የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በአዲስ ስያሜ ሊደራጅ ነው
October 15, 2018 - የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወታደራዊ ምርት የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎችን ለመከላከያ ሚኒስቴር በማስረከብ በአዲስ ስያሜ ሊደራጅ ነው።
ከተቋቋመ ጀምሮ በጥቂት ጊዜ በርካታ የመንግስት ፕሮጀክቶችን እንዲይዝ ተደርጎ የነበረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከብቃት፣ እጦትና ከብክነት ጋር ተያያዘ ስሙ ሲነሳ ቆይቷል።
እጁ ላይ የነበሩ በርካታ የስኳር ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ አቅቶት ፕሮጀክቶቹን ሲቀማ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሃይድሮ መካኒካል ስራዎችን ወስዶ መስራት ባለመቻሉም ቢሊየን ብሮች እንደባከኑ ተሰምቷል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የኮርፖሬሽኑን አመራሮች ከመቀየር አንስቶ የተለያዩ እርምጃዎች እንዲወሰድበት እያደረገ ነው።
የኮርፖሬሽኑ የኮመርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልዓዚዝ መሀመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አሁን በመንግስት የተወሰደው እርምጃ የኮርፖሬሽኑን አደረጃጀት ማስተካከል ነው።
ይህም በሜቴ
|
አለም አቀፍ ኩባንያዎች በሀገር ውስጥ የሎጂስቲክስ ስራ እንዲሰማሩ ተወሰነ
September 4, 2018 - የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ የአምራቹን ዘርፍ ዕድገት ለማፋጠንና ኢንቨስትመንትን እንዲሁም የውጭ ንግድ አፈፃፀምን በበቂ መጠን ለማሳደግ የሚያግዝ የፖሊሲ ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ የተላለፈው ውሳኔ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ጋር ከሀገር ውስጥ የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች በሽርክና መስራት የሚያስችል መሆኑም ተነግሯል።
በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የአምራቹን ዘርፍ ዕድገት ለማፋጠን፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና የውጭ ንግድ አፈፃፀምን በበቂ መጠን ለማሳደግ የሎጂስቲክስ እና የጉምሩክ አሰራሮችን ማሻሻል እንደሚገባ የተገለፀ ቢሆንም እስካሁን በዘርፉ ይህ ነው የሚባል ጉልህ መሻሻል አልታየም ብሏል ቦርዱ በመግለጫው።
በአጠቃላይ ዘርፉ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ ብዙ ርቀት መጓዝ የሚኖርበት ሲሆን፥ ለዚህም እንደማሳያ የሚሆነው የሀገሪቱ የሎጂስቲክስ ኢንዱስትሪና የጉምሩክ ስርዓት ከአለም አቀፍ መመዘኛዎች ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ አፈፃፀም ላይ መገኘቱ
|
ኢትዮ ቴሌኮም በስልክ አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ አደረገ
August 22, 2018 - ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ በሰጠው መግለጫ፥ ተቋሙ በሞባይል ስልክ እና በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህ መሰረት የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የ43 በመቶ፣ የስልክ ድምፅ ላይ የ40 ከመቶ እንዲሁም አጭር የሞባይል የፅሁፍ መልዕክት ላይ የ43 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ገልጿል።
የታሪፍ ቅናሹ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም ነው የገለጸው።
የታሪፍ ቅናሹን ተከትሎም በደቂቃ 83 ሳንቲም የነበረው የሞባይል ስልክ ጥሪ አገልግሎት ወደ 50 ሳንቲም ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
ከዚህ ባለፈም ቀደም ሲል በሜጋ ባይት 35 ሳንቲም የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት 43 በመቶ ቅናሽ ተደርጎበት በሜጋ ባይት ወደ 23 ሳንቲም ዝቅ ብሏል።
በአጠቃላይ በሞባይል ኢንተርኔት ፓኬጆች ላይ ደግሞ ከ33 እስከ 44 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።
በሞባይል እና መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ላይም እስከ 54 በመቶ ቅናሽ መደረጉም ተገልጿል።
የብሮድባ
|
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 6.87 ቢሊዮን ብር አተረፈ
August 14, 2018 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 6.8 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡
የድርጅቱን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም አስመልክቶ ዓርብ ነሐሴ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም፣ አየር መንገዱ 10.6 ሚሊዮን መንገደኞችና 400,339 ቶን ጭነት እንዳጓጓዘ ተናግረዋል፡፡ ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የመንገደኞች ቁጥር በ21 በመቶ፣ የጭነት መጠን ደግሞ በ18 በመቶ እንዳደገ አስረድተዋል፡፡
የአየር መንገዱ ገቢ በ43 በመቶ ዕድገት በማሳየት 89.1 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ተገልጿል፡፡ አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ ስምንት ዓለም አቀፍና ሁለት የአገር ውስጥ መዳረሻዎችን እንደከፈተ ተነግሯል፡፡ ኩባንያው 14 አዲስ አውሮፕላኖች የተረከበ መሆኑን፣ በአዲሱ ዓመት 20 አዲስ አውሮፕላኖች እንደሚያስገባ ተገልጿል፡፡
‹‹አየር መንገዱ ይህን ውጤት ሊያስመዘግብ የቻለው የኩባንያው ማኔጅመንትና 13,000 ሠራተኞች ጠንክረው በመሥራታቸው ነው፤›&rsa
|
የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ ነው
January 23, 2018 - የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በምርቶቹ ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጎ ማከፋፈል መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአገሪቱ ውስጥ ቢራ ፋብሪካዎች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በማከፋፈያ ዋጋቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ቢጂአይ ግን ይህንን የዋጋ ጭማሪ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡
በዛሬው ዕለት ቢጂአይ የዋጋ ለውጡን ተግባራዊ መሆኑን የሚያረጋግጠው፣ በማከፋፈያ ዋጋ የሚረከቡ ሆቴሎች 214 ብር ያወርዱ የነበረውን አንድ ሳጥን ቢራ በ251 ብር መግዛታቸው ነው፡፡
በተመሳሳይ 590 ብር የሚያወርዱትን አንድ በርሚል ድራፍት በ700 ብር እንዲረከቡ መደረጋቸውን የተለያዩ ሆቴሎች ገልጸዋል፡፡
የቢራ ፋብሪካዎቹ ከሦስት ወራት በፊት የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ለጭማሪያቸው ምክንያት አድርገው የነበረው የውጭ ምንዛሪ ለውጥን ነበር፡፡ ሆኖም የፌዴራል የሸማቾች ጥበቃና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን ጭማሪው ምክንያታዊ አይደለም በማለቱ ዋጋው ወደነበረበት እንዲመለስ ተደርጎ ነበር፡፡ ፋ
|
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ዘቢዳር ቢራን ሊገዛ ነው
January 11, 2018 - በቅርቡ የራያ ቢራን አክሲዮኖች ለመጠቅለል ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ በተመሳሳይ መንገድ የዘቢዳር ቢራን አክሲዮኖች ለመግዛት ጫፍ መድረሱ ታወቀ፡፡
የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ ቢጂአይ ኢትዮጵያ የዘቢዳር ቢራን አክሲዮኖች ለመግዛት ባቀረበው ሐሳብ በመሠረት ከዘቢዳር ቢራ ዋነኛ ባለአክሲዮን ከሆነው የቤልጂሙ ዩኒቢራ ጋር በአክሲዮኖች ሽያጭ ላይ ሲደራደር ቆይቷል፡፡
ቢጂአይ የዘቢዳር ቢራ አክሲዮኖችን ለመግዛት ያቀረበው ዋጋ ለጊዜው ባይገለጽም፣ የራያ ቢራን አክሲዮኖች ለመግዛት ካቀረበው ዋጋ ጋር ተቀራራቢ እንደሚሆን ተሰምቷል፡፡ በሌላ በኩል ዘቢዳር ማምረት ከጀመረ በቅርቡ በመሆኑና የኢንቨስትመንት ወጪው ያነሰ ስለሆነ፣ ለአክሲዮኖች ግዥ የሚሰጠው ዋጋ ከራያ ቢራ ያነሰ እንደሚሆን እየተገለጸ ነው፡፡
ከሁለቱም ወገኖች የአክሲዮኖችን ሽያጭ በተመለከተ ለጊዜው መረጃ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ባይሳካም፣ በሽያጩ ላይ ግን ድርድር እየተደረገ መሆኑንና በሒደትም ስምምነት ላይ እየተደረሰ እንደሆነ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
|
ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሠራተኞች አድማ ሥራ አቆመ
January 7, 2018 - ደርባ ሚድሮክ ከታኅሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሠራተኞች አድማ ምክንያት ሥራ አቆመ፡፡ የደርባ ሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ እንደገለጹት፣ ስድስት ያህል ዓላማቸው ግልጽ ያልሆነ ሠራተኞች ለሌሎች ሠራተኞች ማስፈራርያ በመላክ ሥራ እንዲቆም አድርገዋል፡፡
‹‹የሲሚንቶ ምርት ቆሟል፡፡ በአጠቃላይ ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አቁሟል፡፡ በክምችት ያለውንም ምርት ለገበያ ማቅረብ አልተቻለም፤›› ሲሉ አቶ ኃይሌ ገልጸው፣ ‹‹ችግሩን ከወረዳውም ሆነ ከዞኑ ጋር በመነጋገር ለመፍታት ቢሞከርም ሊሳካ ግን አልተቻለም፤›› ሲሉ ደርባ ሚድሮክ የገጠመውን ችግር አስረድተዋል፡፡
የሥራ ማቆም አድማ ከመመታቱ በፊት የግዙፉ ደርባ ሚድሮክ ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ጠይቀው ነበር፡፡ በተለይ መንግሥት ብር ከዶላር ጋር ያለውን ምጣኔ በ15 በመቶ እንዲቀንስ በማድረጉ፣ ሠራተኞች 15 በመቶ ደመወዝ እንዲጨመርላቸው መጠየቃቸውን አቶ ኃይሌ ገልጸዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የ
|
ከተመዘኑት ሆቴሎች ውስጥ 45 በመቶ የሚሆኑት የደረጃ ምደባ መመዘኛን ማለፍ አልቻሉም
December 21, 2017 - በሀገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደውን የሆቴሎች ደረጃ መመዘኛ ተከትሎ በርካታ ሆቴሎች የብቃት መመዘኛ ደረጃዎችን ማለፍ አልቻሉም፡፡ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ማክሰኞ ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓም በሆቴሎች ደረጃ ምደባ ዙሪያ ከባለድርሻ አካለት ጋር ባደረገው ውይይት እንደተመለከተው አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ ክልሎች ያሉ 365 ሆቴሎች ተመዝነው ተገቢውን ደረጃ ማሟላት የቻሉት 198 ብቻ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 167 የብቃት ማረጋገጫውን ማለፍ ባለመቻላቸው ውጤታቸው ሊገለፅ ያልቻለ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በዚሁ ዙሪያ ሰፋ ያለ የጥናት ፅሁፍ ያቀረቡት በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪስት አገልግሎት የብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ደርበው፤ የሆቴሎች የደረጃ ምደባ በሀገር አቀፍ ደረጃ 365 ሆቴሎች የተመዘኑ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በአዲስ አበባና በክልሎች ደረጃውን አሟልተው ከአንድ እስከ አምስት ያለውን የሆቴል ኮከብ ደረጃ መውሰድ የቻሉት 198 ብቻ ናቸው፡፡
በዚህም በአዲስ አበባ ከተመዘኑት 139 ሆቴሎች ውስጥ ደረጃውን አሟልተው ከአንድ እስ
|
ኢትዮጵያ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች በየወሩ 10 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን ወደ ውጭ እየላከች ነው
December 8, 2017 - ከአምስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በየወሩ አስር ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ወደ ውጭ እየተላኩ መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ። ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ የላኩት በመንግስት የተገነቡት የሐዋሳና የቦሌ ለሚ ሲሆኑ በግል ባለኃብቶች የተገነቡት የምስራቅ፣ ጆርጅ ሹ እና ቦግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ናቸው።ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው ምርቶች ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው እሴት ያልተጨመረባቸው የግብርና ምርቶች ሲሆኑ የኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ ከአጠቃላይ የአገሪቱ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ ድርሻ ገና በነጠላ አሀዝ ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከአጠቃላይ ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ የኢንዱስትሪውን ድርሻ 25 በመቶ በማድረስ ወደ ውጭ አገራት ከምትልካቸው ምርቶች ውስጥ 50 በመቶ ያህሉን ከማምረቻ ኢንዱስትሪው የመላክ እቅድ አስቀምጣ እየተንቀሳቀሰች ነው።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለተቀመጠው እቅድ ስኬት ተስፋ እንደተጣለባቸው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር በላቸው መኩሪያ ለኢዜአ እንዳሉት ለዚህ ግብ
|
የንግድ ሕግ የሚያሻሽል አዲስ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ
December 3, 2017 - ከ1952 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ የሚገኘውን የንግድ ሕግ የሚያሻሽል አዲስ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን፣ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በተጨማሪም ከ1954 ዓ.ም. ጀምሮ በተግባር ላይ የቆየውንና ተሞክሮ በተደጋጋሚ ውድቅ ተደርጎ የነበረው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉንም ለማሻሻል፣ ድጋሚ ማሻሻያ ረቂቅ ሕግ መቅረቡንም ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ረቡዕ ኅዳር 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት የመሥሪያ ቤታቸውን የሩብ ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ ሕጎች ላለፉት አምስት አሠርት ዓመታት ሳይሻሻሉ ከቀሩት አምስት በላይ ሕጎች መሠረታዊ (ኮዶች) የሚካተቱ ሲሆን፣ ለምን ይህን ያህል ጊዜ እንደቆዩ ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ከተነሱላቸው ጥያቄዎች ውስጥ ይገኙበታል፡፡
ለጥያቄዎቹ ማብራርያ የሰጡት ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ፣ እነዚህ ሕጎችን ለመከለስ ወይም ለማሻሻል እንደ መደበኛ አዋጆች ቀላል ባለመሆናቸውና የመንግሥት ውሳኔና የፖሊሲ ለውጥ የሚፈልጉ በመሆናቸው ነው ብለ
|
ብሄራዊ ባንክ የወርቅ ዋጋ የ30 ቀናት የዋጋ መምረጫ ማበረታቻ ዳግም ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ
December 2, 2017 - የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የወርቅ ዋጋ መውረድን ተከትሎ አንስቶ የነበረውን የ30 ቀናት የዋጋ መምረጫ ማበረታቻ ዳግም ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
በክልሎች በተከፈቱ የወርቅ ግዥ ማዕከላት አቅራቢዎች የተሻለ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውንም ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ፤ ባንኩ ነጋዴዎቹን ለማበረታታት ወርቅ ለግብይት በቀረበበት ወር ያለውን የክፍያ ዋጋ መሰረት በማድረግ ሰፊ የመምረጫ ጊዜ ሲሰጥ እንደነበር አስታውሷል፡፡
ይህም የወርቁን ትክክለኛ ዋጋ የማያሳይና ባንኩን ለከፍተኛ ወጪ ሲዳርግ መቆየቱን አመልክቷል፡፡የዚህ ዓይነቱ አሰራር እንዲቀር መደረጉን ያወሳው የባንኩ መግለጫ፤ በተለያዩ ምክንያቶች የወርቅ አቅርቦት እየቀነሰ በመምጣቱ መንግስት አቅራቢዎችን በማበረታታት ከዘርፉ መገኘት የሚገባውን አገራዊ ጥቅም ለማሳደግ መወሰኑን አውስቷል።
በዚህም ብሄራዊ ባንኩ አገራዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የ30 ቀናት የዋጋ መምረጫ ማበረታቻውን እንደገና ተግባራዊ ማድረጉን ገልጿል፡፡
እንዲሁም ባንኩ የወርቅ ግዥ የሚፈጽመ
|
በብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ የተደረገው ማስተካከያ መድሃኒት አቅራቢ ደርጅትና የመንግስት ተቋማትን እያወዛገበ ነው
November 21, 2017 - በብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ማስተካከያ መደረጉ መድሃኒቶችን ለማቅረብ ጨርታ ያሸነፉ የግል ድርጅቶች እና የመንግስት ተቋማትን በማወዛገብ ላይ ነው።
ቅሬታቸውን ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ያቀረቡት የኦፕቲማ ፋርማሲዩቲካል ትሬዲንግ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮናታን እስጢፋኖስ፥ የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም ከመደረጉ በፊት ለጨረታ ባስገቡት የገንዘብ መጠን የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ያነሳሉ።
ይሁንና የብር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ መዳከሙ እየታወቀ ከዚህ በፊት በነበረው ዋጋ የውል ስምምነት ልንፈፅም አይገባም የሚል ቅሬታ ያቀርባሉ።
ኬቲ ህይወት ሜዲካል የግል ማህበር ባለቤት አቶ ተገኝ ወርቁም በተመሳሳይ፥ ባሸነፍነው ጨረታ የውል ስምምነቱን እንዳንፈፅም አሁን ያለውን የገበያ ሁኔታ ያገናዘበ አይደልም ሲሉ ያክላሉ።
የውል ስምምነቱን ብንፈፀም በዓለም ገቢያ ያለው የመድሃኒት ዋጋ በጨረታ ካቀረብነው ጋር የሚጣጣም አይደለም፤ ስምምነቱን ካልፈፀምን ደግሞ በጨረታው ለመሳተፍ ያስያዝነው ሁለት በመቶ የጠቅላላ ዋጋ በመንግስት ተቋማት
|
የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ ሆነ ብለው ምርት የደበቁ የ39 ነጋዴዎች መጋዘኖች ታሸጉ
October 29, 2017 - በአዲስ አበባ ከተማ የብር ውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ የተለያዩ ምርቶችን የለም በማለት ያለአግባብ ያከማቹ 39 ነጋዴዎች መጋዘኖች መታሸጋቸው ተገለፀ።
ከእነዚህ 39 ነጋዴዎች መካከል ስምንቱ ከፍተኛ አስመጪ ነጋዴዎች መሆናቸውን የአዲስ አባባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።
ከአስመጪዎች መካከል የብእርና የአገዳ ሰብሎች አስመጪ ሚፍታህ አብዱራሃማን፣ እስማኤል ፒ.ኤል.ሲ፣ ሙክታር አብዲ፣ ይልማ አግሪ ቢዝነስ እና መንሱር ሽፋ ይገኙበታል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አማካሪ አቶ መከታ አዳፍሬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ቢሮው ከጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከአጋር አካላት ጋር ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር ነው መጋዘኖቹ የታሸጉት።
በታሸጉ መጋዘኖች ውስጥ የኢንዱስትሪ፣ የኮንስትራክሽን፣ የግብርና ምርቶች ማለትም 40 ሺህ ኩንታል ሩዝ፣ 200 ሺህ ኩንታል ዛላ በርበሬ፣ 30 አይሱዙ ተሽከርካሪ፣ የታሸጉ የለስላሳ መጠጦች እና በርካታ የህጻናት ንፅህና መጠበቂያዎች ይገኙበታል።
|
ኢትዮጵያ በሩብ ዓመቱ ወደ ውጪ ከተላከ ቡና 215 ሚሊየን ዶላር አገኘች
October 28, 2017 - 2010 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ ቡና 215 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ልማት ግብይት ባለስልጣን ገለፀ።
ገቢው በሩብ ዓመቱ ወደ ውጭ ከተላከ 55 ሺህ 825 ቶን የቡና ምርት የተገኘ ሲሆን፥ በባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው ገቢ የ34 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብልጫ አለው ተብሏል።
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትለከው ምርት 25 በመቶውን ገቢ የምታገኘው ከቡና ምርት መሆኑን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ሀገሪቱ ቡናን ለዓለም ገበያ ከሚያቀርቡ አምስት ሀገራት አንዷ ብትሆንም፥ ከዘርፉ ያቀደችውን ያህል ጥቅም አግኝታ አታውቅም።
በሩብ ዓመቱ 56 ሺህ 550 ቶን ቡናን ለዓለም አቀፍ ገቢያ በማቅረብ እስከ 245 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ቢታቀድም 215 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ብቻ ነው ማሳካት የተቻለው።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማት ግብይት ባለስልጣን የገበያ ልማትና ቁጥጥር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር፥ ከባለፈው ዓመት አፈጻጸም ጋር ያለውን ልዩነት በማሳያነት ጠቅ
|
ከኬንያ ድንበር የተመለሰው ስኳር ለአገር ውስጥ ገበያ ሊቀርብ ይችላል ተባለ
October 11, 2017 - ወደ ኬንያ ኤክስፖርት ለማድረግ ታስቦ ሞያሌ ድንበር ደርሶ የነበረው 4,400 ቶን ስኳር፣ ለአገር ውስጥ ገበያ እንዲቀርብ ሊወሰን እንደሚችል ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተገለጸውን መጠን ስኳር አግሪኮሞዲቲስ ኤንድ ፋይናንስ ለተባለ ኩባንያ ከሸጠ በኋላ፣ ኩባንያው ወደ ኬንያ የሚገባበትን ሁኔታዎች ባለማመቻቸቱ በሞያሌ ድንበር በእርጥበታማ ሙቀት ለሁለት ወራት በተሽከርካሪዎች ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡
ይህንን ስኳር ኩባንያው መረከብ ባለመቻሉ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ስኳሩን የጫኑ 110 ተሽከርካሪዎች ወደ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ እንዲመለሱ ተወስኖ፣ በጉዞ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ስኳሩ ከተመለሰ በኋላ ምን ይሆናል የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽኑ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉም፣ የስኳሩ መጠንና ያለበት የጥራት ደረጃ ከተፈተሸ በኋላ ለአገር ውስጥ ገበያ እንዲቀርብ ሊወስን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
ግዥውን የፈጸመው ኩባንያ የፈረመው የግዥ ውል ‹‹ፋክተሪ ኤግዚት›&rsa
|
ለገቢ ንግድ የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ አስመጪዎች እጅ ለማላቀቅ 215 የክልል አስመጪዎች ተመለመሉ
September 19, 2017 - መንግሥት ለገቢ ንግድ በየዓመቱ የሚፈቅደውን የውጭ ምንዛሪ ከተወሰኑ የአዲስ አበባ አስመጪዎች እጅ ውስጥ ለማስለቀቅ፣ 215 የክልል አስመጪዎችን መመልመሉ ተሰማ፡፡
የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት አስመጪዎቹ የተመለመሉት ከመቐለ፣ ከባህር ዳር፣ ከጅማና ከሐዋሳ ከተሞች ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት የአስመጪነት ንግድ በተወሰኑ የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ውስጥ በመውደቁና ይህም የጎንዮሽ የዋጋ አሻጥር መፍጠር እንዲችሉ እንዳደረጋቸው፣ የአገሪቱን ውስን የውጭ ምንዛሪም በብቸኝነት እንዲቀራመቱ እንዳስቻላቸው የንግድ ሚኒስቴር የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍና አዲስ አበባ ላይ የተወሰነውን የአስመጪነት ንግድ ለመበተን ሲባል፣ ከተመረጡ የክልል ከተሞች ባለሀብቶችን በመመልመልና በማሠልጠን መንግሥት በ2010 ዓ.ም. ወደ ትግበራ እንደሚገባ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ባለሀብቶችን ለመምረጥ የንግድ ሚኒስቴር የተለያዩ መሥፈርቶችን የተጠቀመ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ዋነኞቹ በሕገወጥ ንግድ ያልተሳተፈና ካፒታሉ ተዓማኒነት ያለው የሚሉ ናቸው፡፡
ለሙ
|
ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ስኳር ኤክስፖርት አደረገች - ስኳር ኮርፖሬሽን
September 1, 2017 - የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ከተቋቋመ ከ2003 ዓ.ም. ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ስኳር ኤክስፖርት ተደረገ፡፡ መንግሥት ከኬንያ መንግሥት የቀረበለትን ጥያቄ በመቀበል ለስኳር ኮርፖሬሽን በሰጠው መመርያ መሠረት 43 ሺሕ ኩንታል ስኳር ወደ ኬንያ ተልኳል፡፡ስኳር ኮርፖሬሽን በ2003 ዓ.ም. ከመቋቋሙ በፊት የአውሮፓ ኅብረት ለታዳጊ አገሮች ከጦር መሣሪያ በስተቀር የሚያመርቱትን ምርት ከቀረጥ ነፃ እንዲልኩ በሚሰጠው ዕድል፣ ኢትዮጵያ ያላለቀለት ስኳር ወደ አውሮፓ ትልክ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ከዚያ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ ስኳር ወደ ውጭ መላከ ከማቋረጧም በላይ፣ በአገር ውስጥም ከፍተኛ የስኳር እጥረት በመከሰቱ እስከ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ድረስ ከውጭ ስታስገባ ቆይታለች፡፡የስኳር ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ከኬንያ መንግሥት በቀረበላት ጥያቄ መሠረት 43 ሺሕ ኩንታል ስኳር ወደ ውጭ ልካለች፡፡
‹‹የኬንያ መንግሥት ጥያቄ የመጣው ኮርፖሬሽኑ በጥሩ ዋጋ ኤክስፖርት ለማድረግ፣
|
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ተጠሪነት ወደ ንግድ ሚኒስቴር ተዛወረ
April 21, 2017 - የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ተጠሪነት ወደ ንግድ ሚኒስቴር እንዲዛወር ወሰነ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 27ኛ መደበኛ ጉባዔ በሁለት አዋጆችና ሶስት ደንቦች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን ተጠሪነት የተቀየረበት ዋነኛ ምክንያትም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ከጉዳዩ ጋር አግባብ ካላቸው የዘርፉ መስሪያ ቤቶች ጋር ለማቀናጀት እንዲያመች መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርት ገበያና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ካፒታልን ለማሳደግ የቀረበውን ጥያቄ የተቀበለ ሲሆን ለማሻሻያ የቀረቡ ረቂቅ ደንቦች በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው እንዲወጡና በስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል።
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ግብርና ምርቶች መጋዘን አገልግሎ
|
የኢትዮጵያ ቱሪዝም መለያው ˝ምድረ ቀደምት˝ መሆኑ አስታወቀ
March 22, 2017 - የኢትዮጵያ ላንድ ኦፍ ኦሪጅን በሚል የተዋወቀው የኢትዮጵያ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የአማርኛ ትርጉሙ ˝ምድረ ቀደምት˝ በሚል ተተርጉሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ይፋ መደረጉ ፋና ዜና ዘገበ።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ በየጊዜው የሚነሱ ተመሳሳይ ችግሮችን ለመፍታት አሁንም ከፍተኛ ትኩረትና የቅንጅት ስራ እንደሚያስፈልግ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም ባቀረቡት ሪፖርት ተጠቅሷል።
በቱሪዝም ድርጅት በኩልም በተመሳሳይ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የገበያ እና የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በመዳረሻ ቦታዎች የመግቢያ ክፍያዎች፣ በመስተንግዶና በአገልግሎት ደግሞ በድንገት የዘፈቀደ ጭማሪዎች መኖር እንደሁም ተመሳሳይነት ያለው የመሬት አቅርቦት በየክልሎችና መዳረሻዎች አለመኖር በክፍተት ተነስቷል።
ከምክር ቤቱ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል።
ከእነዚህም መካከል ዘርፉን በማስተዋወቅ ስራውም ሆነ ሌሎች ስራዎች በሚፈለ
|
ንግድ ሚኒስቴር የንግድ ምክር ቤቱን ጠቅላላ ጉባዔ አገደ
February 2, 2017 - የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ሊያካሂደው የነበረው ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ፣ ላልተወሰነ ጊዜ ታግዶ እንዲቆይ ንግድ ሚኒስቴር ውሳኔ ላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡
ለተከታታይ ወራት ውዝግብ ሲፈጥር የነበረው በንግድና ምክር ቤት ውስጥ እየታየ ያለው የሕግ ጥሰትና ተፈጸሙ የተባሉ ሕገወጥ ተግባራት እስኪጣሩ ድረስ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ሊካሄድ የነበረው ጉባዔና ምርጫ እንዲታገድ የተወሰነው ማክሰኞ ጥር 23 ቀን 2009 ዓ.ም. መሆኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ንግድ ሚኒስቴር እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ ቀደም ብሎ በንግድ ምክር ቤቱ አንዳንድ አባላት መረጃዎች ሲቀርብለት የነበረ ቢሆንም፣ ጣልቃ ላለመግባትና ጉዳዩ በንግድ ምክር ቤቱ እንዲቋጭ ሲመክር መቆየቱ ይታወሳል፡፡
የንግድ ሚኒስቴር ደብዳቤ ጥር 30 ቀ
|