ኢትዮጵያ ከሴካፋ ውድድር ተሰናበተች

CECAFADecember 12, 2017 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2017 የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና ሴካፋ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

ትናንት በየምድቡ የመጨረሻ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን፥ በካካሜጋ ቡኩሁንጉ ስታዲየም ደቡብ ሱዳን እና ቡሩንዲ ባደረጉት ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ ተለያይተዋል።

የዋልያዎቹ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የማለፍ እድል በደቡብ ሱዳን ከሶስት ጎል ልዩነት በላይ የማሸነፍ እድል የተመሰረተ ቢሆንም፥ ቡድኖቹ አቻ በመውጣታቸው ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።

ከትናንት ወድያ በካካሜጋ ቡኩሁንጉ ስታዲየም የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፥ ከኡጋንዳ አቻው ጋር አንድ ለአንድ በሆነ ውጤት ተለያይቷል።

በዚህም መሰረት ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ በተመሳሳይ አምስት ነጥብ በግብ ክፍያ ተባላልጠው በቅደም ተከተል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ኡጋንዳ ውድድሩን 14 ጊዜ በማሸነፍ ሪከርዱን የያዘች አገር ናት።

ከየምድቡ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ያለፉት አራት አገራት የፊታችን ሐሙስ እና አርብ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ለ39ኛ ጊዜ በሚካሄደው የ2017 የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ሻምፒዮና ለፍፃሜው አላፊ አገራት እሁድ ታህሳስ 8 ቀን 2010 ዓ.ም ዋንጫውን ለማንሳት የሚፋለሙ ይሆናል።

ምንጭ፦ ኢዜአ


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :