አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - አለም አቀፍ

ያቀድነውን ከማሳካት የሚያግደን ምድራዊ ኃይል የለም - ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERD-response-TrumpOctober 25, 2020 (Ezega.com) -- "ግብጽ ግድቡን ታጋየዋለች!" የሚለው አስደንጋጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር ከተሰማበት ቅጽበት አንስቶ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ቁጣቸውንና ተቃውሟቸውን በተለያየ አግባብ ሲገልጹ ውለዋል። የፌደራልና የክልል ባለስልጣናትም በፕሬዝዳንቱ "ጠብ አጫሪ" ንግግር ዙሪያ በርከት ያሉ መግለጫዎችን አውጥተዋል። በተጨማሪም መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በኩል የአሜሪካውን አምባሳደር አስጠርቶ የትራምፕ አባባል ላይ ማብራሪያ ጠይቋል። አስቀድመን ከጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት የተሰጠውንና በቀጥታ የፕሬዝዳንቱን ንግግር ከማውገዝ ይልቅ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክና በግድቡ ላይ ያላትን ጠንካራ አቋም ማንጸባረቅን የመረጠውን መግለጫ ይዘት እንመልከት። መግለጫው "ማንም ገዝቶን አያውቅም ወደፊትም ማንም አይገዛንም ታሪክ የሠሩ እጆች ዛሬም አሉ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውን ለማክበር እንጂ ጠላቶቻቸውን ለመታዘዝ ተንበርክከው አያውቁም ዛሬም ወደፊትም አናደርገውም" በሚል ይጀምራል። በመቀጠልም ኢትዮጵያ በፍጣሪ

ኢትዮጵያ በግድቡ ጉዳይ ከስምምነት ለመድረስ ጊዜ እያለቀባት ነው - የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢዜጋ ሪፖርተር

US-State-DepartmentAugust 5, 2020 (Ezega.com) -- ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብጽና ሱዳን ጋራ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜው እያለቀባት ነው ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስጠንቀቁን ብሉምበርግ አስንብቧል። ሚኒስቴሩ ለጋዜጣው በኢሜል በላከው መልእክት እንዳሰፈረው ጊዜው አጭር ነው በግድቡ ጉዳይ እየተካሄደ ያለው ድርድር ግን በሚፈለገው ፍጥነት እየተጓዘ አይደለም ከዚህ አንጻር በሀገራቱ መካከል አንዳች ስምምነት ላይ ለመድረስ ያለው እድል እየጠበበ ነው ብሏል። በሶስቱ አገራት መካከል የሚደረግን ገንቢና ፍሬያማ ንግግር እናበረታታለን የሚለው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሁሉም አገራት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት ማሳየት ከቻሉ ግን ሶስቱንም ያማከለና አገራዊ ጥቅሞቻቸውን ከግምት ያስገባ ስምምነት ላይ መድረስ የሚቻልበት እድል መኖሩን ጠቁሟል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው አመት በግብጽ ጥያቄ መሰረት ሶስቱን አገራት ለማደራደር ወስነው ድርድሩ መካሄዱን ያስታወሰው ብሉምበርግ እርሱም ሆነ በቅርቡ በአፍሪካ ህብረት ታዛቢነት የተጀመረው ድርድር ውጤት አላስገኘም ይላል። ያም ሆኖ የአሜሪካ

በኦሮሚያ የተፈጸመው ድርጊት የዘር ማጽዳት ገጽታ ያለው ነው - አለም አቀፍ ሪፖርት

ኢዜጋ ሪፖርተር

Oromia-EthiopiaJuly 23, 2020 (Ezega.com) -- አለም አቀፉ የአናሳ ህዝቦች መብት ቡድን በቅርቡ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተፈጸመውን ግድያ፣ የአካል ማጉደልና የንብረት ማውደም ድርጊት በማውገዝ መግለጫ አውጥቷል። ድርጊቱ "በክልሉ በሚኖሩ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ህዝቦች በተለይም በአማራና ጉራጌ ብሄር ተወላጆች ላይ የተፈጸመ የዘር ማጽዳት ወንጀል ነው" ያለው ተቋሙ ሁኔታው የኦሮሞ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ምክኒያት አድርጎ መቀስቀሱን አስታውቋል። ከአርቲስቱ ሞት በኋላ በብዙ ቁጥር የተደራጁ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ወጣቶች በክልሉ የሚኖሩ አናሳ ቁጥር ያላቸውን የሌላ ብሄር ሰዎች ገድለዋል፣ በእነዚሁ ግለሰቦች ባለቤትነት የተቋቋሙ ሆቴሎችን፣ ት/ቤቶችን፣ የንግድ ተቋማትንና መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል ያለው ሪፖርቱ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ ኦሮሞዎች ያፈሯቸው ንብረቶች የተጎዱበት ሁኔታም አለ ብሏል። ተቋሙ የተፈጸመው ድርጊት የዘር ማጽዳት ገጽታ እንዳለው ያስረዳሉ ያላቸውን ነጥቦችም ዘርዝሯል በእዚህም መሰረት፦

1ኛ ጥቃቶቹ ቀድሞ የታቀዱ ናቸው

መንግስት እስረኞቹ ያሉበትን ቦታና ሁኔታ እንዲያሳውቅ አምነስቲ ጠየቀ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Amnesty-International-EthiopiaJuly 19, 2020 (Ezega.com) -- በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ሰዎች ያሉበትን ትክክለኛ ስፍራና ሁኔታ መንግስት በግልጽ ሊያሳውቅ አንደሚገባ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ። በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ቢያንስ 5 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የጠቀሰው የአምነስቲ የዛሬው ሪፖርት ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የት እንዳሉ በማይታወቁበት ሁኔታ ተለይተው መታሰራቸውን አመልክቷል። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ጃዋር መሐመድን ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፣ እሰክንድር ነጋን ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፖለቲከኞችን እና የኦ ኤም ኤን ጋዜጠኞችን በስም የዘርዘረው ሪፖርቱ ባለስልጣናት ታሳሪዎቹ ያሉበትን ቦታ ለቤተሰቦቻቸው "በአስቸኳይ በማሳወቅ ክስ እንዲመሰርቱባቸው ካልሆነም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ" የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ኃላፊ ዲፕሮስ ሙቼና ጠ

ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ የነበረውን 500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገደ

ኢዜጋ ሪፖርተር

World-Bank-Ethiopia-AidJune 29, 2020 (Ezega.com) -- የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለመስጠት አቅዶ የነበረውን የ500 ሚሊዮን ዶላር አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ወደ ባንኩ ቦርድ ቀርቦ እንዳይጸድቅ ማገዱ ተሰምቷል። 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ከተቋሙ ታማኝ ምንጮች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት የእገዳ ውሳኔውን ያስተላለፉት የዓለም ባንክ ከፍተኛ የስራ አስፈጻሚ አባላት ናቸው። በኢትዮጵያ መንግስት ጠያቂነት ለስምምነት ተዘጋጅቶ የነበረው ይህ የገንዘብ ድጋፍ ለባንኩ የስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀርብ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ለመጪው ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ/ም የነበረ መሆኑን እና ባንኩ የገንዘብ ድጋፉን ያገደው በሁለት ምክንያቶች መነሻነት እንደሆነ የተቋሙ ምንጮች ተናግረዋል። የመጀመሪያ ነው ተብሎ በመረጃ ሰጪዎቹ የተጠቀሰው ምክንያት "ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ተመኗን ለማስተካከል እየሄደችበት ያለው አካሄድ አዝጋሚ ነው" የሚል ነው። ሆኖም ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ እንድታደርግ ተደጋጋሚ ጉትጎታዎችን እና ግፊቶችን ሲያደርግ የቆየው የዓለም አቀፉ የገን

አዳዲሶቹ አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ታወቁ

ኢዜጋ ሪፖርተር

New-Ambassadors-EthiopiaMarch 26, 2020 (Ezega.com) -- በቅርቡ ባልታሰበ ሁኔታ በጠቅላይ ሚንስትሩ ትእዛዝ ከተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ተነስተው በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት "የተሾሙ" ባለስልጣናት ጉዳይ በአጅጉ አነጋጋሪ ክስተት ሆኖ ቆይቷል። በተመሳሳይም ሀገሪቱ በተለይ በግብጽ ሱዳንና  ቤልጂየም የነበሩ አምባሳደሮቿን እንዲመለሱ ያስተላለፈችው ጥሪም ብዙ ጥያቄዎችን ሲያስነሳ ቆይቷል። የውጭ ጉይ ሚንስቴር በዛሬው እለት ይፋ ያደረገው መረጃም አዳዲሶቹ አምባሳደሮች የተመደቡባቸውን ሀገራት ዝርዝር አሳውቋል። ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ ናቸው ተበለው "ሹመቱ" የተሰጣቸው 15 ባለስልጣናት ጉዳይ ከተሰማበት ካሳለፍነው የካቲት 24 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ ስለ ሚመደቡባቸው ሀገራት በርካታ መላምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። ያም ሆኖ የውጭ ጉይ ሚንስቴር ይፋ ያደረገው ምደባ በሚከተለው መሰረት ሆኗል፦

በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት የተመደቡ፦
1. አምባሳደር ብርሁኑ ፀጋዬ- አውስትራሊያ ካንቤራ
2. አምባሳደር ያለ

ኢትዮጵያ በኮሮና ምክኒያት ሁሉንም ድንበሮቿን ለሰዎች ዝውውር ዘጋች

ኢዜጋ ሪፖርተር

Ethiopia-BorderMarch 23, 2020 (Ezega.com) -- መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም የሃገሪቱ ድንበሮች ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ለሰዎች ዝውውር ዝግ መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። የድንበር መዘጋቱ የሎጅስቲክስ አቅርቦት ለማዳረስ የሚደረገውን ተግባር  እንደማያካትትም ተሰምቷል ከዚህ ውጪ ያሉትን ግን ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት በድንበር አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ይገታል ተብሏል። በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የተገመገሙ ሲሆን ማህበረሰቡ ከንክኪ ተራርቆ እንዲንቀሳቀስ የተላለፈው መልዕክት ባለፉት ቀናት በአግባቡ እየተፈጸመ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል። አንደርሳቸው አባባል ባለፉት ቀናት በተለይ ቅዳሜ እና እሁድ በነበሩ የእምነት ተቋማት መርሃ ግብሮች ላይም በቂ የመከላከል እርምጃ እንዳልተወሰደ ተገምግሟል። በመሆኑም የሃይማኖት አባቶች በቀጣይ ምዕመኖቻቸውን ከማስተማር ባለፈ በተግባር እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈ ሰዎችን በአ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሃገራት የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Ethiopian-AirlinesMarch 20, 2020 (Ezega.com) -- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 ሃገራት የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከየትኛውም ሃገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ እንደተጣለባቸው እና በዚህ የ14 ቀናት ቆይታቸውም ወጪያቸውን ሙሉ በሙሉ  ራሳቸው እንዲሸፍኑ መወሰኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል፡፡ በአጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ሀገራዊ ስጋቶችና በመንግስት የሚወሰዱ እርምጃዎች ዙሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማምሻውን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የህግ ታራሚዎችን በሚመልከት በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ቫይረሱ ከገባ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጠር በመሆኑ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ እና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው ታራሚዎች በነጻ እንዲለቀቁ መወሰኑንም አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ የምሽት መዝናኛ ክለቦች አገልግሎት እንዳይሰጡ ሙሉ ለሙሉ ተከልክሏል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ የእምነት ተቋማትን አስመልክተው በሰጡት መረጃም ቤተ እምነቶቹ ከሚሰበስቧቸው በርካታ

በአለም አቀፍ የወንጀል ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የገባ የጦር መሳሪያ መያዙ ተነገረ

ኢዜጋ ሪፖርተር

NISS-ethiopiaMarch 11, 2020 (Ezega.com) -- የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በአለም አቀፍ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ቡድን አማካኝነት በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን የገባ ሁለት ኮንቴነር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን አስታወቀ።  ተቋሙ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ መሰረት መነሻውን ከቱርክ ሜርሲን ወደብ ያደረገው ህገወጥ የጦር መሳሪያው በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ገብቶ በቁጥጥር ስር የዋለው በወደቡ ለአምስት ወራት ያህል በድብቅ ተቀመጦ በረቀቀ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ከገበ በኋላ ነው። ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ህገወጥ የጦር መሳሪያውን በተመለከተ የመረጃ ጥቆማ ካገኘበት ወቅት አንስቶ ለረጅም ግዜ አስፈላጊውን ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን  ጠቁሞ ህገወጥ የጦር መሳሪያው በምን መልኩ፣ እንዴትና በማን ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ እንደሚችል ለመለየት ልዩ የኦፕሬሽን ስራ ሲያካሂድ መቆየቱን አስረድቷል።

ግምታቸው ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሆኑ 501 እሽግ ካርቶኖች ከ18 ሺህ በላይ ቱርክ ሰራሽ

የአድዋን ድል ስናስታውስ የሕዳሴን ግድብ ስኬታማ ለማድረግ የዓላማ አንድነት እንፍጠር

በአክሎግ ቢራራ (ዶር), March 6, 2020

Nile-Ethiopia“አምላካችን የባረከላትን ይህን ኃብቷን (ዐባይን) ለሕዝቦቻቸው ህይወትና ደህንነት ለማዋል እንዲጠቀሙበት ከጎረቤት ወዳጅ አገሮች ጋር በለጋስነት ለመካፈል ዝግጁ ብንሆንም፤ ይህን የውሃ ንብረቷን በቁጥር እየጨመረ ለሚሄደው ሕዝቧና በማደግ ላይ ላለው ኢኮኖሚዋ ጥቅም እንዲውል ማድረግ የኢትዮጵያ ተቀዳሚና የተቀደሰ ግዴታዋ ነው።” --ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ-- ጥቅምት 1957 ዓ.ም.

“ነፋስ እንዳይገባባችሁ፤ አገራችሁን በያላችሁበት በርትታችሁ ጠብቁ፤ ወንድሜ፤ ወንድሜ እየተባባላችሁ ተደጋገፉ። የኢትዮጵያን ጠላት ተጋግዛችሁ ተድንበር መልሱ። የኢትዮጵያ ጠላት ባንዱ ወገን ትቶ ባንዱ ወገን ቢሄድና ደምበር ቢገፋ በኔ ወገን ታልመጣ ምን ቸገረኝ ብላችሁ ዝም አትበሉ…ጠላታችሁን መልሱ፤ እስከ እየቤታችሁ እስቲመጣ ዝም ብላችሁ አትቆዩ…” --አጼ ምኒሊክ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከጻፉት ደብዳቤ የተቀዳ

የአድዋን የሃያ አራተኛ ዓመት የድል በዓል በሃገር ውስጥና ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ እድሜ፤ ጾታ፤ ዘውግ፤ ኃይማኖት ሳይለያየው

ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ለዓረብ ሊግ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን ውድቅ አደረገችው

ኢዜጋ ሪፖርተር

Arab-League-CouncilMarch 6, 2020 (Ezega.com) -- ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ውዝግብ ዙሪያ የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት ኢትዮጵያን በመቃወም ከጎኗ እንዲሰልፉ በማሰብ ያቀረበችውን ሰነድ ሱዳን እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡ በግብጽ ርዕሰ መዲና ካይሮ በተካሔደው የዓረብ ሊግ 153ኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ግብጽ በግድቡ ዙሪያ የሊጉ አባል ሀገራት ከጎኗ እንዲቆሙ ያቀረበችው ሰነድ ላይ ነው ሱዳን ያላትን ልዩነት በይፋ የገለፀችው፡፡ በስብሰባው ላይ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ የአረብ ሀገራት በግድቡ ዙሪያ ከግብጽ እና ሱዳን ጎን እንዲቆሙ ጥያቄ አቅርበው ለዚህም ይረዳ ዘንድ ሱዳንና ግብጽን በመደገፍ የተዘጋጀ ነው ያሉትን ሰነድ በማቅረብ አባላቱ እንዲያጸድቁት ጠይቀው ነበር፡፡ አህራም ኦንላይን የተሰኘው የግብፅ ሚድያ እንደዘገበው ጅቡቲና ሶማሊያን ጨምሮ ሌሎቹ የሊጉ አባል ሀገራት ያጸደቁትን ይህንኑ የትብብር ውሳኔ ሱዳን እንደምትቃወመው አስታውቃለች፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በግብጽ የተዘጋጀውን ይህንን የድጋፍ ማሰባሰቢያ ሰነድ እንደማትቀበል ያስታወቀችው ሱዳን

ከግድቡ ውሃ ሙሌት አስቀድሞ ስምምነቱ መፈረም አለበት - አሜሪካ

ኢዜጋ ሪፖርተር

US-GERDFebruary 29, 2020 (Ezega.com) -- የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን በውሃ በመሙላት የሙከራ ሥራውን ከማስጀመሯ በፊት  ከግብጽ እና ሱዳን ጋር የተጀመረውን ድርድር ዳር ማድረስ እና ስምምነት መፈረም እንዳለባት አመለከተ። የሃገሪቱ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳለው ቀደም ሲል ተፈርም በነበረውና 'ግንባታው በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት ማድረስ የለበትም' በሚለው የመርህ ስምምነት መሰረት ግድቡን በውሃ የመሙላትና ሥራውን የመሞከሩ ሂደት የስምምነት ፊርማው ሳይፈረም  መከናወን የለበትም። የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቴቨን ምኑቺን በመግለጫው ላይ እንዳሉት ከዚህ በፊት በነበሩ ስምምነቶች መሰረት ግድቡን በውሃ የመሙላቱ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በሀገራቱ መካከል ስምምነት መፈረም አለበት። ለዚህም በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል የተጀመረው ድርድር በቶሎ መጠናቀቅ እንዳለበት የሚያሳስበው የሚኒስትሩ መግለጫ በተለይም ግብጽ ስምምነቱን ለመፈረም ያሳየችውን ዝግጁነት አድንቋል።

በመግለጫው አሜሪካ በኢትዮጵያ በኩ

ኢትዮጵያ በዋሽንግተኑ ድርድር ላይ እንደማትሳተፍ አስታወቀች

GERD-talksአዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (Ezega.com) -- ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ የካቲት 19 እና 20 ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በአሜሪካ ሊካሄድ በታሰበው ድርድር ላይ እንደማትገኝ ይፋ አድርጋለች፡፡ ግድቡን የተመለከተው ድርድር በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል የአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ እና የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ‹‹በታዛቢነት›› በተገኙበት በአሜሪካ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ የዚሁ ቀጣይ የሆነ የሁለት ቀናት ድርድር በእዛው በዋሽንግተን ከተማ ይካሄዳል በሚል አሜሪካ ለሶስቱም ሀገራት ጥሪ ያስተላለፈች ቢሆንም የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ‹‹በሃገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባላማጠናቀቁ›› ሊካሄድ በታሰበው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ እንደማይሳተፍ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ሚኒስቴሩ በተጠቀሰው ጊዜ አሜሪካ በመገኘት ድርድሩን ማድረግ እንደማይችል ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ቢሮ ማስታወቁንም ጠቅሷል፡፡

በግድቡ የውሃ አሞላልና አ

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድርጊት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አበሳጨ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Mike-Pompeo-AbiyFebruary 20, 2020 (Ezega.com) -- የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ የኢትዮጵያን እና የአሜሪካን ግንኙነት ለማጠናከር ብሎም በቀጣይ የትብብር አቅጣጫዎች እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በሚል መነሻ ባሳለፍነው ሰኞ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፣ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትላንትናው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ለመነጋገር ወደ ጽሕፈት ቤታቸው አምርተው ያሳዩት ባህሪ ግን ጠቅላይ ሚንስትሩን ያበሳጨ እንደነበር ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በዕለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮን የያዘው ተሽከርካሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በር ላይ የደረሰው ረፋድ አካባቢ ላይ ነው፡፡ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተለመደው ዲፕሎማሲያዊ ስነስርዓት መሰረት ለውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ለማድረግ በሩ ላይ ቆመው እየጠበቋቸው ነበር፡፡ ተሸከርካሪው አጠገ

የግድቡ ድርድር ተራዘመ - በኢትዮጵያ ላይ ማስፈራሪያ እየተደረገ ነው ተብሏል

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERD-Washington-TalksJanuary 30, 2020 (Ezega.com) -- በአሜሪካዋ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ላለፉት ሁለት ቀናት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በተለይም በውሀ አሞላል፣ አለቃቅ እና የድርቅ ማካካሻ ተግባራት ዙሪያ ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች በተመለከተ ከቀናት በፊት መግባባት ላይ ደርሰዋል የተባሉት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በውጭ ጉዳይ እና በውሀ ሚኒስትሮቻቸው እንዲሁም በቴክኒክ ባለሙያዎቻቸው አማካይነት ተወክለው ሲመክሩ የቆዩ ቢሆንም በሁለቱ ቀናት ውይይት የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረስ አለመቻላቸው ተሰምቷል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን ወሳኝ የድርድሩን ነጥቦች በሚወስነው መመሪያ ላይ ከስምምነት ለመድረስ አልሞ አሜሪካ እና የአለም ባንክ በታዛቢነት በተገኙበት በተካሄደው የሁለት ቀኑ የዋሽንግተን ስብሰባ ላይ በተለይ በተከታታይ አመታት ድርቅ ቢከሰት ምን ያህል የውሀ መጠን በምን ዓይነት መንገድ ይለቀቅ የሚለው ጉዳይ ሀገራቱን ያላስማማቸው ዋነኛ ነጥብ ነው፡፡

በግብጽ በአሜሪካ እና በአለም ባንክ በኩል ለተከታታይ አመታት ድርቅ ቢከሰት ውሀ እንዴት መለቀቅ አለበት በሚለው

አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጲያ ለመስጠት ቃል የገባውን የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ

ኢዜጋ ሪፖርተር

IMF-EthiopiaDecember 22, 2019 (Ezega.com) -- ኢትዮጵያ ለቀረጸችው የሶስት ዓመት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ማስፈጸሚያ ከሚያስፈልጋት 10 ቢሊየን ዶላር ውስጥ የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) 2.9 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን ለመሸፈን መስማማቱን የገንዘብ ሚኒስትር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ በእዚህም መሰረት የተቋሙ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ብድሩን ማጽደቁን ይፋ አድርጓል፡፡ አይ ኤም ኤፍ በድህረ ገጹ ባወጠው መረጃ እንዳስነበበው ይኸው በረዥም ጊዜ የሚከፈል እና አነስተኛ ወለድ ያለው የብድር ድጋፍ በሶስት ዓመታት ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን ከእዚህም ውስጥ 308 ሚሊዮን ዶላሩ በፍጥነት የሚለቀቅ ይሆናል፡፡ የብድር ድጋፉ መዕቀፍ ሀገሪቱ ያለባትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማቃለል፣ ድህነትን ለመቅረፍ ለሚውሉ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እና ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የሚያግዙ ሀገራዊ ሀብቶችን ለማሰባበሰብ እንደሚውልም ተነግሯል፡፡

የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ምክትል ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት ዴቪድ ሊ

ጃፓን 115 ዘመናዊ የመንገድ ግንባታ ማሽኖችን ለኢትዮጵያ ሰጠች

ኢዜጋ ሪፖርተር

Japan-EthiopiaDecember 16, 2019 (Ezega.com) -- የጃፓን መንግስት ለአዲስ አበባ የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውሉ 115 ዘመናዊ የመንገድ ግንባታ መሳሪያዎችን ለኢትዮጵያ በስጦታ ለማበርከት የሚያስችለውን ስምምነት ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ተፈራረመ፡፡ ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋቸው 12.7 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ 400 ሚሊዮን የኢትዮጲያ ብር በላይ መሆኑ የተነገረላቸው የእነዚህ ማሽኖች የድጋፍ ስምምነት የተፈረመው በገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር በሆኑት ዳይሱኬ ማስቱናጋ አማካኝነት ነው፡፡ ለአስፓልት መንገዶች ግንባታ እና ጥገና የሚያገለግሉት መሳሪያዎቹ 36 አይነት መሆናቸው በስምምነቱ ወቅት የተገለጸ ሲሆን ሁሉም ማሽኖች አጅግ ዘመናዊ በመሆናቸው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚከናወኑ የመንገድ ግንባተዎችን በከፍተኛ ጥራት እና በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚያግዙም ተጠቅሷል፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከስምምነቱ በኃላ እንደተናገሩት የጃፓን መንግስት ያደረገው ድጋፍ ከአዲስ አበባም አልፎ በመላው ሀገሪቱ በመንግስት አቅም የሚከናወኑ የመንገድ ስራዎችን በብ

የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ የዓለም ቅርስ ሆኖ ተመዘገበ

ኢዜጋ ሪፖርተር

Ethiopian-Epiphany-UNESCODecember 12, 2019 (Ezega.com) -- የጥምቀት በዓል የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ መወሰኑን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስታወቀ። በውሳኔው መሰረት በኢትዮጵያ የሚከበረው ጥምቀት በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ጥበቃ ከሚደረግላቸው የማይዳሰሱ የሰው ልጆች ቅርሶች ተርታ ተመድቧል ማለት ነው። ድርጅቱ የጥምቀት በዓል አከባበር የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ውሳኔ ያስተላለፈው በኮሎምቢያዋ ቦጎታ ከተማ በቅርስ ጥበቃ ዙሪያ ባካሄደው ስብሰባ ወቅት መሆኑም ተዘግቧል።

በመሆኑም በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት መካካል አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል ከመስቀል፣ ከገዳ ስርዓት እና ከፍቼ ጨምበላላ በዓላት በመቀጠል በዩኔስኮ የተመዘገበ አራተኛው ኢትዮጵያዊ የማይዳሰስ ቅርስ ለመሆን ችሏል። የጥምቀት በዓለም ቅርሶች ዝርዘር ውስጥ መካተት ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ያስመዘገበቻቸውን ቅርሶች ብዛት 13 ያደረሰው ሲሆን

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በግድቡ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ዙሪያ መመሪያዎችን ለማውጣት ተስማሙ

ኢዜጋ ሪፖርተር

GERD-meeting-DCDecember 10, 2019 (Ezega.com) -- በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ዲሲ ለሁለተኛ ጊዜ ተገናኝተው የመከሩት የኢትዮጵያ፣ የግብፅ እና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች በመጀመሪያው ዙር ውይይት በታዛቢዎች ፊት ለማካሄድ ከተስማሙባቸው አራት ድርድሮች መካከል የቀጣዮቹ ሁለት መድረኮች ትኩረት ለግድቡ የውሃ ሙሌት፣ አለቃቀቅ እና አስተዳደር የሚረዱ ቴክኒካዊ መመሪያዎችን ማውጣት እንዲሁን ተስማምተዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የታደሙት የሦስቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚንስትሮች በተስማሙት መሰረት የቀጣዮቹን ድርድሮች የትኩረት አቅጣጫ አስቀድሞ መወሰን ባልተግባቡባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በፍጥነት ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደሚያግዝ አምነንበታል ብለዋል፡፡ ሶስቱ የተፋሰሱ ሀገራት፣ አሜሪካ እና የአለም ባንክ ከዋሽንግተኑ ስብሰባ በኃላ ባወጡት የጋራ መግለጫ ላይ እንደተብራራው የሚዘጋጁት ደንቦች እና መመሪያዎች የግድቡን ውሃ አሞላል እና አለቃቅ እንዲሁም አስተዳደር የሚገዙ ይሆናሉ፡፡ ከእዚህም በተጨማሪ ሕገ ደንብና መመሪያዎቹ ከግድቡ ጋር በተጓዳኝ መታየት ስላለባቸው የድርቅ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ170 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሰጠ

ኢዜጋ ሪፖርተር

EU-EthiopiaDecember 8, 2019 (Ezega.com) -- የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለምታካሂዳቸው የልማት እና የዴሞክራሲ ተግባራት የሚውል የ170 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። የህብረቱ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን የተመረጡት ኦርሱላ ቮን ደር ሌይን የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ እያደረጉ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድም ዛሬ ጠዋት አደስ አበባ የገቡትን የህብረቱን ፕሬዝዳንት በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡ በእዚሁ ውይይት ወቅት ነው በኢትዮጵያ እና በህብረቱ ኮሚሽን መካከል በጠቅላላው የ170 ሚሊዮን ዩሮ ዋጋ ያላቸው አራት የሚደርሱ የድጋፍ ስምምነቶች የተፈረሙት፡፡

የድጋፍ ስምምነቶቹ በኢትዮጲያ በኩል በፋይናንስ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ህብረቱን በመወከል ደግሞ በዓለም-አቀፍ ትብብር የአውሮፓውያን ኮሚሽነር በሆኑት ዩታ ኧርፒላይነን መካከል ጠቅላይ ሚንስትሩ እና የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት በተገኙበት ተፈርሟል፡፡ የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ለፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች የሚውል እንደሆነም በፊርማ ስነስርአቱ ወቅት ተገልጿል፡

12345

Archived News

No News to show