የኢንተርናሽናል እግር ኳስ ዳኛ ባምላክ ተሰማ ከካፍ የዓመቱ ምርጥ እጩ ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

Bamlak-Tessema-Ethiopia-FootballNovember 29, 2017 - ከካፍ የዓመቱ ምርጥ ስድስት እጩ ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል እግር ኳስ ዳኛ ባምላከ ተሰማ አንዱ ሆኗል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የ2017 የዓመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን፣ ክለብ፣ አሰልጣኝ፣ ተጫዋች እና ዳኛ እጩዎች ይፋ አድርጓል።

በፈረንጆች 2017 ዓመት በካፍ የዓመቱ ምርጥ ዳኛ በእጩነት የተካተቱት ባካሪ ጋሳማ ከጋምቢያ፣ ባምላክ ተሰማ ከኢትዮጵያ፣ አብዲ ቻሪፍ ከአልጀሪያ፣ ጅሄድ ግሪሻ ከግብጽ፣ ጃኒ ስካዝዊ ከዛምቢያ እና ማላግ ዳይዲሆ ከሴኔጋል ናቸው።

ባምላከ ተሰማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ፣ በቻን ማጣሪያ እና በዘንድሮው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የግብጹን አልአሃሊ እና የሞሮኮው ዋይዳድ ካዛብላንካን በመሀል ዳኝነት መምራት ችሏል።

ፊፋ በያዝነው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በሩሲያ የሚካሄደውን የአለም ዋንጫ ለመምራት ብቁ ያላቸውን ዳኞች ይፋ ሲያደርግ ከአፍሪካ ከተመረጡት ጥቂት ዳኞች መካከል ባምላክ አንዱ ሆኗል።

ጋምቢያው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባካሪ ጋሳማ በካፍ የዓመቱ ምርጥ ዳኛ መመረጥ ከጀመረበት እኤአ 2011 ጀምሮ አራት ጊዜ የዓመቱ ምርጥ ዳኛ በመሆን ተመርጧል።

ባካሪ የአለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎችንና የአፍሪካ ዋንጫን የፍጻሜ ጨዋታ መምራት የቻለ ስመ ገናና ዳኛ ነው፡፡

የካፍ እኤአ የ2017 የዓመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን ፣ክለብ ፣አሰልጣኝና ዳኛ ሆነው ከቀረቡት እጩዎች መካከል አሸናፊዎቹ ታህሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም በጋና መዲና አክራ የሚታወቁ ይሆናል።
 
ምንጭ፡ ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :