የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በፎርፌ ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር አለፈ

Ethiopia-women-under-17October 5, 2017 - የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በፎርፌ ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር አልፏል።ብሔራዊ ቡድኑ በ2018 በኡራጓይ አስተናጋጅነት በሚከናወነው ከ17 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያ ጋር ለማድረግ ተመድቦ ነበር።

ሆኖም ኬንያ ከውድድሩ ራሷን በማግለሏ ታዳጊዎቹ ሉሲዎች ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር በፎርፌ አልፈዋል። በአሰልጣኝ ሰላማዊት ዘርዓይ የሚሰለጥነው ቡድኑ 36 ተጨዋቾችን በመጥራት በወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ሜዳ በጥቅምት ወር ላለበት የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ልምምድ ማድረግ መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ተጋጣሚው የኬንያ ቡድን ጨዋታውን እንደማያደርግ መገለፁን ተከትሎ፥ የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታውን ለማድረግ እስከ ህዳር ወር አጋማሽ ድረስ ለመጠበቅ ይገደዳል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ዋና ፀሃፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ የኬንያን ከማጣሪያው ውጪ መሆን ለሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

ለኬንያ እግርኳስ ፌደሬሽን ቅርበት ካላቸው ምንጮች በተገኘ መረጃ የኬንያ ተማሪዎች እስከ ህዳር 7 ድረስ ፈተና ላይ ስለሆኑ፥ ተጫዋቾችን መልምሎ ወደ ውድድር ለመግባት ፌዴሬሽኑ በመቸገሩ ከማጣሪያው ውጪ መሆንን መርጧል፡፡

የኬንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከውድድሩ ውጪ መሆኑን በይፋ ለሚዲያ በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡የኢትየጵያ ብሔራዊ ቡድን በአንደኛው የማጣሪያ ዙር ከናይጄሪያ ጋር ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።
 
ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :