ቴዲ አፍሮ በባህር ዳር የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው
January 14, 2018 - በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ በባህር ዳር ከአንድ ሳምንት በኋላ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ዝግጅት፣ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደማይኖር ተገለጸ፡፡
‹‹የሙዚቃ ዝግጅቱን ሁሉም የሚፈልገው ስለሆነ የፀጥታ ችግር አይኖርም፤›› ሲሉ፣ የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ከዚህ ቀደም በክልሉ በተለይም በባህር ዳር የተለያዩ ጥቃቶች መድረሳቸው ይታወሳል፡፡ በተለይም በክልሉ ተቀስቅሶ በነበረው አመፅ በባህር ዳር ከተማ በተደጋጋሚ የቦምብ ጥቃቶች ደርሰው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ይህ የሙዚቃ ዝግጅት ለቴዲ አፍሮ ከአራት ዓመታት በኋላ የመጀመርያው የሚሆን ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በተለይም በአዲስ አበባ ለማድረግ ያቀረባቸው ጥያቄዎች ሳይሳኩ ቀርተዋል፡፡
በተለይ ‹‹ኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ለለቀቀው የሙዚቃ አልበም በሚሊኒየም አዳራሽ ሊያደርገ
|
የአዲስ አበባ አስተዳደር የቴዲ አፍሮ አልበም ምረቃ ፕሮግራም ወቅቱን የጠበቀ የዕውቅና ጥያቄ አልቀረበለትም አለ
September 8, 2017 - እሑድ ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በይፋ እንደሚመረቅ ቀን የተቆረጠለት የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ‹‹ኢትዮጵያ›› የተሰኘ አልበም ምርቃት ፕሮግራም፣ ወቅቱን የጠበቀ የዕውቅና ጥያቄ እንዳልቀረበለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ረዳትና የሰላማዊ ሠልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ ፈቃድ ክፍል ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ ተስፋ ዋቅጅራ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሒልተን አዲስ ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. የአልበም ምረቃ ለማካሄድ ጥያቄ የያዘውን ደብዳቤ የተመለከቱት ሰኞ ነሐሴ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. ነው፡፡
‹‹ሐሙስ ነሐሴ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 9፡30 ድረስ ቢሮ ነበርኩ፡፡ የቀረበ ደብዳቤ የለም፡፡ በነጋታው ዓርብ የኢድ አል አድሃ (ዓረፋ) በዓል ስለነበር ሥራ የለም፡፡ ሰኞ ቢሮ ስገባ ደብዳቤውን አግኝቻለሁ፡፡ አለመታደል ሆኖ ግን ቀኑ አልፏል፤›› ሲሉ ፕሮግራሙን
|
ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ለማቅረብ የመንግስት ይሁንታን እየጠበቀ ነው
July 10, 2017 - ቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ" የተሠኘውን አልበም ካወጣ በኋላ ፤ በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን ኮንሰርት ለማቅረብ የመንግስት ይሁንታን እየጠበቀ ነው፡፡
ድምጻዊው ጳጉሜን 5 ቀን 2009 ዓ.ም ለአዲስ አመት ዋዜማ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማቅረብ መዘጋጀቱን ማኔጀሩ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ለሪፖርተር ገልፀዋል፡፡
ኮንሰርቱን አልበሙን ያከፋፈለው ኩባንያ ጆይ ኢቨንትስና ፕሮሞሽን ኩባንያ ከኤፕላስና ኤቨንት ፕሮሞሽን ኩባንያ ጋር በመተባባር የሚያዘጋጁት መሆኑን እና ጆይ ኤቨንትስ የሚሊኒየም አዳራሽን ከሚያስተዳድረው አዲስ ፓርክ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ጆይ ኢቭንትስ ኮንሰርቱን ለማዘጋጀት የሚያስችል ዕውቅና ለማግኘት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ፈቃድ ማሳወቂያ ክፍል ጥያቄ ማቅረቡም ታውቋል፡፡ የአዲስ ፓርክ ዴቨሎፕመንትና ማኔጅመንት ኩባንያ የማርኬቲንግና የሰው ሃይል መምሪያሃላፊ አቶ ስለሺ ለማ ፤ ሰኔ 2 ቀን 2009 ዓ.ም ለከንቲባ ፅህፈት ቤት በፃፉት ደብዳቤ ለ
|