የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከፈረንሳዩ የ2018 የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነ

Ethiopian-Women-Team-EliminatedOctober 1, 2017 - በዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ እየተካፈለ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከኬንያ ጋር ባደረገው የመልስ ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸንፏል።

የኬንያ ቡድን በ11ኛና በ52ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎችን ሲያስቆጥር፥ ኢትዮጵያ የማስተዛዘኛዋን ጎል በምርቃት ፈለቀ አማካኝነት በፍጹም ቅጣት ምት አግኝታለች።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በሜዳው ከኬንያ ጋር መስከረም 7 ቀን ያደረገውን ጨዋታ ሁለት አቻ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የኬንያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ 4 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል።ኬንያ በሁለተኛው ዙር በነገው እለት ጨዋታቸውን ከሚያደርጉት የአልጀሪያና የጋና አሸናፊ ጋር ትገናኛለች።ፈረንሳይ በምታስተናግደው ውደድር ላይ 16 ቡድኖች የሚካፈሉ ሲሆን፥ አፍሪካ በሁለት ቡድኖች የምትወከል ይሆናል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :