ሞ ፋራሕ በዙሪክ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን አሸነፈ

Mo-Farah-winsAugust 25, 2017 - ትናንት ምሽት በተካሄደው የስዊዘርላንድ ዙሪክ ዳይመንድ ሊግ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ከፍተኛ ትንቅቅ ታይቶበት ተጠናቋል። ውድድሩ ላይም በእንግሊዛዊው ሞህ ፋራህ፣ በኢትዮጵያውያኑ ሙክታር አድሪስ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ መካከል ከፍተኛ ትንቅንቅ ታይቶበታል።

በመጨረሻም ውድድሩ በሞህ ፋራህ አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ኢትዮጵያውያኑ ሙክታር እድሪስ እና ዮሚፍ ቀጄልቻ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

ንግሊዛዊው ሞህ ፋራህ ውድድሩን 13 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ05 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውደድሩን በአሸናፊነት አጠናቋል።

ሙክታር አድሪስ 13 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ09 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በሁለተኝነት ሲያጠናቅቅ፤ ዮሚፍ ቀጄልጃ 13 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ18 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቋል።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሰለሞን በርጋ 13 ደቂቃ ከ07 ሰከንድ ከ35 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአራተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል።

አሜሪካዊው ፓውል ኬፕኬሚዮ ቼሌሞ ከሞህ ፋራህ በመቀጠል ሁለተኛ ሆኖ ገብቶ የነበረ ቢሆንም ውደድሩ ላይ ሌላ አትሌት በመግፋቱ ውጤቱ እንዲሰረዝ ተደርጓል።እንግሊዛዊው ሞህ ፋራሀም የመጨረሻውን የመም (ትራክ) ውድድር በድል ማጠናቀቅ ችሏል

ምንጭ፡ ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :