean-armyDecember 8, 2020 (Ezega.com) -- የኤርትራ ወታደሮች በፌደራል መንግስት እና በህወሃት ሃይሎች መካከል በተከሰተው ጦርነት ውስጥ ተሳትፈዋል ብላ አሜሪካ እንደምታስብ ሮይተርስ ከአንድ የአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣን እና ከ5 የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ዲፕሎማቶች ሰምቻለሁ በማለት ዘግቧል። ኤርትራ ጦሯን ስለማስገባቷ የአሜሪካ መንግሥት ግንዛቤ ያገኘው፣ ከሳተላይት ምስሎች፣ ከተጠለፉ የመልዕክት ልውውጦች እና ከትግራይ ክልል ከሚወጡ ሪፖርቶች እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል። ያም ሆኖ በጉዳዩ ላይ የአሜሪካ መንግሥት ድምዳሜ ላይ ስለመድረሱ እና አንዳች አቋም ስለመያዙ ግን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ማረጋገጫ አለመስጠቱን ዘገባው አመልክቷል። የኤርትራ ወታደሮች በዛላንበሳ፣ ራማ እና ባድመ ከተሞች በኩል እንደገቡ ከምንጮች መስማቱን የገለጠው ዜና ወኪሉ የወታደሮቹ ብዛት እና በጦርነቱ ስላላቸው ሚና በተመለከት መረጃ እንዳልተገኘ አክሏል። ብሉምበርግም ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ፣ የኤርትራ ወታደሮች መቀሌ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች መታየታቸውን ዘግቧል። የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግስታት ከህወሃት በኩል በተደጋጋሚ ሲቀርቡ የነበ

የኤርትራ ሰራዊት ድንበር ጥሶ በመግባት ወረራውን ተቀላቅሏል - ደብረፅዮን ገብረሚካኤል

ኢዜጋ ሪፖርተር

Isaias-AbiyNovember 11, 2020 (Ezega.com) -- ከተጀመረ 7ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የእርስበርስ ጦርነት ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኝ ተሰምቷል። የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሃይል በትግራይ 8 ግንባሮች ያሰማራ ሲሆን በዚህም በተለያየ አቅጣጫ ጥቃት እየፈጸመ መሆኑ ይታወቃል።ከዚህ ሌላ የኤርትራ ሰራዊትም ድንበር ጥሶ በመግባት መከላከያውን እያገዘ ነው ሲሉ  የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከሰዋል። "አምባገነኑ አብይ አሕመድ የትግራይን ህዝብ ለመጨፍለቅ የለኮሰውን ጦርነት ከባድ ኪሳራ ስላጋጠመውና እንደሚሸነፍ ስላወቀ አምሳያው ኢሳይያስን ድረስልኝ ብሏል እኛ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ስንገጥም ኢሳይያስ አብይን ለማዳን ከጀርባችን ውጊያ ጀምሯል" ያሉት ሊቀመንበሩ ያም ሆኖ "የትግራይን ህዝብ ለመጨፍለቅ ተግተልትለው የመጡትን ወራሪ ሃይሎች እስካሁን ከባድ ኪሳራ ተከናንበዋል አሳፋሪ ሽንፈትም እየደረሰባቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል። የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር የሆኑት ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሰጡት መግለጫ እንዳሉት "ኢሳይያስ አፈወርቂ ከአብይ አህመድ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት መንግሥትንና ህወሓትን እንዲያሸማግሉ ክራይስስ ግሩፕ ጠየቀ

ኢዜጋ ሪፖርተር

ICG-TigrayAugust 16, 2020 (Ezega.com) -- አለም አቀፉ የግጭቶች ቡድን (ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ) የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በገመገመበት ባለ 14 ገጽ ሰነድ ላይ በተለይ የትግራይንና የፌደራሉን መንግሥት ፍጥጫ ትኩረት ሰጥቶ ተንትኖታል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የሠላም ኖቤል ተሸላሚው ዐቢይ አሕመድ አስታራቂና የሚያቀራርቡ ንግግሮቻቸውን ወደ ተግባር እንዲለውጧቸው የጠየቀው ቡድኑ በመንግሥትና በህወሓት መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ የአፍሪካ ሕብረት ወይም የአፍሪካ መሪዎች በማሸማገሉ በኩል ተሳትፎ ሊያደርጉ ይችላሉ ብሏል። ከእዚህ በተጨማሪ ግን በተለይ የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ ሲልም ቡድኑ አክሏል። አለበለዚያ ግን ተስፋ የተጣለበት ፖለቲካዊ ሽግግር እንቅፋት ሊገጥመው ይችላል ሲል ክራይስስ ግሩፕ ስጋቱን አንጸባርቋል።

ሪፖርቱ የትግራይ ክልል ልሂቃን ክልላዊ ራስን የማስተዳደር መብት በክልልላችን ምርጫ ማካሄድ ሙሉ መብት ያጎናጽፈናል የሚል አቋም እንደያዙና የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ ሕገ መንግሥቱ ይህን እንደማይፈቅድ

ግብጽ በቀጠናው የጦር ሰፈር እንዳታቋቁም ኢትዮጵያ አስጠነቀቀች

ኢዜጋ ሪፖርተር

Egypt-militaryJuly 29, 2020 (Ezega.com) -- ግብጽ በምስራቅ አፍሪካ የጦር ሰፈር በማቋቋም የቀጠናውን ሰላም ለማደፍረስ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንድታቆም ኢትዮጵያ እንዳስጠነቀቀች ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል፡፡ ከ4 ቀናት በፊት ከፍተኛ ባለስልጣናትን የያዘ የግብጽ የልዑካን ቡድን ከሶማሌላንድ ግዛት አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ ጋራ በሀርጌሳ ተገናኝቶ መወያያቱ ይታወሳል፡፡ ዋናው የውይይቱ ማጠንጠኛም ግብጽ በራስ ገዟ አስተዳደር ክልል ውስጥ የጦር ሰፈር ለማቋቋም በምትችልበት ሁኔታ ዙሪያ እንደነበርም ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን የግብጽን እቅድ ተከትሎ ነው ማስጠንቀቂያውን ያወጣችው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለኔሽን እንደተናገሩት ምንም እንኳን ግብጽ እንደ አንድ ሉዐላዊ አገር ከየትኛውም የቀጠናው አገር ጋር ግንኙነት የመመስረት መብት ቢኖራትም ይሄንን ስታደርግ ግን ሌሎች አገራትን በሚጎዳ መልኩ መሆን የለበትም ያ ሳይሆን ቀርቶ የግብጽ ድርጊት ሌላ 3ኛ አገር ላይ ስጋት ከፈጠረ ተቀባይነት የለውም፡፡  

ሶማሌላንድ የግብጽን ጥያቄ መቀበ

የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውኃ ሙሌት ተጠናቀቀ

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERD-first-fillingJuly 22, 2020 (Ezega.com) -- ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ታሪካዊ ምእራፍ በመሸጋገር ለመጀመሪያ ዙር የታቀደለትን 4.9 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ሙሉ ለሙሉ መያዙ ተነገረ። ምንም እንኳን በአጠቃላይ ግድቡ ከሚያስፈልገው ከ74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ አንጻር ሲታይ ሙሌቱ እጅግ ብዙ የሚቀረው ቢሆንም ለመጪዎቹ የውሃ ሙሌት ተግባራት ወሳኝ ኩነት መሆኑን በርካቶች ይስማሙበታል። የጠቅላይ ሚንሰትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንደተገለጸው በዚህ ክረምት ባለው መልካም የዝናብ ሁኔታ ታግዞ በመጀመሪያው ዓመት ለመያዝ የታቀደው የውሃ መጠን ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ተጠናቆ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል። ይህንኑ የሚያሳየው የተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መታየቱን ተከትሎም በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና የመንግስት ባለስልጣናትም የደስታ መግለጫ መልእክቶችን ሲያስተላልፉ ውለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ‘እንኳን ደስ አላችሁ’ መ

የሕዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት ተጀመረ

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERD-filling-startsJuly 14, 2020 (Ezega.com) -- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውሀ መያዝ መጀመሩን ከተለያዩ ምንጮች እንዳረጋገጠ ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል። ቢቢሲ በበኩሉ የከረረ የዲፕሎማሲና የፀጥታ ውዝግብ መንስዔ የሆነው  የግድቡ የውሀ ሙሌት በይፋ ስለመጀመሩ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተሰጠ ማረጋገጫ ባይኖርም ከአካባቢው የተገኙ የሳተላይት ምስሎች በግድቡ ውስጥ ያለው የውሃ መጠን መጨመሩን አሳይተዋል ሲል አትቷል። ባለፉት ቀናት ግድቡ ውሀ መያዝ መጀመሩንና ወደ ግድቡ እየገባ ያለው የውሀ መጠንም 4, 400 ሜትር ኪዩብ በሰከንድ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከስር ያለው የመፋሰሻ ቱቦ (Culvert box) ደግሞ 1,700 ሜትር ኪዩብ በሰከንድ ማስተላልፍ ጀምሯል ተብሏል። የውሀ ፍሰቱ በየዕለቱ የተለያየ መጠን እንደሚኖረውና በነሐሴ ወር ከአሁኑ የበለጠ የውሀ መጠን ወደ ግድቡ እንደሚገባም የሜቶዎሮሎጂ ትንበያ ያመለክታል። በእዚህ ሂደት ከቀጠለም ግድቡ በመጀመሪያው ዓመት ሙሌት የታቀደውን 4.9 ቢሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ውሀ መያዝ ይችላል ተብሎ ታምኖበታል።

ከግድቡ አቅራቢያ የተሰበ

ኢትዮጵያ ከግብፅ የተሰነዘሩ ከባድ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፏን አስታወቀች

ኢዜጋ ሪፖርተር

Egypt-Ethiopia-CyberattackJune 24, 2020 (Ezega.com) -- በተለያዩ መቀመጫቸዉን ግብፅ ባደረጉ የሳይበር ወንጀለኞች በኢትዮጵያ ላይ የተቃጡ መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፉን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታውቋል። ጥቃቱ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በማስተጓጎል ከፍተኛ ጫና ለመፍጠር ታስቦ ሰኔ 10፣ 12 ፣ 13 እና 14/2012 ዓ.ም በተከታታይ እንደተሰነዘረ ኤጀንሲው አብራርቷል። የሳይበር ጥቃት ሙከራው በተለይ በተጠቀሱት ቀናት በተቀናጀ መልኩ የተቃጣው ሳይበር ሆሩስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከር እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ በተባሉ የግብጽ የሳይበር አጥቂዎች ቡድን አማካይነት መሆኑን ኤጀንሲው ጨምሮ ገልጿል። ወንጀለኞቹ በጉዳዩ ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ሲዘጋጁ የቆዩ እና ኤጀንሲው ሲከታተላችው የነበሩ መሆኑን የሚያስረዳው መረጃው ተቋማቱ በይበልጥ አርብ ሰኔ 12/2012 እና ቅዳሜ ሰኔ 13/2012 ዓ.ም ከፍተኛ የሚባል የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ማድረጋቸውን በመጥቀስ ይከስሳል።

የሳይበር ጥቃት ሙከራው በሀገሪቱ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የደህንነት

ኢትዮጵያውያን ጦርነትን እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ግብጾች ያውቁታል - ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERDJune 12, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሩ ህልውና እና ክብር ከመጡበት ሞት የማይፈራ ጀግና ህዝብ መሆኑን አይደለም ግብጽ የአለም ህዝብ ያውቀዋል ሲሉ የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ። ጀነራሉ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋራ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዳሉት የተሳሳተው የመሪዎቿ አስተሳሰብ ግብጽን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳት ይገኛል። የሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቭዥን ጣብያ 'ቃል በቃል' ባቀረበው ዘገባ ጀነራሉ ግብጾች ጦርነት ከመጣ ኢትዮጵያውያን እንዴት ጦርነትን መስራት እንደሚችሉ በሚገባ ያውቁታል ማለታቸውን አስታውቋል። ጀነራሉ የጦር መሳሪያ በገፍ መሰብሰብ ብቻ በጦርነት ውስጥ ለድል አያበቃም ያሉ ሲሆን በጦርነት ውስጥ ለድል የሚያበቁ ሳይንሳዊ የሆኑ የጦርነት መሰረታዊያን የሚባሉ ህጎች አሉ እነዚህ የጦርነት መሰረታዊያን ቁልፎች በሙሉ ደግሞ በኢትዮጵያውያን እጅ ናቸው ብለዋል።

ግብጾች ለ30 እና 40 አመታት የሰበሰቧቸው የጦር መሳሪያዎች አሏቸው በእዚህ አስፈራርተውም የጋራ የሆነውን ውሃ እንዳትነኩ ማለትን ይሞክራሉ ያሉት ጀነራል

በአዲስ መልክ የተጀመረው የግድቡ ድርድር በታዛቢዎች ሚና ላይ ውዝግብ ተነሳበት

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERD-TalksJune 10, 2020 (Ezega.com) -- ለወራት ተቋርጦ የነበረው እና በአለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ድርድር በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ መካከል ዳግም መካሄድ ጀምሯል። በአዲስ መልክ የተጀመረው የህዳሴው ግድብ ድርድር ደቡብ አፍሪካን፣ የአውሮፓ ሕብረትን እና አሜሪካን በታዛቢነት ማሳተፉ ታውቋል። ይሁን እንጂ በድርድሩ በታዛቢነት የሚሳተፉት አካላት ሚና ምን መሆን ይገባዋል በሚለው ሃሳብ ላይ በተደራዳሪ ሀገራቱ መካከል መግባባት ላይ መድረስ አለመቻሉ ተነግሯል። የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለውና ከሱዳንና ከግብጽ ጋር የተራዘመ ድርድርና ውይይት ሲደረግበት የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የተመለከተው ድርድር ማክሰኞ ሰኔ 2/2012 ዓ.ም በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካይነት በድጋሚ መጀመሩን አረጋግጦ በታዛቢዎቹ ሚና ዙሪያ በተነሳው አለመግባባት ዙሪያ ዝርዝር መረጃን ከመስጠት ተቆጥቧል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ እንዳለው "የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ልዩነቶችን በድርድር ለመፍታት ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛ

ግብጽ የኢትዮጵያን የድርድር ጥሪ ተቀበለች

ኢዜጋ ሪፖርተር

Egypt-Ethiopia-NegotiationsMay 23, 2020 (Ezega.com) -- ግብጽ እየከረረ የመጣውን የህዳሴ ግድብ አለመግባባት ለማርገብ 'ወሳኝ' የተባለለትን ውሳኔ ማሳለፏን አልጀዚራን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳለው "ግብጽ ግድቡን በተመለከተ ፍትሀዊ፣ ሚዛናዊና የሶስቱንም ሀገራት  ጥቅም የሚያስከብር ድርድር ለማድረግ ሁሌም ዝግጁ ናት።" በተጨማሪም በሶስቱ ሀገራት መካከል የሚደረገው ድርድር የሁሉንም በውሀው የመጠቀም ፍላጎትና መብት ከግምት ማስገባት እንደሚኖርበት የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  መግለጫ ጠይቋል። ይህ የግብጽ አዲስ አቋም የተሰማው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋራ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ካደረጉት ውይይት በኋላ መሆኑም ተሰምቷል።

ባሳለፍነው ወር ኢትዮጰያ የግድቡን የመጀመሪያውን ዙር የውሃ ሙሌት ማለትም 18.4 ሜትር ኪውብ ውሃ ከመጪው ሃምሌ ጀምሮ ማከናወን እንደምትጀምር ማስታወቋን ተከትሎ ግብጽና ሱዳን ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል። ግብጽ የግድቡ ድርድር

ሱዳን የግድቡ ግንባታ የደኅንነት ሥጋት ስላለበት የውኃ ሙሌቱ መጀመር እንደሌለበት አስታወቀች

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERD-fillingMay 19, 2020 (Ezega.com) -- ሱዳን በኢትዮጵያ የህዳሴ ግንባታ ላይ የደኅንነት ሥጋት እንዳላትና ይህ ጉዳይ መፍትሔ ሳያገኝ ኢትዮጵያ የግድቡን የውኃ ሙሌት መጀመር እንደሌለባት አስታውቃለች። ይሄኛው አስገራሚ የሱዳን አዲስ አቋም ፖለቲካዊ አጀንዳ ያነገበ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ተናግረዋል። ሪፖርተር እንደዘገበው ኢትዮጵያ በመጪው ሐምሌ ይጀመራል ያለችውን የግድቡን የውኃ ሙሌት ዕቅድ የያዘ ሰነድ ለታችኞቹ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት (ለሱዳን እና ግብጽ)  ለመላክ ከሰሞኑ ጥያቄ ያቀረበች ሲሆን ሁለቱ ሀገራት ግን ሰነዱ እንዲላክላቸው እንደማይፈልጉ አስታውቀዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ ከጠየቁ ታማኝ ምንጭ ተገኘ ብሎ ሪፖርተር እንደዘገበው በኢትዮጵያ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት የተሰናዳው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል ዕቅድና ሥነ ሥርዓትን ያካተተ ሰነድ ላይ ድርድር ለማድረግ እንዲረዳ በማሰብ ነበር ኢትዮጵያ ለግብፅና ለሱዳን መንግሥታት ሰነዱን ለመላክ ጥያቄ ያቀረበችው። ይሁን እንጂ ሁለቱም ሀገራት ሰነዱ እንዲላክላቸው እንደማይ

ኢትዮጵያ የኬንያን አውሮፕላን በስህተት መትታ መጣሏን አመነች

ኢዜጋ ሪፖርተር

Kenya-Aircraft-downMay 9, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሶማሊያ ውስጥ የኬንያን የጭነት አውሮፕላን መትቶ መጣሉን በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል አሚሶም አረጋገጠ። የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል አባል እንዳልሆነ የተነገረው የኢትዮጵያ ሠራዊት አንድ ክፍል ሶማሊያ ውስጥ አውሮፕላኑን መትቶ የጣለው ከአጥፍቶ ጠፊ ተልዕኮ ጋር ተመሳስሎበት መሆኑን አስታውቋል። በድምሩ አምስት ሰዎችን ጭኖ ሲበር የነበረው የጭነት አውሮፕላን በሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት ውስጥ ተመቶ የወደቀው ባሳለፍነው ሰኞ ሚያዚያ 26/2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ነበር። አውሮፕላኑ ለዩ ስሟ ባርዳሌ በምትባል ከተማ በሚገኝ አየር ማረፊያ አቅራቢያ የተመታ ሲሆን በክስተቱም የሁሉም ተሳፋሪዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል። አውሮፕላኑ ተመቶ የወደቀበት ቦታን ተቆጣጥሮ የሚገኘው የአሚሶም ሴክተር ሦስት ኃይል አዛዥ የሆኑት ብርጋዴየር ጀነራል አለሙ አየነ ለቢቢሲ እንዳሉት በአካባቢው ያለው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት አባላት ስለ በረራው የሚያውቁት ነገር ያልነበረ ከመሆኑም በላይ እና አውሮፕላኑ ለማረፍ የሄደበት አቅጣጫም አጠራጣሪ ነበር።

ኢትዮጵያ በግዛቷ የሚገኝ 600 ኪ.ሜ.ካሬ መሬት ለሱዳን ልትሰጥ መሆኑ ተሰማ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Al-Fashqa-Ethiopia-SudanApril 17, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ መንግስት ከጎረቤት ሱዳን ጋራ ከሰሞኑ ባደረገው ድርድር ሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑበት ድንበር አካባቢ ለአመታት 'ይገባኛል' በሚል ሲወዛገቡበት የነበረውን ሰፊና ለም የእርሻ መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት መስማማቱን የተለያዩ ምንጮች ዘግበዋል።  አሻርቅ አል-አውሳት የተሰኘው የሱዳን ተነባቢ ጋዜጣ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ውሳኔው በሁለት ሳምንታት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል። ጋዜጣው ማንነታቸው እንዲገለጽ ካልፈለጉ እማኞች አገኘሁት ባለው መረጃ ላይ እንደጠቀሰው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ከሱዳን መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ሲመክሩ ሰንብተዋል። በዚህም መሰረት ሁለቱ ሀገራት ወታደሮቻቸውን ከድንበር አካባቢ ለማስወጣትና ወሰን የማካለል ስራ ለመስራት የሚያስችል  ተግባራዊ እንቅስቃሴም ጀምረዋል።  ሱዳን በኢትዮጵያ ሰራዊት በሃይል ተይዞብኛል የምትለውና አል-ፋሻቅ በሚል የሰየመችው ለም የእርሻ መሬት በአማራ ክልል በተለይም ጎንደር አካ

ኢትዮጵያ የግድቡን ውኃ አሞላል የተመለከተውን አዲስ ሰነድ ይፋ አደረገች

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERDMarch 30, 2020 (Ezega.com) -- ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን በውኃ ለመሙላት የምትከተላቸውን ምዕራፎችና የአሞላል ሒደቶች አስመልክቶ ያዘጋጀችውን አዲስ ሰነድ ይፋ አደረገች። በውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በሌሎች ተባባሪዎች ተዘጋጅቶ በሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ ይፋ የተደረገው ሰነድ እንደሚያመለክተው በመጪው ክረምት የመጀመርያው ዙር የመጀመርያ ምዕራፍ ሙሌት የሚከናወን ሲሆን በዚህም ገደቡ4.9 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ እንዲይዝ ይደረጋል። የዚሁ የመጀመርያው ዙር ሙሌት ሁለተኛ ምዕራፍ ደግሞ በቀጣዩ ክረምት ማለትም በ2013 ዓ.ም. የዝናብ ወቅት ለሁለት ወይም ሦስት ወራት እንደሚከናወንና ግደቡ13.5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ በዚህ ወቅት እንዲይዝ ተደርጎ የመጀመርያው ዙር ሙሌት እንደሚጠናቀቅ ሰነዱ ያስረዳል። በዚህ ዙር የሚደረገው የውኃ ሙሌት በአጠቃለይ 18.4 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ በግድቡ እንዲጠራቀምና የመጀመርያዎቹ ሁለት ተርባይኖች ኃይል እንዲያመነጩ እንዲሁም ሌሎቹ ተርባይኖች ላይ የኃይል ማመንጨት ሙከራ ለማድረግ እንደሚያስችል ሰነዱ ይገልጻል።

በመቀጠል ሁለተኛው ዙር የ

ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ ሲጓዙ የነበሩ 64 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ህይወታቸው አለፈ

ኢዜጋ ሪፖርተር

64-dead-EthiopiansMarch 24, 2020 (Ezega.com) -- ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ በጭነት መኪና በተጫነ ኮንቴነር ውስጥ ሲጓዙ የነበሩ 64 ኢትዮጵያዊያን ህይወት መለፉ ታወቀ። በሞዛምቢክ ምዕራባዊ ግዛት በምትገኘው ቴቴ በተባለችው ክፍለሃገር ውስጥ በተገኘው ተሽከርካሪ ውስጥ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 14 የሚሆኑ ሰዎች በህይወት ተገኝተዋል ተብሏል። የቴቴ ክፍለ ሃገር የጤና ባለስልጣን የሆኑት ካርላ ሞሴ አንደተናገሩት "የሞዛምቢክ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ሰራተኞች የጭነት መኪናውን ሞአትዜ በተባለችው የግዛቲቱ ከተማ ውስጥ አስቁመው ሲፈትሹ ነው ሟቾቹን ያገኙት"ብለዋል። ቢቢሲ እንደዘገበው ባለስልጣኗ በጭነት መኪናው ላይ የተሳፈሩት ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸው በምን ምክንያት ሊያልፍ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው ያሉ ሲሆን ነገር ግን አየር በማጣት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

የሞዛምቢክ ብሔራዊ ኢሚግሬሽን አገልግሎት ቃል አቀባይ የሆኑት አሜሊያ ደሪዬሮ እንደተናገሩት ሟቾቹን ያሳፈረው የጭነት መኪና ሾፌር እንዲቆም ሲጠየቅ ፍላጎት አልነበረውም ብለዋል። ጨምረውም የኢሚግሬሽን ሰራተኞቹ ከመኪናው ውስ

የኢትዮጵያ ወታደሮች የኬንያን ድንበር አልፈው በመግባት 5 ንጹሃንን ገድለዋል - የኬንያ ባለስልጣናት

ኢዜጋ ሪፖርተር

Moyale-KenyaMarch 15, 2020 (Ezega.com) -- በኬንያዋ ማርሳቢት ግዛት ውስጥ በምትገኘው ሞያሌ ከተማ ልዩ ቦታው ሴሲ በተባለ መንድር በድንገት ወረራ የፈጸሙ የኢትዮጵያ ወታደሮች 5 ንጹሃን ዜጎችን ተኩሰው ገድለዋል ሲሉ የሀገሪቱ በርካታ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ወታደሮቹ ግድያውን የፈጸሙት የአካባቢው ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ጥቃት ፈጽመው የሸሹ የተቃዋሚ ቡድን አባላትን ሸሽገዋል በሚል ምክኒያት መሆኑን የአይን እማኞችን ጠቅሰው ዘ ስታርና ዘ ስታንዳርድ የተባሉት የሀገሪቱ ጋዜጦች አስነብበዋል። ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ 3:30 ላይ ወታደሮቹ የአንድ መኖሪያ ቤትን በር ገንጥለው በመግባት በቤቱ ውስጥ የነበሩ ባልና ሚስትን የገደሉ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላም እነዚሁ ታጣቂዎች በአካባቢው ሌሎች 2ሴቶችን መግደላቸው ተሰምቷል። በዛው እለት ከእነዚህ ግድያዎች ቀደም ብሎም በመንደሯ በሚገኝ የአውሮፐላን ማረፊያ ሜዳ አካባቢ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመሄድ ላይ የነበረ አንድ በእድሜ የገፋ የአካባቢው ነዋሪ በወታደሮቹ መገደሉን የጋዜጦቹ መረጃ  ያመለክታል።

የተፈጸመው ግድያ በሞያሌና በሌሎች የሁለቱ ሀገራት ድንበር ከተሞች በሚኖሩ ነ

የግድቡን መደራደሪያ ሰነድ የሚያዘጋጁትን ባለሞያዎች ያላግባባው ምንድን ነው?

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERDMarch 14, 2020 (Ezega.com) -- አሜሪካ በህዳሴ ግድቡ ውሀ አሞላልና አለቃቀቅ እንዲሁም በድርቅ ማካካሻ መርሀ ግብር ላይ ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳንን ለማደራደር የሄደችበት መንገድ ኢትዮጵያን ያላስደሰተ ሆኖ ሂደቱ ተስተጓጉሏል። በአሜሪካና አለም ባንክ  የተዘጋጀው ሰነድ ከመፈረም የተረፈውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በራሳቸው ተነሳሽነት ወደ ዋሽንግተን ለዚህ ጉዳይ አልሄድም በማለታቸው መሆኑን ዋዜማ ራዲዮ አስነብቧል። አሜሪካ ያዘጋጀችው የስምምነት ሰነድ ላይ ኢትዮጵያ አልፈርምም ማለቷ ተገቢ ውሳኔ በመሆኑ ከበርካታ ዜጎች ይሁንታን ያገኘ ሲሆን መንግስትም ይህንን ሰነድ የሚተካና ለግብጽና ሱዳን የሚቀርብ አዲስ የስምምነት ሰነድ እያዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በኢትዮጵያ በኩል እየተዘጋጀ ነው የተባለው የግድቡ የውሀ አያያዝና አለቃቀቅ ሰነድ በሚይዛቸው ይዘቶች ዙሪያ በውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለና በተዋቀረው የተደራዳሪዎች ቡድን አባላት መካከል አለመግባባቶች እንዳሉ ተዘግቧል። ዋዜማ ከታማኝ ምንጮች ተገኙ ባላቸው መረጃዎች መሰረት ዋናው የክርክሩ መነሻ ደግሞ ግድ

በግድቡ ላይ የሚቃጣን ጥቃት መክተን አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነን - የአየር ሃይል ዋና አዛዥ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Eth-Airforce-logoMarch 12, 2020 (Ezega.com) -- የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ሃይሉ በቀጠናው በተለይም በግድቡ ላይ ከማንኛውም አካል የሚቃጣን የአየር ላይ ጥቃት ለመመከት ብሎም አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። ኣዛዡ ይህንን ያሉት ከኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀኔራል አደም መሃመድ እና ከሌሎች የሰራዊቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋራ በመሆን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በጎበኙበት ወቅት ነው። በጉብኝቱ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ስለሺ በቀለ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። በዚህ ወቅት የመከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ህዝቦች ሰላምና ሉዓላዊነት የማስከበር ተልዕኮውን ለመወጣት በላቀ ብቃት ላይ የሚገኝ መሆኑን ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሃመድ ተናግረዋል።

የመከላከያ ሰራዊቱ ሀገራዊ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ህዝብ እና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮ በላቀ ብቃት እየተወጣ መሆኑን የገለጹት ጀኔራል አደም ከዚህም በተጨማሪ የሰራዊቱ

123456

Archived News

No News to show