የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመልስ ጨዋታ የኬንያ አቻውን ይገጥማል

Ethiopia-women-under-20የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለመልስ ጨዋታ ወደ ኬንያ አቅንቷል ቡድኑ በ2018 ፈረንሳይ ለምታስተናግደው ከ20 ዓመት በታች ሴቶች የዓለም ዋንጫ የመጀመርያ ዙር የመልስ ጨዋታውን ለማድረግ ነው ወደ ናይሮቢ የተጓዘው።

በአሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ የሚመራዉ ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመርያ ጨዋታውን ከኬንያ አቻው ጋር በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም አድርጎ ሁለት አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

በምርቃት ፈለቀ እና አለምነሽ ገረመው የመጀመርያ አጋማሽ ሁለት ግቦች 2-0 መምራት ቢችሉም፥ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ኬንያዎች ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች 2-2 ወጥተዋል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን በመልሱ ጨዋታ የማለፍ እድሉ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።

አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ የሚመሩት ብሄራዊ ቡድኑ ባለፉት 10 ቀናት በሀዋሳ ከተማ በጨዋታው በታዩ ደካማ ጎኖች ላይ በማተኮር ጠንካራ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር ለማለፍ የሚያስችለውን ውጤት ለማስመዝገብ የቡድኑ አባላት የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

26 የልኡካን ቡድን በመያዝ ዛሬ ወደ ኬንያ ያቀናው ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመሪያው ጨዋታ ከነበሩት 18 ተጨዋቾች ውስጥ ብሩክታዊት አየለ ተቀንሳ ገነሜ ወርቁን አካቷል፡፡

ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :