በለንደኑ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉት የኢትዮጵያ ልዑካን ሽልማት ተሰጠ
August 21, 2017 - በለንደን አስተናጋጅነት በተካሄደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ትናንት ማምሻውን በአራራት ሆቴል በተካሄደ ስነ ስርዓት ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሻምፒዮናው ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ብር ሸልሟል፡፡ፌዴሬሽኑ የብር ሜዳሊያ ላስገኙ ደግሞ 30 ሺህ ብር አበርክቷል፡፡
ልዩ ተሸላሚ ናቸው ላላቸው ዮሚፍ ቀጄልቻና ለአልማዝ አያና አሰልጣኝና ባለቤቷ ለሆኑት ሶሬሳ ሲዳ ለእያንዳንዳቸው 40 ሺህ ብር ሸልሟል፡፡የልዑኩ መሪ የነበረው አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረ ማርያም የተሸለመውን 40 ሺህ ብር፥ በውድድሩ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ እንድታገኝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከተው ዮሚፍ ቀጄልጃ አበርክቶለታል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በበኩሉ ወርቅ ላስገኙ አትሌቶች የ20 ሺህ ብር ሽልማት ሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ የልዑኩ አባል ለነበሩ ከ8 ሺህ ብር ጀምሮ ሽልማት መሰጠቱ ነው የተነገረው፡፡
ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ