ከጠ/ሚንሰትር አብይ ጋራ በግድቡ ዙሪያ በሩሲያ ለመነጋገር ተስማምተናል - ፕሬዝዳንት አልሲሲ

በኢዜጋ ሪፖርተር

Abiy-Al-SisiOctober 14, 2019 (Ezega.com) - የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ አልሲሲ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋራ እንደሚወያዩ ተናገሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ የሚደረገው ውይይት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከግድቡ የውሀ አያያዝና አለቃቀቅ ጋራ በተያያዘ የተፈጠረውን ውጥረት ለማረገብ ይረዳል በሚል ያቀረቡት ጥያቄ በጠቅላይ ሚንሰትር አብይ በኩል ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ከኢትዮጲያው ጠቅላይ ሚንስትር ጋር በሞስኮ ተገናኝተን ለመወያየት ተስማምተናል እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ነገሮች የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በሚያስችለን መንገድ ይጓዛሉ››

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ ውይይቱ የሚካሄድበትን ትክክለኛ ጊዜ ይፋ ባያደርጉም ሩሲያ ከ 10 ቀናት በኃላ ከምታስተናግው የሩሲያ-አፍሪካ የጋራ ጉባዔ ጎን ለጎን ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ አልሲሲ ጠቅላይ ሚንስትር  አብይ የ2019 አለም አቀፍ የሰላም ኖቤል ሽልማትን በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡ በእዚሁ ወቅት ነው እንግዲህ የ‹እንነጋገር› ጥያቄውን አቅርበው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀባይነትን ያገኙት ፡፡ የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ባሳም ራዲም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡ ‹‹ንግግሩ ከደስታ መልዕክቱ በተጨማሪ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግም የተነሳበት ነበር››

ግብጽ በተደጋጋሚ እንደምትለው የህዳሴው ግድብ ግንባታ አሁን የተጋረጠባትን ከፍተኛ የውሀ እጥረት ይበልጥ ያባብሰዋል የሚል ስጋት አላት፡፡

የአባይ ወንዝ መነሻ የሆነችው ኢትዮጵያ በአንጻሩ የግድቡ ግንባታ የወንዙን ተፈጥሯዊ ፍሰት የማያዛባ፣ የውሀውን ፍሰት መጠን የሚያመጣጥንና የቀጠናውን ሀገራት የሀይል አቅርቦት ችግር የሚፈታ መሆኑን ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

ሌላኛዋ የሶስትዮሽ ድርድሩ ተሳታፊ ሀገር የሆነችው ሱዳን በበኩሏ ግድቡ በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የሚያደረሰው ጉልህ ጉዳት የለም በሚለው ሀሳብ የተስማማች ትመስላላች እንደውም ግንባታው ሲጠናቀቅ ከኢትዮጲያ ክፍተኛ የሀይል አቅርቦት የመግዛት እድሉ እንደሚኖር በማማን የተለሳለሰ አቋም ይዛ ቆይታለች፡፡

በርካታ ግብጻውያን ፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ አልሲሲ ከአራት አመታት በፊት ከኢትዮጲያና ግብጽ ጋራ የፈረሙትን ስምምነት ካባድ ስህተት ነው በማለት ሲወቅሷቸው ቆይተዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹ ስምምነቱ የኢትዮጲያን በግድቡ ዙሪያ የመደራደር አቅም ያጠናከረና ግብጽን ደግሞ ተጎጂ ያደረገ ነው ባይ ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንት አልሲሲ ግን በእዚህ አይስማማሙም እንደርሳቸው አባባል ክፍተቱን የፈጠረው የካርቱሙ ስምምነት ሣይሆን በሀገሪቱ የቀድሞ መሪ ሆስኒ ሙባረክ ላይ ተነስቶ የነበረው ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ በካይሮ በተካሄደው ወታደራዊ ጉባኤ ወቅትም ይህንኑ አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡ ‹‹ ከ ዘጠኝ አመታት በፊት የተነሳው ከፍተኛ ተቃውሞ እንደፈጠረው ችግር ባይሆን ኖሮ በግድቡ ዙሪያ የምናደርገው ድርድር በጥነካሬ የምንወጣውና ቀላል በሆነልን ነበር ሀገር በእንደዚህ መልኩ በምትጋለጥበት ወቅት ይህንን የመሰሉ ክፍተቶች መፈጠራቸው አይቀርም››

እርሳቸው ይህንን በሉ እንጂ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ፕሬዝዳንት አልሲሲ አጋጣሚውን በእርሳቸው ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተቀጣጠለ የመጣውን የህዝብ ተቃውሞ ለመቀልበስ እየተጠቀሙበት ነው የሚል አስተያየት አላቸው፡፡

ምንጭ፡ ሬውተርስ

_____________________________
ኢዜጋን በሶሺያል ሚድያ ይከታተሉ

ለኢትዮጵያ ዜና፣ ለመዝናኛ ቪድዮዎች፣  የሚከራዩና የሚሸጡ ቤቶች፣ ለክላሲፋይድስ ኢዜጋ ፌስ ቡክ ገፅ ይከታተሉን

ለአዳዲስ ዜናዎች እና ሌሎች አስቸኳይ መረጃዎች በ ኢዜጋ ትዊተር ይከታተሉን

ለ አዳዲስ ስራዎች እና የኢትዮጵያ ዜናዎች የ ኢዜጋ ሊንክደን ገፅ ይከታተሉን


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :