ፌዴሬሽኑ 5 ተጫዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔዎችን አሳለፈ

Ethiopian-Football-FederationJanuary 1, 2018 - የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ በ7ኛ እና 8ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ተጫዋቾች በፈፀሙት የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።

በ8ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከወልዲያ ባደረጉት ጨዋታ ዳኛውን ለመማታት ሙከራ ያደረገው አማረ በቀለ 6 ወራት ከእግርኳስ እንዲታገድ እና 10 ሺህ ብር እንዲከፍል ተወስኖበታል።

በእለቱ ኤልያስ ማሞ ያስቆጠረው የፍጹም ቅጣት ምት እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው አማረ በቀለ ከፍጹም ቅጣት ምቱ ውሳኔ በኋላ ከዳኛው ጋር በገባው እሰጥ እገባ 62ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል።

የእለቱ አመራሮች ባቀረቡት ሪፖርት መሰረትም አማረ ዳኛውን ለመማታት ሙከራ ማድረጉ በመገለጹ ነው 6 ወራት ከእግር ኳስ እንዲታገድ እና 10 ሺህ ብር እንዲከፍል የተወሰነበት።በተመሳሳይ አማረ በቀለ ከሜዳ ከወጣ ከ3 ደቂቃ በኋላ የቀይ ካርድ የተመዘዘበት ብሩክ ቃልቦሬ የተጋጣሚ ተጫዋችን በቡጢ መማታቱ በሪፖርት በመገለፁ ለፈፀመው ጥፋት 4 ጨዋታ እና 4 ሺህ ብር ቅጣት ተጥሎበታል።

ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ከሀዋሳ ከተማ አቻ በተለያዩበት ጨዋታ የእለቱን ዳኞች አፀያፊ ስድብ እንደተሳደበ በጨዋታ አመራሮች ሪፖርት የተደረገበት ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን 3 ጨዋታ ቅጣት እና 3 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል። በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲግራት ላይ ወልዋሎ ከመከላከያ ባደረጉት ጨዋታ እርስ በእርስ ተደባድበው በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጡት የመከላከያው ሳሙኤል ሳሊሶ እና የወልዋሎው እንየው ካሳሁን እያንዳንዳቸው 4 ጨዋታ እና 4ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎባለቸዋል።

ምንጭ፦ soccerethiopia


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :