የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Girma-Woldegiorgis-deadDecember 15, 2018 - የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከቤተሰቦቻቸው እንዳረጋገጠው ፕሬዚዳንቱ ለሊት ማረፋቸውን ሰምቷል፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነ ስርዓትም የፊታችን ረቡዕ ታህሳስ 10 2011 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈፀመም ተነግሯል።

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ታህሳስ 19 ቀን 1917 ዓ.ም. ነበር በመዲናዋ አዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከ1994 እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ርዕሰ ብሔር ሆነው አገልግለዋል።

በጥቅሉ ፕሬዚዳንት ግርማ ኢትዮጵያን በርዕሰ ብሄርነት ለ12 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ የፓርላማ አባል በመሆን ነበር ሀገርንና ህዝብን ማገልገል የጀመሩት፡፡

የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሮሚኛ፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ጣሊያንኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋዎችን እንደሚችሉም ይነገራል፡፡

የፕሬዚዳንት ግርማ ባለቤት ከአንድ ዓመት በፊት ማረፋቸው የሚታወስ ሲሆን በጥቅሉ የአምስት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

Source: FBC


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :