አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - እግር ኳስ

ፊፋ በአፍሪካ ስስተኛ ቢሮውን በኢትዮጵያ ቢሮ ሊከፍት ነው

FIFA-Ethiopia-officeJanuary 19, 2019 - የአለም-አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ኢትዮጵያ ውስጥ ቢሮውን ሊከፍት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ይከፈታል የተባለው ቢሮ የተቋሙ የምስራቅ አፍሪካ ማስተባበሪያ ቢሮ ነው።፡ማስተባበሪያ ቢሮው የፊፋው ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ባለፈው መጋቢት ወር በካፍ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በገቡት ቃል መሰረት የሚከፈት ነው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በትዊተር ገጻቸው፥ ለቢሮው የሚሆነውን ቦታ የሚመለከቱ የፊፋ ተወካዮች በዛሬው እለት አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስታውቀዋል።

በነገው እለትም ለቢሮው የሚሆን ቦታ ከመረጡ በኋላ ሪፖርት ያደርጋሉ ነው የተባለው። ፌዴሬሽኑም ለማስተባበሪያ ቢሮው የሚሆን ቦታ እየመረጠ ነው ተብሏል።ፊፋ በሴኔጋልና ደቡብ አፍሪካ ሁለት የማስተባበሪያ ቢሮዎች አሉት።

ምንጭ፡ ኤፍ.ቢ.ሲ

ፌዴሬሽኑ 5 ተጫዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔዎችን አሳለፈ

Ethiopian-Football-FederationJanuary 1, 2018 - የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በ7ኛ እና 8ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ተጫዋቾች በፈፀሙት የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።

በ8ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከወልዲያ ባደረጉት ጨዋታ ዳኛውን ለመማታት ሙከራ ያደረገው አማረ በቀለ 6 ወራት ከእግርኳስ እንዲታገድ እና 10 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኖበታል።

በእለቱ ኤልያስ ማሞ ያስቆጠረው የፍጹም ቅጣት ምት እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው አማረ በቀለ ከፍጹም ቅጣት ምቱ ውሳኔ በኋላ ከዳኛው ጋር በገባው እሰጥ እገባ 62ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።

የእለቱ አመራሮች ባቀረቡት ሪፖርት መሰረትም አማረ ዳኛውን ለመማታት ሙከራ ማድረጉ በመገለጹ ነው 6 ወራት ከእግር ኳስ እንዲታገድ እና 10 ሺህ ብር እንዲከፍል የተወሰነበት።በተመሳሳይ አማረ በቀለ ከሜዳ ከወጣ ከ3 ደቂቃ በኋላ የቀይ ካርድ የተመዘዘበት ብሩክ ቃልቦሬ የተጋጣሚ ተጫዋችን በቡጢ መማታቱ በሪፖርት በመገለፁ ለፈ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ከስራቸዉ ለቀቁ

Ashenafi-bekele-Coach-EthiopiaDecember 26, 2017 - የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያስገቡት የስራ መልቀቂያ ተቀባይነት አገኘ። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን በሻህ የአሰልጣኙ የስራ መልቀቂያ በፌዴሬሽኑ ተቀባይነት ማግኘቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል።አሰልጣኝ አሸናፊ በ100 ሺህ ብር ወርኃዊ ደመወዝ ዋልያዎቹን ለማሰልጠን ባሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነበር የሁለት ዓመት ኮንትራት የተሰጣቸው።

ኮንትራቱም ከመጋቢት 1 ቀን 2009 ዓ.ም እስከ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም የሚቆይ የነበረ ሲሆን፥ በቆይታቸው ዋልያዎቹን ካሜሮን ለምታስተናግደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ግዴታ ተጥሎባቸው እንደበረ ይታወሳል። አሰልጣኝ አሸናፊ በወቅቱ በሰጡት መግለጫም፥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድንን በአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሩብ ፍጻሜ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገልፀው ነበር።

"ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ብቻ አይደለም ለቻን ውድድር ማሳለፍ ካልቻልኩ ሁለት ዓመት አልጠብቅም፤ በራሴ ፍቃድ እለቃለሁ" ማለታቸውም አይዘነጋም።አ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስመራጭ ኮሚቴ አጣብቂኝ ውስጥ መሆኑን ገለጸ

Ethiopian-Football-FederationDecember 18, 2017 - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስመራጭ ኮሚቴ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የምርጫ ህግ ባለመኖሩ ምክንያት መቸገሩን ገለጸ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀጣዮቹ አራት ዓመታት የሚመሩ ፕሬዚዳንትና ስራ አስፍጻሚ ምርጫ ጉዳይ የሚከተታል አስመራጭ ኮሚቴና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ መምረጡ የሚታወስ ነው።

ይህ አስመራጭ ኮሚቴ እየሰራቸው ያሉ ጉዳዮችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም አስመራጭ ኮሚቴው ምርጫን በተመከለተ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በኩል የተቀመጠ የምርጫ ህግ ባለመኖሩ ስራውን ለመስራት መቸገሩን ገልጿል።

አስመራጭ ኮሚቴው የአለም አቀፉን እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ህግን ተከትሎ እንደ ሀገሪቱ ነበራዊ ሁኔታ ህጉ ባለመቀመጡ አያሰራንም በሚል የአንዳንድ አባላት ጥያቄ ተግባራዊ ለማድረግ ተቸግሯል።

ይህ በመሆኑም አንዳንዴ የፊፋን ህግ ተከትሎ ይሰራል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ የፊፋን በጣሰ መልኩ በአስመራጭ ኮሚቴው በአብላጫ ድምጽ እንዲወሰኑ የተደረጉ ጉዳዮች እንዳሉ የተነገረው።

ሌላ ጊዜ ደ

ኢትዮጵያ ከሴካፋ ውድድር ተሰናበተች

CECAFADecember 12, 2017 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2017 የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና ሴካፋ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

ትናንት በየምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን፥ በካካሜጋ ቡኩሁንጉ ስታዲየም ደቡብ ሱዳን እና ቡሩንዲ ባደረጉት ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል።

የዋልያዎቹ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የማለፍ እድል በደቡብ ሱዳን ከሶስት ጎል ልዩነት በላይ የማሸነፍ እድል የተመሰረተ ቢሆንም፥ ቡድኖቹ አቻ በመውጣታቸው ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።

ከትናንት ወድያ በካካሜጋ ቡኩሁንጉ ስታዲየም የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፥ ከኡጋንዳ አቻው ጋር አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት ተለያይቷል።

በዚህም መሰረት ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ በተመሳሳይ አምስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተባላልጠው በቅደም ተከተል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ኡጋንዳ ውድድሩን 14 ጊዜ በማሸነፍ ሪከርዱን የያዘች አገር ናት።

ከየምድቡ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ያለፉት አራት አገራት የፊታችን ሐሙስ እና አርብ የግማሽ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቡሩንዲ 4 ለ1 ተሸነፈ

Burundi-national-teamDecember 7, 2017 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር በቡሩንዲ አቻው 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸነፈ።የ2017 የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና (ሴካፋ) ውድድር በኬኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጨዋታ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ያደረጉት ዋልያዎቹ በቡሩንዲ ብሄራዊ ቡድን ሽንፈትን አስተናግደዋል።

ማክሰኞ እለት ደቡብ ሱዳን 3 ለ 0 ያሸነፉት ዋልያዎቹ ምድቡን በሶስት ነጥብ መምራት ችለው ነበር።

ይሁን እንጂ ዛሬ ሽንፈትን በማስተናገዳቸው ምድቡን ቡሩንዲ በአራት ነጥብ ስትመራ ኢትዮጵያ በሶስት ነጥብ በሁለተኝነት ለመቀመጥ ተገዳለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምደቡን የመጨረሻ ጨዋታ እሁድ ከዩጋንዳ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

በእሁዱ ጨዋታ ምድቡን በአንደኝነት ወይም በሁለተኝነት መያዝ የሚያስችላቸውን ነጥብ  ማስመዝገብ ከቻሉ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የሚቀላቀሉ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በተደለደለችበት ምድብ ሁለት ላይ አንድ አንድ ጨዋታ ያደረጉት የዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድንና የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ቡድን እንደ

የኢትዮጵያ ከ17 በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከናይጄሪያ አቻው ጋር አንድ እኩል በሆነ ውጤት ተለያየ

U-17-EthiopianDecember 5, 2017 - ኡራጓይ በ2018 ለምታስተናግደው ከ17 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ከ17 በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከናይይጄሪያ አቻው ጋር ባደረገው የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ አንድ እኩል ወጥቷል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ናይጄሪያ በ22ኛው ደቂቃ በፕሪሺየስ ቪንሰንት ጎል መሪ የነበረች ቢሆንም በ63ኛው ደቂቃ ታሪኳ ደቢሶ ለቡድኗ የአቻነቷን ጎል አስቆጥራለች።

ናይጄሪያ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ እድሏን ስታሰፋ የኢትዮጵያ ከ17 በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የሜዳ እድሉን ሳይጠቀም ቀርቷል።

የማጣሪያው የመልስ ጨዋታ ታህሳስ 7 ቀን 2010 ዓ.ም በናይጄሪያ ቤኒን ከተማ በሚገኘው ሳሙኤል ኦግቤዲያ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።በድምር ውጤት ያሸነፈው ቡድን በቀጣዩ ዙር ከካሜሮንና ከአልጄሪያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የካቲት ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።

ከትናንት በስቲያ የካሜሮን ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሜዳው ውጪ የአልጄሪያ አቻውን አራት ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለቀጣይ ዙር የማለፍ እድሉን ማስፋት ችሏል።

የኢትዮጵያ

የኢንተርናሽናል እግር ኳስ ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከካፍ የዓመቱ ምርጥ እጩ ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

Bamlak-Tessema-Ethiopia-FootballNovember 29, 2017 - ከካፍ የዓመቱ ምርጥ ስድስት እጩ ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል እግር ኳስ ዳኛ ባምላከ ተሰማ አንዱ ሆኗል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የ2017 የዓመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን፣ ክለብ፣ አሰልጣኝ፣ ተጫዋች እና ዳኛ እጩዎች ይፋ አድርጓል።

በፈረንጆች 2017 ዓመት በካፍ የዓመቱ ምርጥ ዳኛ በእጩነት የተካተቱት ባካሪ ጋሳማ ከጋምቢያ፣ ባምላክ ተሰማ ከኢትዮጵያ፣ አብዲ ቻሪፍ ከአልጀሪያ፣ ጅሄድ ግሪሻ ከግብጽ፣ ጃኒ ስካዝዊ ከዛምቢያ እና ማላግ ዳይዲሆ ከሴኔጋል ናቸው።

ባምላከ ተሰማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ፣ በቻን ማጣሪያ እና በዘንድሮው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የግብጹን አልአሃሊ እና የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካን በመሀል ዳኝነት መምራት ችሏል።

ፊፋ በያዝነው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በሩሲያ የሚካሄደውን የአለም ዋንጫ ለመምራት ብቁ ያላቸውን ዳኞች ይፋ ሲያደርግ ከአፍሪካ ከተመረጡት ጥቂት ዳኞች መካከል ባምላክ አንዱ ሆኗል።

ጋምቢያው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባካሪ ጋሳማ በካፍ የዓመቱ ምርጥ

በፊፋ ወርሃዊ ደረጃ ኢትዮጵያ 6 ደረጃዎችን አሻሻለች

FIFA-EthiopiaNovember 24, 2017 - በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ወርሃዊው የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ 6 ደረጃዎችን አሻሽላለች።

ይህን ተከትሎም ከዓለም 145ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 44ኛ ደረጃን ይዛለች።

ኢትዮጵያ በወሩ 12 ደረጃዎችን ካሽቆለቆለችው ኢኳቶሪያል በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።የዓለም ቀዳሚ ደረጃዎችን ጀርመን በአንደኝነት ስትመራ ብራዚል እና ፖርቹጋል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነው ይከተላሉ።

አርጀንቲና፣ ቤልጂየም፣ ስፔን፣ ፖላንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ ፈረንሳይ እና ቺሊ ደግም በቅደም ተከተል ከአራተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ሴኔጋል 23ኛ ደረጃን በመያዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ቱኒዚያ 27ኛ እና ግብፅ 31ኛ ደረጃን በመያዝ ከአፍሪካ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ሆነዋል።

አንጉሊያ፣ ባህማስ፣ ኤርትራ፣ ጅብራልተር፣ ሶማሊያ እና ቶንጋ ደግሞ አሁንም ያለምንም ነጥብ በደረጃው ግርጌ ላይ ይገኛሉ።

በወሩ ሰሜን ኮሪያ 18፣ ሊባኖን 13 እንዲሁም ቡርኪናፋሶ እና ኢንዶኔዥያ 11 ደረጃዎችን በማሻሻል የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

በአንጻሩ ኢኳዶ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ ያደርጋል

Ethiopian-football-federationNovember 22, 2017 - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬ  እለት እንደሚያደርግ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም ባጠናቀቀው 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ፥ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን በ45 ቀን ማራዘሙ ይታወሳል።

በነገው እለት በሚያካሂደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውም በፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ዙሪያ እንደሚወያይ ይበቃል። ከዚህ ባለፈም አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚመርጥ እና የምርጫ ደንብ ውይይት እንደሚያካሂድም ይጠበቃል።

ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች እጩዎቻቸውን ለፌዴሬሽኑ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።ለፕሬዚዳንትነት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከሁለት በላይ እጩዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። :

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ በ10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጠቅላላ ምርጫው ደግሞ በሌላ ጊዜ እንዲካሄድ በ

አቶ ተክለወይኒ ክልሉን የማይወክል መግለጫ በመስጠታቸው ውክልናቸው መነሳቱ ተገለፀ

Tekleweini-Assefa-Tigray-EthiopiaNovember 12, 2017 - የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን በመወከል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፋጻሚነት ሲወዳደሩ የቆዩትን አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ውክልና ያነሳ መሆኑን የትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡

አቶ ተክለውይኒ ውክልናቸው የተነሳው ሰሙኑን ለጋዜጠኞች የሰጡት መግለጫ የትግራይ ክልላዊ መንግስትን የማይወክል በመሆኑ ነው፡፡

በዚህም ትግራይን በመወከል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፋጻሚነት ሲወዳደሩ የቆዩትን አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ውክልና መነሳቱን ተገልጿል።
 
በዚህም ትግራይን በመወከል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፋጻሚነት ሲወዳደሩ የቆዩትን አቶ ተክለወይኒ አሰፋ ውክልና መነሳቱን ተገልጿል።
 
ምንጭ፡ ኤፍ.ቢ.ሲ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚዎች ምርጫ ከ45 ቀናት በኋላ እንዲካሄድ ተወሰነ

Ethiopian-Football-Federation-ElectionNovember 10, 2017 - ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን ወስኗል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬ ውሎው ምርጫው ከ45 ቀናት በኋላ ታህሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም እንዲደረግ ወስኗል።

የፌደሬሽ 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ፌደሬሽኑ ባዘጋጀው የጉባኤ መርሀ ግብር መሰረት ተጠባቂው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ነገ ህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም ከ3 ሰዓት ጀምሮ እንደሚያከናወን ያሳይ ነበር።

ሆኖም ግን በትናንትናው እለት በተካሄደው ጉባዔ ላይ ጠቅላላ ምርጫው በሌላ ጊዜ እንዲካሄድ በአብላጫ ድምፅ መወሰኑም ይታወሳል።

የኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌደሬሽን ምርጫው በአንድ ወር እንዲራዘም በይፋ መጠየቁ የሚያወስ ሲሆን፥ ሌሎች አንዳንድ ክልሎችም ምርጫው እንዲራዘም ፍላጎት እንዳላቸው ሲገልፁ ነበር::

በዚህም መሰረት ምርጫው ከ45 ቀ

የኢትዮጵያ የፕሪምየር ሊግ ተጀመረ

Ethiopian-Premier-LeagueNovember 5, 2017 - በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2010 የውድድር ዘመን መክፈቻ ጨዋታዎች በተለያዩ ከተማዎች ተካሂደዋል።

የዛሬዎቹ ሶስት ጨዋታዎች በተመሳሰይ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ተካሂደዋል።

ወልዲያ ላይ ወልዲያ እና አዳማ ከተማ ተገናኝተው በወልዲያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል። አርባ ምንጭ ላይ ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ እና መቀሌ ከተማ ተገናኝተው 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።

ጅማ ላይ፥ ጅማ አባ ጅፋር ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። እሁድ አዲግራት ላይ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ፋሲል ከተማ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ።

ምንጭ፡- ሶከር ኢትዮጵያ

ካፍ ኢትዮጵያ ወደ ቻን እድትመለስ የሚያስችላት ሁለተኛ እድል ሰጠ

CAF-Ethiopia-FootballOctober 29, 2017 - የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ኢትዮጵያ በ2018 በሞሮኮ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ቻን ውድድር ላይ እንድትካፈል የሚያስችላት ሁለተኛ እድል ሰጠ።

የ2018 የአፍሪካ ሃገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ያለፉ 16 ሃገራት አስቀድመው ቢታወቁም፤ ካፍ የግብፅን አለመካፈል ተከትሎ የምስራቅ እና መካከኛው አፍሪካ ዞን አንድ ተጨማሪ ሀገር ለውድድሩ እንዲያልፍ ወስኗል።

በመጨረሻው የማጣሪያ ዙር የወደቁት ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የደርሶ መልስ ጨዋታ አድርገው ወደ ሞሮኮ እንዲያመሩም ካፍ ዳግመኛ እድል ሰጥቷቸዋል።

ኢትዮጵያ በሱዳን፤ ሩዋንዳ ደግሞ በዩጋንዳ ተሸንፈው ነው ከውድድሩ ውጪ መሆናቸው ይታወሳል።

ግብፅ የሊግ ውድድሯን ላለሟቋረጥ እና ለዋናው ብሄራዊ ቡድኗ የዓለም ዋንጫ መዘጋጃ ሰፋ ያለ ግዜ ለመስጠት በማሰብ ከቻን እራሷን ማግለሏን ተክተሎ ከሰሜን ዞን አልጄሪያ ትሳተፋለች ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ሳይሆን በመቅረቱ እድሉ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ዞሯል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የካፍ የሚዲያ ኃላፊ ጁኒየር ቢኒያም

ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ይፋለማሉ

Ethiopia-Coffee-St.GeorgeOctober 21, 2017 - በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስን አገናኝቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አንድ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ማምሻውን ተካሂዷል። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመስዑድ መሐመድ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በመርታቱ፥ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በፍጻሜው ይፋለማሉ።

ትናንት በነበረው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ጂማ አባ ጅፋር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ተገናኝተዋል።

በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ከስታዲየሙ ውጪ የሚገኝ ትራንስፎርመር ፈንድቶ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ተቋርጦ ነበር።

ጨዋታው 82ኛው ደቂቃ ላይ ከተቋረጠ በኋላ በድጋሚ ተጀምሮ ተጠናቋል።ጨዋታው ያለ ግብ መጠናቀቁን ተከትሎም ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት አምርተዋል።

በተሰጠው የመለያ ምትም ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ለ 2 በማሸነፍ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

ለፍፃሜ ያለፉት ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በመጪው እሁድ ለዋንጫ የሚያደርጉት ፍልሚያ ከወዲሁ ተጠባቂ ሆኗል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

በፊፋ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ የኢትዮጵያ ደረጃ ወደ 151ኛ አሽቆለቆለ

Ethiopia-FIFAOctober 16, 2017 - በአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ወደ 151ኛ አሽቆልቁላለች።በወርሃዊው የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከነበረችበት 144ኛ ደረጃ 7 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 151ኛ ላይ ተቀምጣለች።

ኢትዮጵያ በተከታታይ ወራት ከፍተኛ የደረጃ መንሸራተት እያስመዘገበች ትገኛለች።ወርሃዊውን የፊፋ የሃገራት ደረጃ የብራዚሉ የአለም ዋንጫ አሸናፊ ጀርመን ስትመራው ብራዚልና ፖርቹጋል ደግሞ ይከተሏታል።

ጀርመን በ1 ሺህ 631 ነጥቦች ስትመራ ብራዚል በ1 ሺህ 619 ነጥብ ትከተላታለች።ፖርቹጋልና አርጀንቲና በአንድ ነጥብ ተበላልጠው ተከታዮቹን ደረጃዎች ሲይዙ፥ ቤልጂየምና ፖላንድ ባለፈው ወር በነበሩበት 5ኛ እና 6ኛ ደረጃ ላይ ፀንተዋል።

ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ቺሊ እና ፔሩም እስከ 10 ባለው ደረጃ መካተት ችለዋል።ቱኒዚያ 28ኛ ደረጃን በመያዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ግብጽ እና ሴኔጋል 30ኛ እና 32ኛ በመሆን ይከተላሉ።ከአፍሪካ ምድብ ቀድማ የአለም ዋንጫ ትኬት የቆረጠችው ናይጀሪያ ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ በመሆን ከአፍሪካ 5ኛ

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በፎርፌ ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር አለፈ

Ethiopia-women-under-17October 5, 2017 - የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በፎርፌ ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር አልፏል።ብሔራዊ ቡድኑ በ2018 በኡራጓይ አስተናጋጅነት በሚከናወነው ከ17 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያ ጋር ለማድረግ ተመድቦ ነበር።

ሆኖም ኬንያ ከውድድሩ ራሷን በማግለሏ ታዳጊዎቹ ሉሲዎች ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር በፎርፌ አልፈዋል። በአሰልጣኝ ሰላማዊት ዘርዓይ የሚሰለጥነው ቡድኑ 36 ተጨዋቾችን በመጥራት በወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ሜዳ በጥቅምት ወር ላለበት የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ልምምድ ማድረግ መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ተጋጣሚው የኬንያ ቡድን ጨዋታውን እንደማያደርግ መገለፁን ተከትሎ፥ የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታውን ለማድረግ እስከ ህዳር ወር አጋማሽ ድረስ ለመጠበቅ ይገደዳል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ዋና ፀሃፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ የኬንያን ከማጣሪያው ውጪ መሆን ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ለኬንያ እግርኳስ ፌደሬሽን ቅርበት ካላቸው ምንጮች በተገኘ መረጃ የኬንያ ተማሪዎች እስከ ህዳር 7 ድረስ ፈተና ላይ ስለ

ኢትዮጵያ የ2018 የቻን አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ አላቀረብኩም አለች

Ethiopia-CAFOctober 2, 2017 - ኢትዮጵያ የ2018 የቻን አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ምንም አይነት ጥያቄ አለማቅረቧን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ገለጸ።

የ2018 የቻን አፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ጥያቄ  ማቅረቧን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) በድረ ገጹ ላይ አስፍሯል። የአገር ውስጥ ተጨዋቾች ብቻ የሚሳተፉበት የቻን ውድድር፤ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ሞሮኮ ጥያቄ ማቅረባቸውን ኮንፌደሬሽኑ አስታውቋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ እንደገለጹት  የቻን አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ለካፍ ያስገባነው ሰነድ የለም ብለዋል።

ውድድሩን ለማስተናገድ ኬኒያ የተመረጠች ቢሆንም በቂ ዝግጅት እያደረገች ባለመሆኑ የአስተናጋጅነት መብቷ መነጠቋን ተከትሎ ውድድሩን እናዘጋጅ ወይስ አናዘጋጅ? በሚል ውይይት እንደተደረገ ገልጸው ነገር ግን ውድድሩን ለማስተናገድ በይፋ የቀረበ ጥያቄ እንደሌለ ገልጸዋል።

በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ በ2020 የሚካሄደውን የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ናት፤ የአሁኑን

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከፈረንሳዩ የ2018 የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ

Ethiopian-Women-Team-EliminatedOctober 1, 2017 - በዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ እየተካፈለ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከኬንያ ጋር ባደረገው የመልስ ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸንፏል።

የኬንያ ቡድን በ11ኛና በ52ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎችን ሲያስቆጥር፥ ኢትዮጵያ የማስተዛዘኛዋን ጎል በምርቃት ፈለቀ አማካኝነት በፍጹም ቅጣት ምት አግኝታለች።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በሜዳው ከኬንያ ጋር መስከረም 7 ቀን ያደረገውን ጨዋታ ሁለት አቻ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የኬንያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ 4 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል።ኬንያ በሁለተኛው ዙር በነገው እለት ጨዋታቸውን ከሚያደርጉት የአልጀሪያና የጋና አሸናፊ ጋር ትገናኛለች።ፈረንሳይ በምታስተናግደው ውደድር ላይ 16 ቡድኖች የሚካፈሉ ሲሆን፥ አፍሪካ በሁለት ቡድኖች የምትወከል ይሆናል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመልስ ጨዋታ የኬንያ አቻውን ይገጥማል

Ethiopia-women-under-20የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለመልስ ጨዋታ ወደ ኬንያ አቅንቷል ቡድኑ በ2018 ፈረንሳይ ለምታስተናግደው ከ20 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የመጀመርያ ዙር የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ነው ወደ ናይሮቢ የተጓዘው።

በአሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ የሚመራዉ ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመርያ ጨዋታውን ከኬንያ አቻው ጋር በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም አድርጎ ሁለት አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

በምርቃት ፈለቀ እና አለምነሽ ገረመው የመጀመርያ አጋማሽ ሁለት ግቦች 2-0 መምራት ቢችሉም፥ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ኬንያዎች ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች 2-2 ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በመልሱ ጨዋታ የማለፍ እድሉ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።

አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ የሚመሩት ብሄራዊ ቡድኑ ባለፉት 10 ቀናት በሀዋሳ ከተማ በጨዋታው በታዩ ደካማ ጎኖች ላይ በማተኮር ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር ለማለፍ የሚያስችለውን ውጤት ለማስመዝገብ የቡድኑ አባላት የሚቻለውን

12

Archived News

No News to show