ቴዲ አፍሮ በባህር ዳር የሙዚቃ ኮንሰርት ሊያቀርብ ነው

Teddy-Afro-Concert-Bahir-DarJanuary 14, 2018 - በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ በባህር ዳር ከአንድ ሳምንት በኋላ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ዝግጅት፣ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደማይኖር ተገለጸ፡፡

‹‹የሙዚቃ ዝግጅቱን ሁሉም የሚፈልገው ስለሆነ የፀጥታ ችግር አይኖርም፤›› ሲሉ፣ የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ከዚህ ቀደም በክልሉ በተለይም በባህር ዳር የተለያዩ ጥቃቶች መድረሳቸው ይታወሳል፡፡ በተለይም በክልሉ ተቀስቅሶ በነበረው አመፅ በባህር ዳር ከተማ በተደጋጋሚ የቦምብ ጥቃቶች ደርሰው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ይህ የሙዚቃ ዝግጅት ለቴዲ አፍሮ ከአራት ዓመታት በኋላ የመጀመርያው የሚሆን ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በተለይም በአዲስ አበባ ለማድረግ ያቀረባቸው  ጥያቄዎች ሳይሳኩ ቀርተዋል፡፡

በተለይ ‹‹ኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ ለለቀቀው የሙዚቃ አልበም በሚሊኒየም አዳራሽ ሊያደርገው የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ፈቃድ ባለማግኘቱ መሰረዙ ይታወሳል፡፡  አልበሙን ለማስመረቅ በሒልተን ሆቴል አዘጋጅቶት የነበረው ዝግጅት በመጨረሻ ሰዓት የፀጥታ ችግር ሊፈጥር እንደሚል የፀጥታ አስከባሪ በሌለበት መካሄድ አይችልም በሚል ምክንያት መሰረዙ ይታወሳል፡፡

ቅዳሜ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. 60 ሺሕ ሰዎችን በሚይዘው የባህር ዳር ስታዲየም፣ ከ30 ሺሕ እስከ 40 ሺሕ ታዳሚዎች ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የቴዲ አፍሮ ማኔጀር አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹የሚያስፈልጉንን ዝግጅቶች እያጠናቀቅን ነው፤›› ሲሉ አቶ ጌታቸው ኮንሰርቱን ለማካሄድ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ በሙዚቃ ኮንሰርቱ ለመታደም ለመደበኛ 350 ብር፣ እንዲሁም ለቪአይፒ 1,000 ብር መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኮንሰርቱን በዋናነት ጆይ ፕላስና ኤፕላስ የተባሉ ድርጅቶች ናቸው የሚያዘጋጁት፡፡

ምንጭ:- ሪፖርተር


  እትምContact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :