መስፍን ኢንዱስትሪያል በውቅሮ ያቋቋመውን የትራክተር መገጣጠሚያ አስመረቀ

Mesfin-IndustrialJuly 24, 2017 - መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪን ኩባንያ በውቅሮ ከተማ ያቋቋመውን የትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ ትናንት አስመርቋል።የኩባንያው ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍተ ሓዱሽ በወቅቱ እንደገለፁት ፋብሪካው በወር 240 ትራክተሮችን የመገጣጠም አቅም አለው።

''ሶናሊካ'' ከተባለው የህንድ ኩባንያ ጋር በመተባበር በፋብሪካው የሚገጣጠሙ ትራክተሮች ከ20 እስከ 110 የፈረስ ጉልበት ያላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

የትግራይ መልሶ ማቋቋም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍን በበኩላቸው፥ "በትግራይ መልሶ ማቋቋም ስር የሚገኙ ተቋማት ሀገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት እየደገፉ ናቸው" ብለዋል። ተቋማቱ ከተለያዩ የውጭ ኩባንያዎች ጋር በሚፈጥሩት ትብብር፥ የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን ለማጎልበት አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኪሮስ ቢተው፥የትራክተር መገጣጠሚያ የክልሉ አርሶ አደሮችን የቆየ ዘመናዊ ማረሻ ይቅረብልን ጥያቄን የሚመልስ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ በግብርና ስራ የተሰማሩት ባለሃብቶችም ከ40 ዓመታት በፊት የያዟቸው ትራከተሮች፥ በመለዋወጫ እጦትና በእርጅና የተፈለገውን አገልግሎት ሳይሰጡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ የትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካው በአቅራቢያቸው መቋቋም ብክነቱን በማሰቀረት የእርሻ ስራቸውን በአግባቡ ለማካሄድ አቅም እንደሚፈጥር መናገራቸውን ኢዜአ በዘገባው ጠቅሷል፡፡

ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :