የቻይናው አሊባባ በኢትዮጲያ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሊጀምር ነው
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 27, 2019 (Ezega.com) -- የቻይናው ቁጥር አንድ ቢሊየነር እና የአሊባባ መስራች ጃክ ማ ከጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድ በቀረበለት ግብዣ መሰረት በኢትዮጲያ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡ ኩባንያው ካለው እጅግ የገነነ ዓለም አቀፍ እውቅና እና ስኬት አንጻር ጉብኝቱ በተለይ ሀገሪቱ የናፈቀችውን ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ለማስፋፋት አቋራጭ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ብዙዎች ተስፋ አድርገዋል፡፡
ተስፋውን ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየር ያስችላል የተባለለት ስምምነትም በኢትዮጲያ እና በአሊባባ ኩባንያ መካከል በአዲስ አበባ ተፈርሟል፡፡ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንሰትሩ ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና በአሊባባ ኩባንያ ተወካይ አማካኝነት የተፈረመው ስምምነት ዓለም አቀፍ የኤሊክትሮኒክ ግብይትን በኢትዮጲያ ለመጀመር የሚያስችል መሆኑ በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ በመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ የፊርማ ስነስረዓት ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ እንዳሉት የተደረሰው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትብብር ስምምነት ኢትዮጲያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ከአፍሪካ ከቀዳሚዎቹ 5 ግዙፍ ኢ
|
35 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ የዳያስፖራ አባላት የንግድና ኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስዱ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 18, 2019 (Ezega.com) -- በተያዘው 2012 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺህ 32 በላይ ዳያስፖራዎች ከ 35 ቢሊዮን ብር የሚልቅ የካፒታል መጠን አስመዝግበው የንግድና ኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ይህንን ያለው ከፌዴራልና ከሁሉም ክልሎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ ባደረገው ውይይት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት እና የቀጣይ ጊዜያት እቅዶች ላይ ለተሰብሳቢው ማብራሪያ ሰጥተዋል። እንዲሁም የኤጀንሲው የክልል ዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች እና የዳያስፖራ ማህበራት የበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል። በኤጀንሲው የዳያስፖራ ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ አውላቸው ማስሬ እንዳብራሩት በተያዘው ዓመት በቁጥር በርካታ የሆኑ ዳያስፖራዎች በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ዘርፎች የጎላ ተሳትፎ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማ
|
በትውልደ ኢትዮጵያውያን በመድንና በፋይናንስ ዘርፍ እንዲሰማሩ ተፈቀደ
ኢዜጋ ሪፖርተር
November 5, 2019 (Ezega.com) -- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በመድን እና በአነስተኛ ፋይናንስ ዘርፍ እንዳይሰማሩ የሚከለክለውን ህግ አነሳ፡፡ ምክር ቤቱ በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው የመድን እና የአነስተኛ ፋይናንስ ስራ አዋጅን ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ያጸደቀው በሙሉ ድምጽ ነው፡፡
አዋጁ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በመድን እና በፋይናንስ ስራ ላይ እንዳይሳተፉ የተጣለውን የህግ እገዳ በማንሳት በዘርፉ መዋእለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚፈቅድ መሆኑን ታውቋል። የገቢ፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያትተው አዋጁ ትውልደ ኢትዮጲያውያን በሀገራቸው ኢኮኖሚ ውስጥ ገብተው የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ያግዛል፡፡
አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የሚመሰርቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ ከተዘረዘሩት ስራዎች በተጨማሪ በዲጂታል ዘዴዎች የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት፣ የወኪል ባንኪንግ፣ የሐዋላ እና ከወለድ ነጻ አነስተኛ የፋይናንስ ስራ ላይ እንዲሰማሩ ተፈቅዷል፡
|
የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ታገደ
May 10, 2018 - የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን የኢፌዴሪ የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን ሚድሮክ ጎልድ በለገደምቢ በሚያካሂደው የወርቅ ማዕድን ልማት ስራ ላይ የአካባቢው ነዋሪ፥ የኩባንያው የምርት ሂደት የአካባቢ ብክለት እያስከተለ ነው የሚል ቅሬታ ማንሳቱን ተከትሎ ነው ፍቃዱን ያገደው።
በገለልተኛ አካል ጥልቀት ያለው ጥናት እስከሚጠና ድረስ የኩባንያው ወርቅ የማምረት ስራው መታገዱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ጥናቱ በገለልተኛ አካል ከፌደራል እስከ ቀበሌ ያሉ አመራሮችን እና ባለ ድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እንደሚካሄድ፥ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ባጫ ፋጂ ተናግረዋል።
የኩባንያው ወርቅ የማምረት ሂደት መቀጠል ያለመቀጠል ሂደትም በጥናቱ ውጤት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
Source:
|
መንግሥት የትምባሆ ድርጅት ላይ የነበረውን ድርሻ በ434 ሚሊዮን ዶላር ሙሉ በሙሉ ሸጠ
December 21, 2017 - መንግሥት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ላይ የነበረውን የ30 በመቶ ድርሻ ሙሉ በሙሉ ጃፓን ቶባኮ ለተባለ ኩባንያ በ434 ሚሊዮን ዶላር አስተላለፈ፡፡ ክፍያው ዛሬ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ገዥው ኩባንያ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ይህ ሽያጭ ኩባንያው በድርጅቱ ላይ ያለውን ድርሻ ወደ 70 በመቶ አሳድጓል፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል የመንግሥት ልማት ድርጅት ሚኒስትሩ አቶ ግርማ አመንቴ ከጃፓን ቶባኮ ኩባንያ ተወካይ ጋር ተፈራርመዋል፡፡
ከብሔራዊ ትምባሆ ቀሪ ድርሻዎች 29 በመቶው ሼባ በተባለ የየመን ድርጅት ባለቤትነት ሥር ያለ ሲሆን፣ ቀሪው አንድ በመቶ በአንድ ግለሰብ ተይዟል፡፡
ምንጭ.:ሪፖርተር
|
ኤ ቲ ኤም ካርድ በመጠቀም ወቅት በስህተት ገንዘብ የሚወስድባቸው ኢትዮጵያውያን ምሬታቸውን ገለፁ
October 15, 2017 - በኤ ቲ ኤም ካርድ ገንዘብ በማውጣቱ ሂደት በስህተት ከባንክ ሂሳባቸው የሚወሰድ ገንዘብ በአግባቡ እና በፍጥነት እየተመለሰልን አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች አማረሩ። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው ከሆነ ከሚያጋጥም የኔትወርክ መቆራረጥ እና ካርድ ማስቀረት በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች ያዘዙትን ገንዘብ የማይቀበሉበት እና ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ የሚቀንስበት ሁኔታ ያጋጥማቸዋል።
በእነዚህ ችግሮች ሂደት ውስጥ በስህተት ከሂሳባቸው የሚቀነስ ገንዘብ በአግባቡ እና በፍጥነት እየተመለሰላቸው አለመሆኑን ነው የገለፁልን። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ካነጋገራቸው ደንበኞች መካከል ከሳምንት እስከ አንድ ወር ለሚደርስ ጊዜ ገንዘባቸው ሳይመለስላቸው የቆዩ እንደሚገኙም መታዘብ ችሏል። ስለጉዳዩ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ በልሁ ታከለ፥ የባንኩ ደንበኛ ሆነው በሌሎች ንግድ ባንኮች ኤቲኤም ተጠቅመው ገንዘባቸው ለሚቆረጥባቸው ደንበኞች ምላሽ ለመስጠት ሂሳብ የማጥራት ስራ በየቀኑ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ነገርግን አንዳንድ ጊዜ ደንበኞች የተጠቀሙበትን የየት
|
ቤተ-ክህነት ዋና ባለድርሻ የሆነችበት አዲስ ባንክ በምሥረታ ላይ ነው ተባለ
October 8, 2017 - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ቤተ ክህነት) ባለድርሻ የሆነችበትና ተጨማሪ 18 ባለድርሻዎች የተካተቱበት ባንክ ለመመሥረት ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቃቸው ተሰማ፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት ባንኩን ለመመሥረት ከፍተኛ አማካሪዎች ሁኔታዎችን ሲያመቻቹና የአመሠራረቱ ሁኔታ በልዩ ሚስጥር ሲካሄድ ቆይቶ፣ የድርሻው መጠንና የመሥራቾች ብዛት መወሰኑን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት አዲስ የሚመሠረተው ባንክ ባለድርሻዎች ብዛት 22 ሲሆን፣ እያንዳንዱ ባለድርሻ አንድ መቶ ሚሊዮን ብር ድርሻ እንዲኖረውና ጠቅላላ መመሥረቻ ካፒታሉ 2.2 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ውሳኔ ላይ መደረሱንም ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ቤተ ክህነት በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ ባሉ አራት ድርጅቶች አማካይነት የአራት መቶ ሚሊዮን ብር ድርሻ የሚኖራት ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 18 ባለድርሻዎች ደግሞ የአንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሚሊዮን ብር ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ ባለድርሻዎቹ ለምሥረታው 25 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ፈጽመው፣ ቀሪውን ወደፊት በሚወሰነው የጊዜ ሰሌዳ መሠረ
|
የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ለታዳሽ ኃይል ልማት አንድ ቢሊዮን ብር መደበ
October 5, 2017 - በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ የታዳሽ ኃይል ልማት ፕሮጀክቶች የአውሮፓ ኅብረት የአንድ ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ፡፡
ማክሰኞ መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተከፈተው የታዳሽ ኃይል ልማት ጉባዔ ንግግር ያደረጉት የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ዩሃን ቦርግስታም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የታዳሽ ኃይል ልማት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ልማት ዋና አካል አድርጎ መቅረፁን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የኢንዱስትሪ ልማት የኃይል አቅርቦት ወሳኝ ሚና እንዳለው የገለጹት ሚስተር ቦርግስታም፣ መንግሥት ለታዳሽ ኃይል ልማት ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ 90 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል የምታመነጨው ከውኃ ኃይል ነው፡፡ የተለያዩ የንፋስ፣ የፀሐይና የጂኦተርማል ልማት ፕሮጀክቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ በታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ በአርዓያነት ልትጠቀስ የምትችል አገር ናት፤›› ብለዋል፡፡
ሚስተር ቦርግስታም የአውሮፓ ኀብረት በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ለኢትዮጵያ ትልቅ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ እ
|
ሐዋሳ፣ ቦሌ ለሚና ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርኮች 248 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኙ - ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
September 15, 2017 - የሐዋሳ ፣ ቦሌ ለሚና ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርኮች 248 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘታቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለፀ።ከዚሁ ገቢ 200 ሚሊዮን ዶላር ያስገኘው ስራ ከጀመረ አራት ወራትን ያስቆጠረው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ነው። በውስጡ 52 ፋብሪካዎችን የያዘው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በግዙፍነቱ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሲሆን ከዓለም ግዙፍ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች መካከልም ይጠቀሳል።
ቦሌ ለሚና ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርኮችም በ2009 በጀት ዓመት እያንዳንዳቸው 24 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አስገኝተዋል።
ፓርኮቹ ከ31 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎችም አዲስ የሥራ ዕድል ፈጥረዋል። ኢትዮጵያን በ2017 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ በሚደረገው ጥረት ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች ላይ በስፋት እንደሚሰራ ኮሚሽነር ፍጹም አመልክተዋል።
የግብርናና ምርቶች ፣ ማኑፋክቸሪንግ ፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ጫማና የቆዳ ውጤቶች ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዘርፎች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
"በእነዚህ ዘርፎች ጠንክረ
|
ዳንጎቴ ሲሚንቶ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ዕርቅ አወረደ
September 14, 2017 - በ2008 እና በ2009 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ተቀጣጥሎ በነበረው ሕዝባዊ አመፅ ሳቢያ ሁለት ጊዜ ንብረቶቹ የተጎዱበት ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የ2010 ዓ.ም. ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የዋዜማ ድግስ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ዕርቅ አወረደ፡፡
ቅዳሜ ጳጉሜን 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ 85 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳበርጋ ወረዳ፣ ልዩ ስሙ ረጂ በተባለ አካባቢ በሚገኘው ግዙፉ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ፍሪዳዎች ተጥለው፣ የተለያዩ መጠጦች ቀርበው የአገር ሽማግሌዎች በተገኙበት፣ የድርጅቱ ማኔጅመንትና ሠራተኞች የአዲስ ዓመት አቀባበል በዓል ባከበሩበት ሥነ ሥርዓት ላይ የዕርቅ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡
በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ዲፕ ካማራ በሥራ ላይ ብዙ አለመግባባቶችና ግጭቶች መፈጠራቸውን አስታውሰው፣ ይህን ሁሉ ተቋቁሞ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ኢትዮጵያ በየዕለቱ እያደገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
‹&lsaq
|
ለግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ተጠየቀ
August 27, 2017 - ለግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክን 12 ቢሊዮን ብር ብድር መጠየቁን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ልማት ባንክ በበኩሉ የቀረበልኝን የብድር ይሰጠኝ ጥያቄ በመፈተሽ ላይ ነኝ በቅርቡ ምላሽ እሰጣለሁ ብሏል። በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የግብርና ምርቶች ባለባቸው አካባቢዎች 17 የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት ዕቅድ የተያዘ ቢሆንም በያዝነው ዓመት መጋቢት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በይርጋለም ፣ቡልቡላ ፣ ቡሬና ባዕኸር ላይ የአራቱን ፓርኮች የግንባታ መሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸው ይታወቃል።
የፓርኮቹ የመጀመርያው ምዕራፍ ግንባታ በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ በወቅቱ የፓርኮቹ መሰረተ ድንጋይ ሲቀመጥ መዘገባችን የሚታወስ ነው። ይሁንና ፓርኮቹን በተያዘላቸው ጊዜ ይጠናቀቃሉ ቢባልም እስካሁን ግንባታቸው አልተጀመረም፡፡
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴሩ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች ትራንስፎርሞሽን ዳሬክተር አቶ ሁነኛው አበባው ጉዳዩን አስመልክቶ እንዳሉት የአዋጭነት ጥናት፣ዲዛይ
|
መስፍን ኢንዱስትሪያል በውቅሮ ያቋቋመውን የትራክተር መገጣጠሚያ አስመረቀ
July 24, 2017 - መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪን ኩባንያ በውቅሮ ከተማ ያቋቋመውን የትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ትናንት አስመርቋል።የኩባንያው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍተ ሓዱሽ በወቅቱ እንደገለፁት ፋብሪካው በወር 240 ትራክተሮችን የመገጣጠም አቅም አለው።
''ሶናሊካ'' ከተባለው የህንድ ኩባንያ ጋር በመተባበር በፋብሪካው የሚገጣጠሙ ትራክተሮች ከ20 እስከ 110 የፈረስ ጉልበት ያላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
የትግራይ መልሶ ማቋቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍን በበኩላቸው፥ "በትግራይ መልሶ ማቋቋም ስር የሚገኙ ተቋማት ሀገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት እየደገፉ ናቸው" ብለዋል። ተቋማቱ ከተለያዩ የውጭ ኩባንያዎች ጋር በሚፈጥሩት ትብብር፥ የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን ለማጎልበት አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኪሮስ ቢተው፥የትራክተር መገጣጠሚያ የክልሉ አርሶ አደሮችን የቆየ ዘመናዊ ማረሻ ይቅረብልን ጥያ
|
ዳንጎቴ ከኢትዮጵያ ሊወጣ እንደሚችል አስጠነቀቀ
November 23, 2017 - ንብረትነቱ የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር የሆኑት የናይጄሪያዊ አሊኮ ዳንጎቴ የሆነው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ፋብሪካውን ሊዘጋ እንደሚችል አስጠነቀቀ፡፡
የፋብሪካው አመራሮች ይህንን የተናገሩት ፋብሪካው የሚገኝበት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የስሚንቶ ፋብሪካዎች ለስሚንቶ ማምረት ግብዓትነት የሚውለውን ፑሚስ የተባለ ማዕድን ማምረቻ ለወጣቶች ማስረከብ እንዳለባቸው ካዘዘ በኋላ ነው፡፡
ተቀማጭነታቻው ሌጎስ የሆነው የድርጅቱ ዳይሬክተር ኤድዊን ዴቫኩማር እንዳሉት ከሆነ በህንፃም ሆነ በመሳሪያ አያያዝ ላይ የሚፈጥሩ ጥቃቅን ስህተቶች ጠቅላላ የፋብሪካውን ስራ ሊያቃውሱ ይችላሉ፡፡‘ይህ ግልፅ የሆነ የመብት ጥሠት ነው፡፡ መንግስት አንዴ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ ሠጥቶናል፡፡ እኛ በምንፈልገው መጠን የኖራ እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ካላገኘን ፋብሪካው ስራውን ማከናወን አይችልም ’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ በዚህ ሳምንት ለፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥያቄ
|
ፎርብስ 5 ቀዳሚ የኢትዮጵያ ቢሊየነሮችን ይፋ አደረገ
June 17, 2017 - በየአመቱ የዓለም ባለፀጎችን የሃብት መጠን በማጥናት ደረጃቸውን ይፋ የሚያደርገው ፎርብስ መፅሄት ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ 5 የኢትዮጵያ ቢሊየነሮችን የሃብት መጠንና ደረጃ ከተሰማሩባቸው የንግድ ዘርፎች ጋር አወጣ ፡፡
በዚህም መሠረት ከ5ቱ ኢትዮጵያ ቁንጮ ባለሃብቶች መካከል በቅባት እህሎች ንግድ ላይ የተሠማሩት አቶ በላይነህ ክንዴ ከ60 ሚሊዮን ዶላር (1.3 ቢሊየን ብር) በላይ በማስመዝገብ ቀዳሚው ቢሊየነር ሊሆኑ በቅተዋል፡፡ በዚህ የቢሊየነሮች ዝርዝር ውስጥ አንዲት ሴት ባለፀጋም ተካተዋል፡፡ በ5ተኛ ደረጃ ላይ የሰፈሩት ወ/ሮ አኪኮ ስዩም አምባዬ ፤ ኦርቼድ ቢዝነስ ግሩፕ በተኘው ግዙፍ የኮንስትራክሽን ኩባንያቸው ፤ ከ50 ሚሊዮን ዶላር (1.1 ቢሊየን ብር) በላይ አካብተዋል ብሏል -ፎርብስ፡፡
በዚህ ዝርዝር ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አቶ በላይነህ ክንዴ የሃብት ምንጫቸው የግብርና ውጤት የሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ንግድ ሲሆን በ1997 ዓ.ም በተመሠረተው "በላይነህ ክንዴ አስመጪና ላኪ" በተሠኘው ኩባንያቸው አማካይነት በአመዛኙ በቅባት&nbs
|
የኢንዱስትሪ ፓርኩ ግንባታ ወደ ሦስተኛ ምዕራፍ ተሸጋግሯል
April 21, 2017 - የኢትዮ-ቻይና ኋጂዬን ዓለም አቀፍ የቀላል ኢንዱስትሪ ግንባታ ወደ ሦስተኛ ምዕራፍ መሸጋገሩ የኋጂዬን ግሩፕ ፕሬዚዳንት ዃሮን ጇን ገለጹ።
በጫማ ምርት የተሰማራው ኋጂዬን ግሩፕ በመስኩ የበቁ ኢትዮጵያዊያን ሙያተኞችን ለማፍራት በቻይና ሥልጠና እየሰጠ ነው።
ፕሬዚዳንቱ ዃሮን ጇን ለኢዜአ እንደገለጹት በአንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እየተካሄደ ያለው የኢትዮ-ቻይና ኋጂዬን የተቀናጀ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል።
ከሁለት ዓመት በኋላ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው የኢንዱስትሪ ፓርኩ ወደ ሦስተኛ ምዕራፍ ግንባታ መሸጋገሩን ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት።
በአዲስ አበባ 137 ነጥብ 8 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ ያለው የኢትዮ-ቻይና ኋጂዬን የተቀናጀ የኢንዱስትሪ
|
የኢትዮጵያ ባንኮች ለመረጃ መንታፊዎች ተጋላጭ መሆናቸው ተገለጸ
April 11, 2017 - የኢትዮጵያ ባንኮች ለመረጃ መንታፊዎች ተጋላጭ መሆናቸውን ካስፐርስኪ የሚባል የሩሲያ ኩባንያ አስታወቀ ሲል ረፖርተር ገለጸ፡፡ ተቀማጭነቱን በሩሲያ ያደረገው ካስፐርስኪ የተባለው ዓለም አቀፍ የመረጃ መረብ ደኅንነትና የኮምፒዩተር ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሮችን በማቅረብ የሚታወቀው ኩባንያ፣ ከሰሜን ኮሪያ መንግሥት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በሚነገርላቸው ላዛሩስ በሚባል ስያሜ ለሚጠሩ ዓለም አቀፍ የመረጃ መንታፊዎች ተጋላጭ ናቸው ብሏል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሦስት የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ባንኮች በመረጃ መንታፊዎች ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነና ተጨማሪ ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችልም አስጠንቅቋል፡፡
በቅርቡ ኩባንያው ባወጣው ሪፖርት ተከታታይ የሆኑ የመረጃ መንታፊዎች ጥቃቶች 18 አገሮች ውስጥ በሚገኙ የገንዘብ ተቋማት ላይ እንዳነጣጠሩ ገልጿል፡፡ ከእነዚህም መሀል ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ፣ ጋቦን እንዲሁም ናይጄሪያ በዚህ ዝርዝ
|
የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በእንፋሎት ኃይል ዘርፍ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ
March 15, 2017 - የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በእንፋሎት ኃይልና በሴራሚክ ማምረት ስራዎች ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ።
ባለሃብቶቹ ዛሬ ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር በፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ውይይት አድርገዋል።
ባለሃብቶቹ በእንፋሎት ኃይል፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በሴራሚክ ሥራ ላይ ለመሰማራት ነው ፍላጎት ያላቸው።
ቀደም ብሎ ኢትዮጵያ ለቱርክ ባለሃብቶች ያቀረበችው ማበረታቻና በሥራቸው ውጤታማ መሆናቸው መዋዕለ ንዋያቸውን ለማውጣት ለመፈለጋቸው በምክንያት ተጠቅሷል።
በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ፋቲህ ዩሉሶይ፥ ፕሬዚዳንት ሙላቱ በቱርክ ከወራት በፊት ያደረጉት ጉብኝት ባለሃብቶቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ካደረጉ ምክንያቶች ተጠቃሽ መሆኑን አውስተዋል።
ፕሬዚደንት ሙላቱ ከቱርክ አቻቸው ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸው ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 440 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል።
|
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእንጦጦ ተራራ በ4.8 ቢሊዮን ብር የቱሪስት ማዕከል ለመገንባት ተዘጋጀ
February 19, 2017 - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ4.8 ቢሊዮን ብር ካፒታል በእንጦጦ ተራራ ላይ ደረጃውን የጠበቀ የቱሪስት ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ ነደፈ፡፡
በሰሜን አዲስ አበባ በሚገኘው እንጦጦ ተራራ በ4,200 ሔክታር ቦታ ላይ የሚያርፈውን የቱሪስት ማዕከል ግንባታ ለማስጀመር በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራ ሥራ አመራር ቦርድ ተሰይሟል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤትና ማዕከሉን ማቋቋም የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረ ጻዲቅ ሐጎስ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የቱሪስት ማዕከሉ አራት ማዕቀፎች አሉት፡፡
ከእነዚህ ማዕቀፎች ውስጥ የመጀመሪያው የብሔርና ብሔረሰቦች ማዕከል ግንባታ ነው፡፡
አዲስ አበባ የብሔርና የብሔ
|
አዲስ አበባ በሪልእስቴት ኢንቨስትመንት ከአፍሪካ 3ኛ ሆናለች
February 13, 2017 - አዲስ አበባ በሪልእስቴት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ከአፍሪካ ከተሞች በ3ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና የከተማዋ የሪልእስቴት ልማት ዘርፍ ኢንቨስትመንት፣ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የዓለም ባንክ ከትናንት በስቲያ ይፋ ባደረገው የአፍሪካ ዋና ዋና ከተሞች ወቅታዊ ሁኔታ አመላካች ሪፖርት አስታውቋል፡፡
የታንዛንያዋ ዳሬ ሰላም በሪልእስቴት ልማት ዘርፍ ከአፍሪካ ከተሞች በአንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የጠቆመው ሪፖርቱ፣ የከተማዋ የሪልእስቴት ኢንቨስትመንት 12 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የገለጸ ሲሆን፣ የ9 ቢሊዮን ዶላር የሪልእስቴት ኢንቨስትመንት ባለቤት የሆነቺው የኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ፣ በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝም አስረድቷል፡፡
በአፍሪካ ከተሞች የሪልእስቴት ዘርፍ ልማት እየተስፋፋ ቢመጣም፣ የከተማ ነዋሪዎች ከነፍስ ወከፍ ገቢያቸው ጋር ሲነጻጸር የመኖሪያ ቤት ፍላጎታቸውን ለ
|
የእንግሊዝ ኩባንያዎች የገናሌ ዳዋ ቁጥር 6 የኃይል ማመንጫና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ሊገነቡ ነው
February 6, 2017 - የእንግሊዝ የታዳሽ ኃይል ኩባንያዎች ከ 850 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የገናሌ ዳዋ ቁጥር 6 የኃይል ማመንጫና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ሊገነቡ ነው።
ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ የእንግሊዝ የታዳሽ ኃይል ኩባንያዎች ግሎብሌክና አጋሮቹ የልዑካን ቡድንን ዛሬ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።
የካምብሪጅ ኢንዱስትሪዎች የኮርፖሬት ጉዳዮችና ዋና አማካሪ የሆኑት አሌክስ ስቴዋርት ለጋዜጠኞ እንደገለጹት ኩባንያዎቹ 250 ሜጋ ዋት የሚያመነጨውን ገናሌ ዳዋና የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን ያከናውናሉ።
የመስኖ ፕሮጀክቱ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች 27 ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል።
እናም ኩባንያዎቹ ባለፉ
|
|