የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ ያደርጋል

Ethiopian-football-federationNovember 22, 2017 - የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬ  እለት እንደሚያደርግ አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም ባጠናቀቀው 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ፥ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ የሚካሄድበትን ቀን በ45 ቀን ማራዘሙ ይታወሳል።

በነገው እለት በሚያካሂደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውም በፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ዙሪያ እንደሚወያይ ይበቃል። ከዚህ ባለፈም አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚመርጥ እና የምርጫ ደንብ ውይይት እንደሚያካሂድም ይጠበቃል።

ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች እጩዎቻቸውን ለፌዴሬሽኑ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።ለፕሬዚዳንትነት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከሁለት በላይ እጩዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። :

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ በ10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ጠቅላላ ምርጫው ደግሞ በሌላ ጊዜ እንዲካሄድ በአብላጫ ድምፅ መወሰኑ የሚታወስ ነው።

በዚህም መሰረት ምርጫው ከ45 ቀናት በኋላ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እንዲካሄድ ነው ጉባዔው የወሰነው።

ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :