በኬፕ ታውን ማራቶን ኢትዮጵያውያን በሁለቱም ፆታዎች አሸንፈዋል

Cape-Town-Marathon-EthiopiaSeptember 19, 2017 - በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች አሸንፈዋል።

በወንዶች አትሌት አሰፋ መንግስቱ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቂ ከ01 ሰኮንድ በመግባት ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን ከተማ በቀለ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

ከተማ የገባበት ጊዜ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ሲሆን፥ ኬንያዊው ዱንካን ማዮ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ826 ሰከንደ በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

አትሌት አሰፋ ከውድድሩ በኋላ በሰጠው አስተያየት በውድድሩ በ2016 በራሱ ተይዞ የነበረውን የቦታውን የ2 ሰዓት ከ08 ደቂቃ 42 ሰኮንድ ክብረወሰን ለመስበር አስቦ እንደነበር ገልጿል።

ከፍተኛ የነፋስ ግፊት ፍጥነቱን እንዳይጨምር ስላደረገው ክብረ ወሰኑን ባያሻሽልም፥ ሁሉም ነገር ጥሩ ከሆነ በቀጣይ ዓመት በኬፕታውን ማራቶን በመሳተፍ የራሱን ክብረወሰን ለማሻሻል ጥረት እንደሚያደርግ ጠቁሟል።

በውድድሩ በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ቤተልሔም ሞገስ 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ከ22 ሰከንድ በመግባት አንደኛ ሆናለች።

ናሚቢያዊቷ ሄላሊያ ጆሃንስ 2 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ከ28 ሰኮንድ በማጠናቀቅ ቤተልሄምን ተከትላ ሁለተኛ ወጥታለች።

ሶስተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ኬንያዊቷ አግነስ ጄፕኬምቦይ ኪፕሮፕ ስትሆን፥ 2 ሰዓት ከ31 ደቂቃ ከ00 ሰከንድ ውድድሩን ያጠናቀቀችበት ጊዜ ነው።

ምንጭ- ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :