አትሌት ዝናሽ ገዝሙ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

Zinash-Gezmu-Ethiopian-Athlete-deadDecember 1, 2017 - ዋሪነቷን በፈረንሳይ ሀገር አድርጋ የነበረችው የ29 አመቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት ዝናሽ ገዝሙ ከዚህ አለም በሞት መለየቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የእትሌቷን ህልፈት ከስፍራው በደረሰው መረጃ ማረጋገጥ መቻሉንም አስታውቋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 በአምስተርዳም በተካሄደ የማራቶን ውድድር ላይ ተካፍላ 2:32:48 በሆነ ሰዓት 6ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ አይዘነጋም።

የአትሌት ዝናሽን የአሟሟት ምክንያትና ሁኔታ ፌዴሬሽናችን እያጣራ የሚገኝ መሆኑን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

አትሌቷ ከሀገሯና ከፌዴሬሽኑ ለረጅም ጊዜ እርቃ መኖሯ ሙሉ መረጃውን በቀላሉ አግኝቶ ለማድረስ አስቸጋሪ እንዳደረገውም ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ስለአጠቃላይ የአሟሟቷ ሁኔታ ለአትሌቲክስ ስፖርት ቤተሰቡ መረጃውን እንደሚያደርስ አስታውቋል።

ፌዴሬሽኑ በአትሌት ዝናሽ ገዝሙ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን የገለፀ ሲሆን፥ ለመላው ቤተሰቦቿና ለወዳጅ ዘመዶቿ ፍጹም መጽናናትን ተመኝቷል።

ምንጭ፡- ኤፍ.ቢ.ሲ


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :