የእንግሊዝ ኩባንያዎች የገናሌ ዳዋ ቁጥር 6 የኃይል ማመንጫና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ሊገነቡ ነው

Companies-to-invest-USD850-hydroFebruary 6, 2017 - የእንግሊዝ የታዳሽ ኃይል ኩባንያዎች ከ 850 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የገናሌ ዳዋ ቁጥር 6 የኃይል ማመንጫና የመስኖ ፕሮጀክቶችን ሊገነቡ ነው።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ የእንግሊዝ የታዳሽ ኃይል ኩባንያዎች ግሎብሌክና አጋሮቹ የልዑካን ቡድንን ዛሬ በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።

የካምብሪጅ ኢንዱስትሪዎች የኮርፖሬት ጉዳዮችና ዋና አማካሪ የሆኑት አሌክስ ስቴዋርት ለጋዜጠኞ  እንደገለጹት ኩባንያዎቹ 250 ሜጋ ዋት የሚያመነጨውን ገናሌ ዳዋና የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታን ያከናውናሉ።

የመስኖ ፕሮጀክቱ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች 27 ሺህ ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል።

እናም ኩባንያዎቹ ባለፉት ሦስት ዓመታት በገናሌ ዳዋ 6 የኃይል ማመንጫ ግንባታ በማህበራዊና አካባቢያዊ ላይ ሊኖረው ስለሚችለው ተጽዕኖ የዳሰሳ ጥናት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል።

ለሁለቱም ፕሮጀክቶች ግንባታ ከ 850 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገንዘብ የተመደበ ሲሆን ለ 55 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል ያስገኛል ብለዋል።

የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በዚህ የበጀት ዓመት የሚጀመር ሲሆን በአምስት ዓመት ውስጥም ይጠናቀቃል ነው የተባለው።

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በዚሁ ጊዜ በኃይል ዘርፍ ልማት ለሚሰማሩ ኩባንያዎች መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

በተለይ በታዳሽ ኃይል ልማት ለሚሰማሩ እንደ ግሎብሌክ ያሉ ኩባንያዎች መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው ያረጋገጡት።

የገናሌ ዳዋ 6 የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ከእንግሊዙ ሲ.ዲ.ሲ ፈንድና ከኖርዌይ መንግሥት በተገኘ ድጋፍ የሚከናወን ነው። (ENA)


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :