የኢትዮጵያ የፕሪምየር ሊግ ተጀመረ
November 5, 2017 - በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2010 የውድድር ዘመን መክፈቻ ጨዋታዎች በተለያዩ ከተማዎች ተካሂደዋል።
የዛሬዎቹ ሶስት ጨዋታዎች በተመሳሰይ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ተካሂደዋል።
ወልዲያ ላይ ወልዲያ እና አዳማ ከተማ ተገናኝተው በወልዲያ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸናፊነት ተጠናቋል። አርባ ምንጭ ላይ ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ እና መቀሌ ከተማ ተገናኝተው 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል።
ጅማ ላይ፥ ጅማ አባ ጅፋር ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። እሁድ አዲግራት ላይ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ፋሲል ከተማ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ።
ምንጭ፡- ሶከር ኢትዮጵያ