የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ታገደ

MIDROC-Gold-MiningMay 10, 2018 - የሚድሮክ ጎልድ የለገደምቢ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ፍቃድ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን የኢፌዴሪ የማዕድን፣ ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል ጉጅ ዞን ሚድሮክ ጎልድ በለገደምቢ በሚያካሂደው የወርቅ ማዕድን ልማት ስራ ላይ የአካባቢው ነዋሪ፥ የኩባንያው የምርት ሂደት የአካባቢ ብክለት እያስከተለ ነው የሚል ቅሬታ ማንሳቱን ተከትሎ ነው ፍቃዱን ያገደው።

በገለልተኛ አካል ጥልቀት ያለው ጥናት እስከሚጠና ድረስ የኩባንያው ወርቅ የማምረት ስራው መታገዱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ጥናቱ በገለልተኛ አካል ከፌደራል እስከ ቀበሌ ያሉ አመራሮችን እና ባለ ድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እንደሚካሄድ፥ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ባጫ ፋጂ ተናግረዋል።

የኩባንያው ወርቅ የማምረት ሂደት መቀጠል ያለመቀጠል ሂደትም በጥናቱ ውጤት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

Source: FBC


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :