የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ ነው

Beer-EthiopiaJanuary 23, 2018 - የቢራ ፋብሪካዎች የዋጋ ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ ቢጂአይ ኢትዮጵያ በምርቶቹ ላይ የዋጋ ጭማሪ አድርጎ ማከፋፈል መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአገሪቱ ውስጥ ቢራ ፋብሪካዎች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በማከፋፈያ ዋጋቸው ላይ የዋጋ ጭማሪ ያደርጋሉ ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ምንጮች የገለጹ ሲሆን፣ ቢጂአይ ግን ይህንን የዋጋ ጭማሪ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡

በዛሬው ዕለት ቢጂአይ የዋጋ ለውጡን ተግባራዊ መሆኑን የሚያረጋግጠው፣ በማከፋፈያ ዋጋ የሚረከቡ ሆቴሎች 214 ብር ያወርዱ የነበረውን አንድ ሳጥን ቢራ በ251 ብር መግዛታቸው ነው፡፡

በተመሳሳይ 590 ብር የሚያወርዱትን አንድ በርሚል ድራፍት በ700 ብር እንዲረከቡ መደረጋቸውን የተለያዩ ሆቴሎች ገልጸዋል፡፡

የቢራ ፋብሪካዎቹ ከሦስት ወራት በፊት የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ለጭማሪያቸው ምክንያት አድርገው የነበረው የውጭ ምንዛሪ ለውጥን ነበር፡፡ ሆኖም የፌዴራል የሸማቾች ጥበቃና የንግድ ውድድር ባለሥልጣን ጭማሪው ምክንያታዊ አይደለም በማለቱ ዋጋው ወደነበረበት እንዲመለስ ተደርጎ ነበር፡፡ ፋብሪካዎቹ አሁን የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል የተባለው፣ ከአዲሱ የምንዛሪ ለውጥ ወዲህ ጥሬ ዕቃ ማስገባት በመጀመራቸውና በተለይ የብቅል ዋጋ ጭማሪ በመደረጉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምንጭ:- ሪፖርተር


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :