መንግሥት የትምባሆ ድርጅት ላይ የነበረውን ድርሻ በ434 ሚሊዮን ዶላር ሙሉ በሙሉ ሸጠ
December 21, 2017 - መንግሥት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት ላይ የነበረውን የ30 በመቶ ድርሻ ሙሉ በሙሉ ጃፓን ቶባኮ ለተባለ ኩባንያ በ434 ሚሊዮን ዶላር አስተላለፈ፡፡ ክፍያው ዛሬ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ገዥው ኩባንያ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ይህ ሽያጭ ኩባንያው በድርጅቱ ላይ ያለውን ድርሻ ወደ 70 በመቶ አሳድጓል፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ መንግሥትን በመወከል የመንግሥት ልማት ድርጅት ሚኒስትሩ አቶ ግርማ አመንቴ ከጃፓን ቶባኮ ኩባንያ ተወካይ ጋር ተፈራርመዋል፡፡
ከብሔራዊ ትምባሆ ቀሪ ድርሻዎች 29 በመቶው ሼባ በተባለ የየመን ድርጅት ባለቤትነት ሥር ያለ ሲሆን፣ ቀሪው አንድ በመቶ በአንድ ግለሰብ ተይዟል፡፡
ምንጭ.:ሪፖርተር