ኤ ቲ ኤም ካርድ በመጠቀም ወቅት በስህተት ገንዘብ የሚወስድባቸው ኢትዮጵያውያን ምሬታቸውን ገለፁ

Ethiopian-ATMOctober 15, 2017 - በኤ ቲ ኤም ካርድ ገንዘብ በማውጣቱ ሂደት በስህተት ከባንክ ሂሳባቸው የሚወሰድ ገንዘብ በአግባቡ እና በፍጥነት እየተመለሰልን አይደለም ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች አማረሩ። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደዘገበው ከሆነ ከሚያጋጥም የኔትወርክ መቆራረጥ እና ካርድ ማስቀረት በተጨማሪ በተለያዩ ምክንያቶች ያዘዙትን ገንዘብ የማይቀበሉበት እና ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ የሚቀንስበት ሁኔታ ያጋጥማቸዋል።

በእነዚህ ችግሮች ሂደት ውስጥ በስህተት ከሂሳባቸው የሚቀነስ ገንዘብ በአግባቡ እና በፍጥነት እየተመለሰላቸው አለመሆኑን ነው የገለፁልን። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ካነጋገራቸው ደንበኞች መካከል ከሳምንት እስከ አንድ ወር ለሚደርስ ጊዜ ገንዘባቸው ሳይመለስላቸው የቆዩ እንደሚገኙም መታዘብ ችሏል። ስለጉዳዩ የተጠየቁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ በልሁ ታከለ፥ የባንኩ ደንበኛ ሆነው በሌሎች ንግድ ባንኮች ኤቲኤም ተጠቅመው ገንዘባቸው ለሚቆረጥባቸው ደንበኞች ምላሽ ለመስጠት ሂሳብ የማጥራት ስራ በየቀኑ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ነገርግን አንዳንድ ጊዜ ደንበኞች የተጠቀሙበትን የየትኛው ባንክ ኤ ቲኤ ም መሆኑን ካለማስታወስ እና እንደተቆረጠባቸው ወዲያውኑ ሪፖርት ካለማድረግ የተነሳ ገንዘቡ የሚመለስበት ጊዜ ሊራዘም እንደሚችል ገልፀዋል።

በአጠቃላይ ግን ባንኩ በኤ ቲ ኤም ማሽን ገንዘባቸው የተቆረጠባቸው የየትኛውም ባንክ ደንበኞች የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ እና በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ እንደሚያድርግ ነው ያብራሩት፡፡

ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :