የኢትዮጵያ ቱሪዝም መለያው ˝ምድረ ቀደምት˝ መሆኑ አስታወቀ

Ethiopia-land-of-originMarch 22, 2017 - የኢትዮጵያ ላንድ ኦፍ ኦሪጅን በሚል የተዋወቀው የኢትዮጵያ የቱሪዝም መለያ ብራንድ የአማርኛ ትርጉሙ ˝ምድረ ቀደምት˝ በሚል ተተርጉሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ይፋ መደረጉ ፋና ዜና ዘገበ።

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ በየጊዜው የሚነሱ ተመሳሳይ ችግሮችን ለመፍታት አሁንም ከፍተኛ ትኩረትና የቅንጅት ስራ እንደሚያስፈልግ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም ባቀረቡት ሪፖርት ተጠቅሷል።

በቱሪዝም ድርጅት በኩልም በተመሳሳይ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የገበያ እና የማስተዋወቅ ስራ ለመስራት የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በመዳረሻ ቦታዎች የመግቢያ ክፍያዎች፣ በመስተንግዶና በአገልግሎት ደግሞ በድንገት የዘፈቀደ ጭማሪዎች መኖር እንደሁም ተመሳሳይነት ያለው የመሬት አቅርቦት በየክልሎችና መዳረሻዎች አለመኖር በክፍተት ተነስቷል።

ከምክር ቤቱ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል።

ከእነዚህም መካከል ዘርፉን በማስተዋወቅ ስራውም ሆነ ሌሎች ስራዎች በሚፈለገው ልክ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እየተደገፉ አለመሆኑ ተነስቷል።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ ጌታሁን መኩሪያ፥ ኢትዮጵያ ከጎረቤት የአፍሪካ ሀገራት ልምድ መውሰድ አለባት፤ እነዚህ ሀገራት ቴክኖሎጂን አደንን እና ወረርሽኝን መቆጣጠሪያ እስከማድረግ ደርሰዋል ብለዋል።

ከፓርኮች እና ከዱር እንስሳት ጥበቃ ጋር በተያያዘ የሚነሱት ችግሮችም አሁንም እንደ ችግር ከመነሳት ባለፈ እንዳልተፈቱ ነው የተነሳው።

ህብረተሰቡ በሚገባ ስለፓርኮቹ እንዲይውቅ አለመደረጉና በፓርኮች ጉዳይ ላይ የሚመለከታቸው ተቋማት በጋራ አለመስራታቸው ሁሌም ችግሩ መፍትሄ አልባ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል የአፋር ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ መሃመድ መሃመዴ። (FBC)


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :