ዳንጎቴ ከኢትዮጵያ ሊወጣ እንደሚችል አስጠነቀቀ

Dangote-May-Shut-Ethiopian-PlantNovember 23, 2017 - ንብረትነቱ የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊየነር የሆኑት የናይጄሪያዊ  አሊኮ ዳንጎቴ የሆነው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ በኢትዮጵያ የሚገኘውን ፋብሪካውን ሊዘጋ እንደሚችል አስጠነቀቀ፡፡

የፋብሪካው አመራሮች ይህንን የተናገሩት ፋብሪካው የሚገኝበት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የስሚንቶ ፋብሪካዎች ለስሚንቶ ማምረት ግብዓትነት የሚውለውን  ፑሚስ የተባለ ማዕድን ማምረቻ ለወጣቶች ማስረከብ እንዳለባቸው ካዘዘ በኋላ ነው፡፡

ተቀማጭነታቻው ሌጎስ የሆነው የድርጅቱ ዳይሬክተር ኤድዊን ዴቫኩማር እንዳሉት ከሆነ በህንፃም ሆነ በመሳሪያ አያያዝ ላይ የሚፈጥሩ ጥቃቅን ስህተቶች ጠቅላላ የፋብሪካውን ስራ ሊያቃውሱ ይችላሉ፡፡‘ይህ ግልፅ የሆነ የመብት ጥሠት ነው፡፡ መንግስት አንዴ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ ሠጥቶናል፡፡ እኛ በምንፈልገው መጠን የኖራ እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ካላገኘን ፋብሪካው ስራውን ማከናወን አይችልም ’ ሲሉም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ በዚህ ሳምንት ለፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጥያቄ እንደሚያቀርብና  ጥያቄው ተሰሚነትን ካላገኘ ከአዲስ አበባ በ90 ኪሎ ሜትር ርቀት ሙገር ውስጥ የሚገኘውን ፋብሪካውን እንደሚዘጋ አስጠንቅቋል፡፡

ዳንጎቴ ናይጄሪያን ጨምሮ በ አስር የአፍሪካ አገሮች  ውስጥ በሲሚንቶ ማምረት ኢንቨስትመንት  ላይ የተሠማራ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ፣ በናይጄሪያ እና በደቡብ አፍሪካ ላይ የተለየ ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል፡፡

ጉዳዩን አሰመልክቶ ለብሉምበርግ አስተያየታቸውን የሠጡት የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርት ባለስልጣን ሃላፊ አቶ ተክሌ ኡማ እንዳሉት ከሆነ ‘የክልሉን ደንቦችና ህጎች አክብሮ እስከተንቀሳቀሰ ድረስ የትኛውንም ኢንቨስትመንት የማፈናቀል ሀሳብ የለንም፡፡ ይህ ለዳንጎቴም ይሠራል፡፡’ ብለዋል፡፡ ሃላፊው አያይዘውም የኦሮሚያ ክልልዊ መንግስት ቅሬታ ካለው ከማንኛውም አካል ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነው ፤ ማንኛውም ኢንቨስትመት ሊመጣና ሊሄድ ይችላል ብለዋል፡፡

የፌደራል የማዕድን፣ የነዳጅ እና ጋዝ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ ሞቱማ መቃሳ በበኩላቸው እስከ አሁን ድረስ ከዳንጎቴ ሲሚንት በኩል ምንም ዓይነት ቅሬታ እንዳልሰሙ ተናግረዋል፡፡

ዳንጎቴ እስከ አሁን ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ 700 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ኢንቬስት አድርጓል፡፡ ድርጅቱ ተጨማሪ ማስፋፊያዎችን ለማድረግ በሂደት ላይ የነበረ ሲሆን በዚህ አለመግባባት የተነሣ የማስፋፊያ ስራውን ማቆሙን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡ ብሉምበርግ  


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :