የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቡሩንዲ 4 ለ1 ተሸነፈ

Burundi-national-teamDecember 7, 2017 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር በቡሩንዲ አቻው 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸነፈ።የ2017 የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና (ሴካፋ) ውድድር በኬኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ ጨዋታ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ያደረጉት ዋልያዎቹ በቡሩንዲ ብሄራዊ ቡድን ሽንፈትን አስተናግደዋል።

ማክሰኞ እለት ደቡብ ሱዳን 3 ለ 0 ያሸነፉት ዋልያዎቹ ምድቡን በሶስት ነጥብ መምራት ችለው ነበር።

ይሁን እንጂ ዛሬ ሽንፈትን በማስተናገዳቸው ምድቡን ቡሩንዲ በአራት ነጥብ ስትመራ ኢትዮጵያ በሶስት ነጥብ በሁለተኝነት ለመቀመጥ ተገዳለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የምደቡን የመጨረሻ ጨዋታ እሁድ ከዩጋንዳ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።

በእሁዱ ጨዋታ ምድቡን በአንደኝነት ወይም በሁለተኝነት መያዝ የሚያስችላቸውን ነጥብ  ማስመዝገብ ከቻሉ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የሚቀላቀሉ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በተደለደለችበት ምድብ ሁለት ላይ አንድ አንድ ጨዋታ ያደረጉት የዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድንና የደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ቡድን እንደ ቅደም ተከተላቸው በአንድ ነጥብና  ካለምንም  ነጥብ ሶስተኛና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ምንጭ፡ኢ.ዜ.አ


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :