አዳዲስ የኢትዮጽያ ዜናዎች - ስፖርት ሌላ

አምስተኛው አለም አቀፍ የ"ቱር መለስ" የብስክሌት ውድድር በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው

Cycling-Hawassa-EthiopiaAugust 29, 2017 - አፍሪካንና  አውሮፓን ያሳተፈ አምስተኛው  አለም አቀፍ የ"ቱር መለስ" የብስክሌት ውድድር በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ ውድድሩ በአለም አቀፍና በአፍሪካ ብስክሌት አሶሴሽን ከኢትዮጵያ የብስክሌት ፌደሬሽን፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ፣ ትግራይ እና ደቡብ ህዝቦች  ክልሎች ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው፡፡

መነሻውን ሀዋሳ አድርጎ 120 ኪሎ ሜትርና አራት የውድድር አይነቶችን የሚሸፍነው የብስክሌት ውድድር ወንዶ ገነት፣ ሻሸመኔና ጥቁር ውሀ ከተሞችን ያካለለ ዛሬ ተካሂዷል፡፡ ነገ ደግሞ አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ውድድር ይጀምራል፡፡

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት መበጀመሪያው ውድድር ኢትዮጵያ 12 ተወዳዳሪዎች በማሳተፍ ተካፍላለች፡፡  ከኢትዮጵያ ሌላ በአፍሪካ ሩዋንዳ፣ ብሩኪናፋሶ፣ ኬኒያ፣ አልጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ጅቡቲ፣ ናይጄሪያና ጋና ከአውሮፓ ደግሞ የጀርመን ብስክሌተኞች ተሳትፈዋል፡፡

አሁንም ከአፍሪካ የግብፅ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኮትዲቫር፣ የካሜሮን የዙምባዌ፣ የሱዳንና የታንዛኒያ ተወዳዳሪዎች የተካፈሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከ140 በላይ

Archived News

No News to show