አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - ሲነማ

ብሔራዊ የጋራና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ

satellite-platform-launchedApril 21, 2017 - ኢትዮ ሳት የተሰኘ ብሄራዊ የጋራ እና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ ሲል ፋና ዜና አስታወቀ።

የቴሌቪዥን ስርጭት ሳተላይት ማዕቀፉ የሚዲያ እኩልነትንና ፍትሃዊነትን እንዲሁም ተደራሽነትን በማረጋገጥ በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚናን ይጫወታል ተብሏል።

ኢትዮ ሳት የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሳተላይት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ለሳተላይት ኪራይ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረትና የመረጃውን ደህንነት በመቆጣጠር ረገድ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ ተናግረዋል።

ሳተላይቱ በሀገር ውስጥ ያለውን የሚዲያ ተደራሽነት በማስፋት ከሞገድ አጠቃቀም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላልም ነው የተባለው።

በሀገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ሊደረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኘው ሳተላይቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ አስራ አንዱም ክልሎች የቴሌቪዥን ስርጭታቸውን በአንድ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

ከዚህ በተጨ

ለ3 የግል ቴሌቪዥንና ለ3 የኤፍኤም ሬዲዮ ፈቃድ ተሰጠ

Ethiopia grants TV licenseOctober 29, 2016 - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ለሁለት “ሴት ቶፕ ቦክስ” አምራቾች፣ ለሦስት የግል ቴሌቪዥንና ለሦስት የኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስተር ድርጅቶች ፈቃድ ሰጠ፡፡  

ባለፈው ረቡዕ በሸራተን አዲስ በተከናወነው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት፣ “ሴት ቶፕ ቦክስ” ለማምረት ከባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ዘርዓይ አስገዶም ጋር የተፈራረሙት ጣና ኮሙኒኬሽን ኃ.የተ. የግ.ማ እና ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሃይቴክ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ናቸው፡፡

የግል የቴሌቪዥን ብሮድካስት ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስት ድርጅቶች፡- ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ኃ.ተ. የግ.ማ ናቸው፡፡ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ብሮድካስቲንግ ፈቃድ የተሰጣቸው ሦስት ድርጅቶች ደግሞ ኤዲስቴለር ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ (አሐዱ 94.3)፣ አርኪ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስና ዋን ላቭ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ኃ.የተ. የግ.ማ (ሉሲ 107.8) ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ናቸው፡፡ በዕለቱ የተሰጠው ሦስት የኤፍ ኤም ሬዲዮ

Archived News

No News to show