አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - አትሌቲክስ

የማራቶን ሯጩ አትሌት ኃይሌ ቶሎሳ በተከለከለ አበረታች መድሃኒት ሳቢያ ተቀጣ

Haile-Tolossa-finedJanuary 11, 2018 - የማራቶን ሯጩ አትሌት ኃይሌ ቶሎሳ ቦኩማ የተከለከለ የስፖርት አበረታች መድሃኒት ተጠቅሞ በመገኘቱ የቅጣው ውሳኔ ተላለፈበት።የቅጣት ውሳኔውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ነው ያሳለፈበት።

አለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር በአውሮፓውያኑ ግንቦት 15 ቀን 2016 በፔሩ በተካሄደው የሞቪስታር ሊማ ማራቶን ውድድር ላይ አትሌት ኃይሌ ቶሎሳ የስፖርት የፀረ-አበረታች መድሃኒት (ዶፒንግ) የህግ ጥሰት መፈፀሙን በመግለፅ እርምጃ እንዲወሰድበት ማሳወቁን ተከትሎ ነው ውሳኔው የተላለፈበት ተብሏል።በወቅቱ በተደረገው የቤተ ሙከራ ምርመራ አትሌት ኃይሌ ቤንዞላይክጎኒን፣ ሜታሊክጎኒን እና ኮኬይን ሜታቦሊቲስ የተባሉ የተከለከሉ ቅመሞችን መጠቀሙ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤትም አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የላከውን መረጃና የውሳኔ ኃሳብ መነሻ በማድረግ አትሌቱ ለ4 ዓመታት ከስፖርታዊ ውድድሮች እንዳይሳተፍ ቅጣት አሳልፎበታል። በዚህ መሰረት አትሌቱ የህግ ጥሰቱን መፈፀሙ ላይ የማጣራት ሂደት ከተጀመረበት የአውሮፓውያኑ

ቀነኒሳ በቀለ የህንድ ካልካታ የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርን አሸነፈ

Kenenisa-IndiaDecember 18, 2017 - አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በህንድ ካልካታ በዛሬው እለት የተካሄደውን የካልካታ ታታ ስቲል የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በአሸናፊነት አጠናቀቀ። ቀኒሳ በቀለ ውድድሩን 1 ሰዓት ከ13 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ በማግባትን በአንደኝነት ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በዚህም የስፍራውን ከብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።

አትሌት ቀነኒሳ ከውደድሩ ቀደም ብሎ ባሳለፍነው ዓረብ በሰጠው መግለጫ በርቀቱ የግሉ ሰዓት የሆነውን 1 ሰዓት ከ12 ቀዲቃ ከ47 ሰከንድ ለማሻሻል እንደሚሮጥ ተናግሮ ነበር።ሆኖም ግን ቀነኒሳ የግሉን ሰዓት ማሻሻል ባይቸልም፤ በህንዳዊው አትሌት ጎቪንዳን ላክሽማን የተያዘውን የስፍራውን ክብረ ወሰን በ3 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ በማሻሻል የግሉ አድርጓል።

በውድድሩ ኤርታራዊው አትሌት ፀጋይ ጥኡመይ 2ኛ፣ ታንዛኒያዊው አትሌት አጉስቲኖ ሱሌ 3ኛ፣ ህዳዊው አቪናሽ ሳብሌ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን ሲያጠናቅቁ፤ ኢትዮጵያዊው አትሌት አሰፋ ዲሮ 5ኛ ወጥቷል።

በሴቶች ምድብ የተካሄደውን የካልካታ ታታ ስቲል የ25 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ደጊቱ አዝመራው 1 ሰዓት ከ26 ቀዲቃ

አትሌት ዝናሽ ገዝሙ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

Zinash-Gezmu-Ethiopian-Athlete-deadDecember 1, 2017 - ዋሪነቷን በፈረንሳይ ሀገር አድርጋ የነበረችው የ29 አመቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት ዝናሽ ገዝሙ ከዚህ አለም በሞት መለየቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የእትሌቷን ህልፈት ከስፍራው በደረሰው መረጃ ማረጋገጥ መቻሉንም አስታውቋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 በአምስተርዳም በተካሄደ የማራቶን ውድድር ላይ ተካፍላ 2:32:48 በሆነ ሰዓት 6ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ አይዘነጋም።

የአትሌት ዝናሽን የአሟሟት ምክንያትና ሁኔታ ፌዴሬሽናችን እያጣራ የሚገኝ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

አትሌቷ ከሀገሯና ከፌዴሬሽኑ ለረጅም ጊዜ እርቃ መኖሯ ሙሉ መረጃውን በቀላሉ አግኝቶ ለማድረስ አስቸጋሪ እንዳደረገውም ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ስለአጠቃላይ የአሟሟቷ ሁኔታ ለአትሌቲክስ ስፖርት ቤተሰቡ መረጃውን እንደሚያደርስ አስታውቋል።

ፌዴሬሽኑ በአትሌት ዝናሽ ገዝሙ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን የገለፀ ሲሆን፥ ለመላው

አትሌቶች በኦሎምፒክና በአትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉበትን አሰራር የሚቀይር ስርዓት ሊተገበር ነው

Ethiopian-Athletics-federationNovember 5, 2017 - አትሌቶች በኦሎምፒክና በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉበትን አሰራር የሚቀይር የዓለም የአትሌቶች ደረጃ ስርዓት ተግባራዊ ሊሆን ነው።

የዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር ስርዓቱን መተግበር የሚያስችለውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ከእንግሊዙ የቢዝነስ ተቋማት የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ኢሊት ኩባንያ ጋር ትናንት በፈረንሳይ ሞናኮ ተፈራርሟል።

ስርዓቱ እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን ማህበሩ በየዓመቱ በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች አትሌቶች ያስመዘገቡት ውጤት በመረጃ ቋት እንዲመዘገብ ያደርጋል።በዚሁ መሰረት አትሌቶች በዓመት ውስጥ ባስመዘገቡት ውጤት መሰረት የሚሰጣቸው ነጥብ ተደምሮ በኦሎምፒክና በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።

የሚሰጣቸው ነጥብ ባስመዘገቡት ደረጃና የሚሳተፉባቸው ውድድሮች በማህበሩ በተሰጣቸው ደረጃና ባላቸው ፋይዳ ላይ እንደሚወሰን የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር በድረ ገጹ አስነብቧል።

ይህ ስርዓት ማህበሩ በሚያካሂዳቸው ሁሉም የስፖርት አይነቶች የሚተ

ሙክታር የጂሮ አል ሳስ የጎዳና ሩጫ ውድድር አሸነፈ

Muktar-Edris-EthiopiaOctober 1, 2017 - አትሌት ሙክታር እድሪስ ትናንትና በተካሄደው የጂሮ አል ሳስ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድርን አሸንፏል፡፡ በጣልያን ትሬንቶ ከተማ የተካሔደውን ውድድር አትሌት ሙክታር እድሪስ በ28 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል። ውድድሩን ሲያሸንፍ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ጥላሁን ሃይሌ ከአትሌት ሙክታር በአንድ ሰከንድ ዘግይቶ ሁለተኛ ሲወጣ፤ አትሌት ሀሰን ሀጂ 29 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ በመግባት ሶስተኛ በመውጣት የኢትዮጵያውያን አትሌቶችን የበላይነት አረጋግጧል። አትሌት ሙክታር እድሪስና ጥላሁን ሃይሌ እስከ ውድድሩ ማብቂያ ድረስ ትንቅንቅ አድረገዋል።

አትሌት ሙክታር ውድድሩን በአስገራሚ የአጨራረስ ብቃት ማሸነፉን  የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማህበር በድረ ገጹ አስፍሯል። "በከፍታ ቦታ ላይ ያደረኩት ልምምድ ውድድሩን እንዳሸንፍ አግዞኛል" ሲል አትሌት ሙክታር ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

"ብቃቴ ከዕለት ዕለት እየተሻሻለ ነው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ድል ህይወቴን ቀይሮታ

በኬፕ ታውን ማራቶን ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታዎች አሸንፈዋል

Cape-Town-Marathon-EthiopiaSeptember 19, 2017 - በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች አሸንፈዋል።

በወንዶች አትሌት አሰፋ መንግስቱ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቂ ከ01 ሰኮንድ በመግባት ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን ከተማ በቀለ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

ከተማ የገባበት ጊዜ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ሲሆን፥ ኬንያዊው ዱንካን ማዮ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ826 ሰከንደ በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

አትሌት አሰፋ ከውድድሩ በኋላ በሰጠው አስተያየት በውድድሩ በ2016 በራሱ ተይዞ የነበረውን የቦታውን የ2 ሰዓት ከ08 ደቂቃ 42 ሰኮንድ ክብረወሰን ለመስበር አስቦ እንደነበር ገልጿል።

ከፍተኛ የነፋስ ግፊት ፍጥነቱን እንዳይጨምር ስላደረገው ክብረ ወሰኑን ባያሻሽልም፥ ሁሉም ነገር ጥሩ ከሆነ በቀጣይ ዓመት በኬፕታውን ማራቶን በመሳተፍ የራሱን ክብረወሰን ለማሻሻል ጥረት እንደሚያደርግ ጠቁሟል።

በውድድሩ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ቤተልሔም ሞገስ 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ከ22

አትሌት ሻለቃ ዋሚ ቢራቱ የክብር ዶክትሬት አገኙ

Ethiopian-Athlete-Wami-BiratuAugust 27, 2017 - አትሌት ሻለቃ ዋሚ ቢራቱ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ  ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት አገኙ።አትሌት ሻለቃ ዋሚ  በሚሊኒየም አዳራሽ ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬት ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እጅ ተቀብለዋል።

አትሌት ዋሚ ቢራቱ ሃገራቸውን በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ወክለው ውጤታማ መሆን የቻሉ አንጋፋ አትሌት ናቸው። ዋሚ ቢራቱ በተወዳደሩባቸው የማራቶንና የረጅም ርቀት ሩጫዎች 80 ሜዳልያ ማግኘት ችለዋል።

ከዚህ ውስጥ 30 ወርቅ ሲሆን፥ 40 የብር እንዲሁም 10 የነሃስ ሜዳልያዎችን አሸንፈዋል።ዋሚ ቢራቱ ለኢትዮጵያ በማራቶን ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን ያመጣው አትሌት አበበ ቢቂላ ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸው ይነገራል።

አበበ ቢቂላ ውጤታማ በነበረበት የሮም ኦሊምፒክ በኢትዮጵያ የማራቶን ቡድን አባል ቢሆኑም በህመም ምክንያት በውድድሩ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተዋል።በአሰልጣኝነትም አበበ ቢቂላን ማሰልጠን ችለዋል።

ባለፈው ጥር ወር 10

ሞ ፋራሕ በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን አሸነፈ

Mo-Farah-winsAugust 25, 2017 - ትናንት ምሽት በተካሄደው የስዊዘርላንድ ዙሪክ ዳይመንድ ሊግ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ከፍተኛ ትንቅቅ ታይቶበት ተጠናቋል። ውድድሩ ላይም በእንግሊዛዊው ሞህ ፋራህ፣ በኢትዮጵያውያኑ ሙክታር አድሪስ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ መካከል ከፍተኛ ትንቅንቅ ታይቶበታል።

በመጨረሻም ውድድሩ በሞህ ፋራህ አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ኢትዮጵያውያኑ ሙክታር እድሪስ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

ንግሊዛዊው ሞህ ፋራህ ውድድሩን 13 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ05 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውደድሩን በአሸናፊነት አጠናቋል።

ሙክታር አድሪስ 13 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ09 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ፤ ዮሚፍ ቀጄልጃ 13 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ18 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቋል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሰለሞን በርጋ 13 ደቂቃ ከ07 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአራተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

አሜሪካዊው ፓውል ኬፕኬሚዮ ቼሌሞ ከሞህ ፋራህ በመቀጠል ሁለተኛ ሆኖ ገብቶ

በለንደኑ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉት የኢትዮጵያ ልዑካን ሽልማት ተሰጠ


Team-Ethiopia-London-2017August 21, 2017 - በለንደን አስተናጋጅነት በተካሄደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ትናንት ማምሻውን በአራራት ሆቴል በተካሄደ ስነ ስርዓት ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

በስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሻምፒዮናው ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ብር ሸልሟል፡፡ፌዴሬሽኑ የብር ሜዳሊያ ላስገኙ ደግሞ 30 ሺህ ብር አበርክቷል፡፡

ልዩ ተሸላሚ ናቸው ላላቸው ዮሚፍ ቀጄልቻና ለአልማዝ አያና አሰልጣኝና ባለቤቷ ለሆኑት ሶሬሳ ሲዳ ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ብር ሸልሟል፡፡የልዑኩ መሪ የነበረው አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም የተሸለመውን 40 ሺህ ብር፥ በውድድሩ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ እንድታገኝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከተው ዮሚፍ ቀጄልጃ አበርክቶለታል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በበኩሉ ወርቅ ላስገኙ አትሌቶች የ20 ሺህ ብር ሽልማት ሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ የልዑኩ አባል ለነበሩ ከ8 ሺህ ብር ጀምሮ ሽልማት መሰጠቱ ነው የተነገረው፡፡

"መሀመድ ፋራህን እንደማሸንፈው እርግጠኛ ነበርኩ" - አትሌት ሙክታር እድሪስ

Muktra-Idris-defeats-Mo-FarrahAugust 14, 2017 - "ለውድድሩ በከፍተኛ ሁኔታ ስለተዘጋጀሁ መሐመድ ፋራህን እንደማሸንፈው እርግጠኛ ነበርኩ" ሲል በአምስት ሺህ ሜትር ወንዶች ለኢትዮጵያ ወርቅ ያስገኘው አትሌት ሙክታር እድሪስ ተናገረ።

እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ በበኩሉ "አትዮጵያውያን አትሌቶች ይዘውት የገቡት የውድድር ዕቅድ እንድሸነፍ አድርጎኛል" ብሏል።

ትናንት ማታ በተደረገው የአምስት ሺህ ሜትር ወንዶች የፍጻሜ ውድድር በአትሌት ሙክታር እድሪስ አስገራሚ የአጨራረስ ብቃትና የአረንጓዴው ጐርፍ የሚለውን መጠሪያ ባስታወሰ የቡድን ስራ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ በአምስት ሺህ ሜትር ወንዶች በጀርመን በርሊን በተካሄደው 12ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በርቀቱ ካስገኘው የወርቅ ሜዳሊያ በኋላ ትናንት ወርቅ ስታገኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

14 አትሌቶች በተሳተፉበት የፍጻሜ ውድድር እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ የማሸነፍ የቅድሚያ ግምት በተለያዩ የአትሌቲክስ ባለሙያዎች ተሰጥቶት ነበር።<

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ እና ሁለት እህቶቿ በለንደን ዝርፊያ ተፈፀመባቸው

Tirunesh-Dibaba-Robbed-LondonAugust 8, 2017 - በለንደኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተሳተፈ በሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አባላት ላይ ዝርፊያ ተፈጽሟል። ዝርፊያው ትናንት ምሽት ቡድኑ ባረፈበት ጎማን ታወር በተባለው ሆቴል ውስጥ ነው የተፈጸመው።

በወቅቱም በሆቴሉ የህንጻው 9ኛ ወለል ላይ በሚገኙ ሁለት የአትሌቶች ክፍል ላይ ዝርፊያው ተፈጽሟል። አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከሁለት እህቶቿ ጋር ያረፈችበት ክፍልና ሴት የማራቶን ተወዳዳሪዎቹ ማሬ ዲባባና አሰለፈች መርጊያ ባረፉበት ክፍል ውስጥ ነበር ዝርፊያው የተፈጸመው።

በሆቴሉ የጽዳት ሰራተኞች ሳይፈጸም አልቀረም በተባለው ዝርፊያ፥ ከአትሌቶች ኪስ፣ ቦርሳ እና መሳቢያ ውስጥ ገንዘብ መጥፋቱን የስፖርት ዞን ባልደረባ ከስፍራው ዘግቧል። አትሌት ጥሩነሽ የሆቴሉ የጽዳት ሰራተኞች ወደ ክፍላቸው በተደጋጋሚ በመምጣት እረፍት ይነሷቸው እንደነበር ከስፖርት ዞን ጋር ባደረገችው ቆይታ ተናግራለች።

የጽዳት ሰራተኞቹ ከተለመደው ሰዓታቸው ውጪ እነርሱ ባረፉበት ወለል ላይ በተደጋጋሚ ይመጡ እንደነበርና ሁኔታው እረፍት እንዳሳጣቸውም ነው የተናገረችው

አልማዝ አያና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

Ethiopian-Almaz-Ayana-Wins-GoldAugust 6፣ 2017 - በለንደኑ 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አገኘች፡፡

ኢትዮጵያ በአልማዝ አያና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች፡፡

አልማዝ በርካታ ዙሮችን  ከተወዳዳሪዎቿ ተነጥላ  ወጥታ ቀሪዎቹን ዙሮች ብቸዋን በመሮጥ ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

አልማዝ ርቀቱን 30:16.33 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው የወርቅ ሜዳሊያ ማሸነፍ የቻለችው፡፡

ጥሩነሽ ዲባባ ከኬንያዉያን የገጠማትን ብርቱ ፍኩክር በመቋቋም ከአልማዝ ተከትላ ሁለተኛ መውጣት ችላለች፡፡

ጥሩነሽ በ31፡02.69 በማስመዝገብ የብር ሜዳልያ ለሀገራ አስገኝታለች፡፡

በጥሩነሽ ዲባባና በአልማዝ አያና መካከል የሚደረገው ፉክክር በጉጉት ይጠበቃል

Tirunesh-Dibaba-Almaz-AyanaAugust 5, 2017 - በለንደን አስተናጋጅነት የሚካሄደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ የሁለተኛ ቀን ውድድሮችን ያስተናግዳል፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ከ10 ደቂቃ የሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን፥ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ አልማዝ አያና እና ደራ ዲዳ ኢትዮጵያን ይወክላሉ።

በዚህ ውድድር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ እና አልማዝ አያና የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል። በውድድሩም በማራቶን እንደምትካፈል ሰትጠበቅ ወደ 10 ሺህ የተመለሰችዉ ጥሩነሽ ዲባባና በሪዮ ኦሎምፒክ የዓለምን ክብረወሰን የሰበረችዉ አልማዝ አያና የማሸነፍ ቅድመ ግምት አግኝተዋል፡፡

ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ45 ላይ በ ወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያ መሀመድ አማን ኢትዮጵያን ይወክላል፡፡በሌላ በኩል ምሽት 3 ሰዓት ከ35 ላይ በሚደረገው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ዉድድር ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል፡፡

ዓለም በጉጉት የሚጠብቀዉ የወንዶች መቶ ሜትር ፍጻሜም ይከናወናል፡፡

ትናንት ሻምፒዮናው ሲጀመር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉባቸው ሁለት ውድድ

በለንደን በሚካሄደው 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ተሸኙ

Ethiopian-Athletes-send-offAugust 1, 2017 - በለንደን በሚካሄደው 16ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የልዑካን ቡድን ትናንት ምሽት በአራራት ሆቴል ሽኝት ተደርጎለታል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ስመ ጥር አትሌቶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፥ የቡድን መንፈስ ከምንም ነገር በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወሳኝ በመሆኑ አትሌቶች በቡድን ሰርተው ለድል እንዲበቁ ምክሩን ለግሷል።

“አንድ ከሆናችሁ ማንም አያሸንፋችሁም፤ ከተለያያችሁ እንኳን ጠንካራው ደካማው ያሸንፋዋል፤ ስለዚህ እባካችሁ እንድ ሁኑ አትነጣጠሉ፤ አንድነት ሃይል ነው፣ ኢትዮጵያዊነትን አስቀድሙ፤ ድል ከእናንተ ጋር ይሁን" በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።

የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ተስፋዬ ይገዙ በበኩላቸው፥ &

ለለንደኑ የአለም ሻምፒዮና ባለመመረጡ ምክንያት አሠልጣኙን የደበደበው ኢትዮጵያዊ አትሌት በፖሊስ እየተፈለገ ነው

Athlete-Attacks-CoachJuly 29, 2017 - ለለንድኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለመመረጡ የተነሣ አሰልጣኙን ደብድቦ በአሠልጣኙ የግራ አይን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው አትሌት ጫላ በዩ በፖሊስ እየተፈለገ ነው። አትሌቱ አሠልጣኙን በቡጢ ከመማታቱ በተጨማሪ፤ ጥቃቱን ባደረሰበት ወቅትም በእጁ ትልቅ ድንጋይ ይዞ ነበር ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ፖሊሲ አትሌቱን በማፈላለግ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ አትሌቱ በአሰልጣኝ ሻምበል ዮሃንስ መሃመድ ላይ በፈፀመው ድብደባ ለሁለት ዓመታት ከማንኛውም የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ እንዲታገድ የቀረበውን ውሳኔ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት በ2003 ዓ.ም በጸደቀው የፌዴሬሽኑ ደንብና መመሪያ አንቀጽ 15 ቁጥር 2 መ ላይ በተመለከተው መሰረት፥ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጉድለት የፈጸመ አትሌት ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ከማንኛውም ውድድር እንዲታገድ በሚደነግገው መሰረተው ነው እንዲቀጣ የተወሰነው።

ፌዴሬሽኑ በአትሌቱ ላይ የተጀመረው የወንጀል ክስ በፖሊስ አካላት ተጣርቶ ይታወቃል ብሏል።አትሌት

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶች ይፋ ሆኑ

Ethiopian-Athletics-FederationJuly 26, 2017 - የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶችን ይፋ አድርጓል።ኢትዮጵያ በለንደኑ ሻምፒዮና ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን የምትሳተፍ ሲሆን 40 አትሌቶችን ታሳትፋለች።

በዚህ ቡድን ውስጥ ጥሩነሽ ዲባባ፣ አልማዝ አያናና ገንዘቤ ዲባባ ተካተዋል።የሀገር አቋራጭ ሩጫው ንጉስ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበኩሉ ከለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውጭ ሆኗል።

አትሌት ቀነኒሳ አሁን ያለኝ ብቃት በለንደን ማሸነፍ የሚያስችለኝ አይደለም በማለቱና ከፌዴሬሽኑ ጋረ በመስማማቱ ከቡድኑ ውጭ ሆኗል።

በ800 ሜትር ወንዶች
1 መሃመድ አማን
2 ማሙሽ ሌንጮ

በ800 ሜትር ሴቶች
1 ሀብታም አለሙ
2 ኮሬ ቶላ
3 ማህሌት ሙሉጌታ

በ1500 ሜትር ሴቶች
1 ገንዘቤ ዲባባ
2 ጉዳፋይ ጸጋዬ
3 በሱ ሳዶ

በ1500 ሜትር ወንዶች
1 አማን ወጤ
2 ሳሙኤል ብርሃኑ
3 ተሬሳ ቶ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በአንደኝነት አጠናቀቀች

African-Youth-AthleticsJuly 4, 2017 - 13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ላይ የተካፈለችው ኢትዮጵያ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቃለች። በአልጀሪያ ቴልማስ ከተማ ሲካሄድ የነበረው 13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል።

በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው ኢትዮጵያም 13 ወርቅ፣ 13 ብር እና 12 ነሃስ ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችላለች። በዚህም በድምሩ 38 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ 13ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በአንደኝነት ማጠናቀቅ ችላለች።
ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ400 ሜትር፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር፣ በእርምጃ ውድድር እንዲሁም በመሰናክል ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያ ካገኘችባቸው የስፖርት አይነቶች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

ደቡብ አፍሪካ በ12 ወርቅ፣ 4 ብር እና 1 የነሃስ ሜዳሊያዎች በድምሩ 17 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችላለች። አዘጋጇ አልጄሪያ 4 ወርቅ፣ 8 ብር እና 8 የነሃስ ሜዳሊያዎች በድምሩ 20 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ውድድሩን በ3ኛ በመሆን ማጠናቀቅ ችላለች።
እንዲሁም ኬንያ 4 ወርቅ፣ 4ብ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሰባት ወርቆች በማግኘት በአንደኝነት እየመራች ነው።

Ethiopia-Leading-African-Youth-AthleticsJuly 2, 2017 - 13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአልጀሪያ ቴልማስ ከተማ  ውስጥ በመካሄድ ላይ ሲሆን ፤ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በድረ-ገጹ እንዳስነበበው፥ ኢትዮጵያ በሰባት ወርቅ፣ አራት ብርና ሰባት ነሐስ፣ በድምሩ 18 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ እየመራች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ400 ሜትር፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር፣ በእርምጃ ውድድር እንዲሁም በመሰናክል ውድድሮች የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በስድስት ወርቅ፣ በሶስት ብርና በአንድ ነሐስ በድምሩ በ10 ሜዳሊያ በሁለተኛነት ትከተላለች።

በ2007 ዓ.ም ኢትዮጵያ ባስተናገደችው 12ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ናይጄሪያ በ12 ወርቅ፣ በ8 ብርና በ7 ነሐስ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ እንደነበረች ይታወሳል። ደቡብ አፍሪካ በ9 ወርቅ፣ በ7 ብርና በ7 የነሐስ ሜዳሊያ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ በ6 ወርቅ፣ በ12 ብርና በ10 የነሐስ ሜዳሊያዎች በሦስተኛ ደረጃ ነበር ያጠናቀቀችው።

በአልጄሪያ በመካሄድ ላይ የሚገኘው 13ኛው የአፍሪካ

Archived News

No News to show