በፊፋ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ የኢትዮጵያ ደረጃ ወደ 151ኛ አሽቆለቆለ

Ethiopia-FIFAOctober 16, 2017 - በአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ወደ 151ኛ አሽቆልቁላለች።በወርሃዊው የእግር ኳስ ደረጃ ኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከነበረችበት 144ኛ ደረጃ 7 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 151ኛ ላይ ተቀምጣለች።

ኢትዮጵያ በተከታታይ ወራት ከፍተኛ የደረጃ መንሸራተት እያስመዘገበች ትገኛለች።ወርሃዊውን የፊፋ የሃገራት ደረጃ የብራዚሉ የአለም ዋንጫ አሸናፊ ጀርመን ስትመራው ብራዚልና ፖርቹጋል ደግሞ ይከተሏታል።

ጀርመን በ1 ሺህ 631 ነጥቦች ስትመራ ብራዚል በ1 ሺህ 619 ነጥብ ትከተላታለች።ፖርቹጋልና አርጀንቲና በአንድ ነጥብ ተበላልጠው ተከታዮቹን ደረጃዎች ሲይዙ፥ ቤልጂየምና ፖላንድ ባለፈው ወር በነበሩበት 5ኛ እና 6ኛ ደረጃ ላይ ፀንተዋል።

ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ቺሊ እና ፔሩም እስከ 10 ባለው ደረጃ መካተት ችለዋል።ቱኒዚያ 28ኛ ደረጃን በመያዝ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን ግብጽ እና ሴኔጋል 30ኛ እና 32ኛ በመሆን ይከተላሉ።ከአፍሪካ ምድብ ቀድማ የአለም ዋንጫ ትኬት የቆረጠችው ናይጀሪያ ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ በመሆን ከአፍሪካ 5ኛ ደረጃን ይዛለች።

አንጉሊያ፣ ባህማስ፣ ኤርትራ፣ ጅብራልተር፣ ሶማሊያ እና ቶንጋ ደግሞ አሁንም ያለምንም ነጥብ በደረጃው ግርጌ ላይ ይገኛሉ።በወሩ ተርክሜኒስታን 22፣ ላቲቪያ 19 እንዲሁም መቄዶንያና ኦስትሪያ 18 ደረጃዎችን በማሻሻል የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።በአንጻሩ ኢኳዶርና ሊዩቴኒያ 25፣ አዘርባጃን 23፣ አንቲጓና ባርቡዳ 19 እንዲሁም ሞንቴኔግሮ 17 ደረጃዎችን አሽቆልቁለዋል።

ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :