ብሔራዊ የጋራና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ

satellite-platform-launchedApril 21, 2017 - ኢትዮ ሳት የተሰኘ ብሄራዊ የጋራ እና የተቀናጀ የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት ማዕቀፍ ተዘጋጀ ሲል ፋና ዜና አስታወቀ።

የቴሌቪዥን ስርጭት ሳተላይት ማዕቀፉ የሚዲያ እኩልነትንና ፍትሃዊነትን እንዲሁም ተደራሽነትን በማረጋገጥ በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚናን ይጫወታል ተብሏል።

ኢትዮ ሳት የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሳተላይት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የተዘጋጀ ሲሆን፥ ለሳተላይት ኪራይ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረትና የመረጃውን ደህንነት በመቆጣጠር ረገድ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ተክለብርሀን ወልደአረጋይ ተናግረዋል።

ሳተላይቱ በሀገር ውስጥ ያለውን የሚዲያ ተደራሽነት በማስፋት ከሞገድ አጠቃቀም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያስችላልም ነው የተባለው።

በሀገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ሊደረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኘው ሳተላይቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ አስራ አንዱም ክልሎች የቴሌቪዥን ስርጭታቸውን በአንድ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የሀገር ውስጥ የግልና የህዝብ የቴሌቪዥን ቻናሎችንም በሳተላይቱ በዝቅተኛ ክፍያ ለመጠቀም የሚያስችል አሰራርም ተዘርግቷል።

ሳተላይቱ ሌሎችም አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃኖችን መጠቀም እንዲያስችል ተደርጎ የተዘጋጀና ሲሆን፥ አሁን ላይ የቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ ተቋማት በቀላሉ ሳተላይቱን እንዲጠቀሙ ተደርጎም ነው የተዘጋጀው።

የፊታችን ሰኞ የሙከራ ስርጭቱን የሚጀምረው አዲሱ ሳተላይት አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቆ በ2010 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ መደበኛ ተግባሩን ይጀምራል። (FBC)


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :