የ“ሰንደቅ ዓላማ”ው ተወዛጋቢዎች

ሪያድ አብዱል ወኪል (የህግ ባለሙያ)

October 12, 2020 (Ezega.com)

Ethiopian-Flag“ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ ጥቅምት ወር
የመጀመሪያ ሰኞ በአገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡”
(የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ -ማሻሻያ)

መንደርደሪያ….

ባንዲራ (Bandiera) የሚለውን ቃል ባለማስተዋል ብንጠቀምበትም ቃሉን ጣሊያኖች ሰንደቅ ዓላማን ለመግለፅ የሚጠቀሙበት በመሆኑ ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ በያዙበት ወቅት ያስተዋወቁት በመሆኑ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የምንግባባው “ሰንደቅ ዓላማ” በሚለው ቃል ይሆናል፡፡ የሰንደቅ ዓላማው ጫፍ (ልሣን) የጦር ምልክት እንዲሆን የሚጠበቅበት፣ መጠሪያው “ሰንደቅ” እና “ዓላማ” ከሚሉት የሁለት ቃላት ጥምረት የተመሰረተ ሲሆን ሰንደቅ ማለት “ምሰሶ ወይም ቋሚ ዘንግ” “ዓላማ” ማለት ደግሞ ምልክት ወይም መለዮ እንደማለት ነው ይሉናል ፈታሄ ቃላቶቻችን፡፡

እንግዲህ የሁለቱ ቃላት ጥምረት ነው  “ሰንደቅ ዓላማ” የሚለውን ቃል በአንድ ሐረግ አስሮ “በአብዛኛው የተወሰኑና የተለያዩ ቀለማት ካሏቸው ጨርቆች የሚዘጋጅ የአንድ አገር የነፃነት ምልክትና መለያ፡፡” የአንድ ሀገርና ህዝብ የሉዓላዊነቱ ምልክት ወይም ትዕምርት ተደርጎ የሚወሰደው በማለትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል ከመጠነኛ ማሻሻያዎችጋ የታተመው “የአማርኛ መዝገበ ቃላት” ከህዝቦች ማንነትን ማሳያ፣ ከታሪካቸውና ሉዓላዊነታቸው መገለጫጋ በማቆራኘት ዘርዘርና ጠለቅ ያለ ትርጉም ይሰጠዋል፡፡

በእርግጥ ከዘንጉም ሆነ ከባለህብረ-ቀለማቱ “ጨርቅ” በስተጀርባ ያለው መልዕክት ሰፊ ነው፡፡ ሀገራትና ህዝቦች ለሰንደቃቸው ያላቸውን ፍቅርም በተለያየ መልኩ የሚገልፁ ሲሆን በዚሁ ዙሪያ በርካታ ታሪኮች ተፅፈዋል፣ ፊልሞችም ተሰርተው ተመልክተናል፡፡ በሰላሙም ሆነ በጦርነቱ ወቅት ኢትዮጵያውያን ለሰንደቅ ዓላማችን ጥልቅ ፍቅርና ልባዊ ክብር ያለን ህዝቦች ነን፡፡ ኢትዮጵያችን እንደቀዳሚና ገናና ስልጣኔዋ ሁሉ የረጅም ዘመን የሰንደቅ ዓላማ ታሪክ ያላት ሀገር ስትሆን እስከ-1890-ዎቹ ድረስም አንድ ወጥ የሆነ ሰንደቅ አላማ አልነበራትም፡፡ የታሪክ ገፆች ሲፈተሸ በሀገረ ኢትዮጵያ ከአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ውጪ ያሉ ቀለማት ተውለብልበው እንደሚያውቁ ይነግሩናል፡፡

ከበደ ሚካኤል “ታሪክና ምሳሌ አንደኛ መጽሃፍ” መግቢያ ላይ “ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ምልክት፣ የአንድ ህዝብ ማተብ፣ የኅብረት ማሰሪያ ጥብቅ ሐረግ ነው….. ሰንደቅ ዓላማ ትዕምርተ ሃይል ትዕምርተ መዊዕ ነው፡፡ ሰንደቅ ዓላማችን አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ፣ ሦስት ቀለማት ናቸው፡፡ ምሳሌያቸውም አረንጓዴው ተስፋ፣ ልምላሜና ሀብት፣ ብጫው ሃይማኖት አበባና ፍሬ፣ ቀዩ ፍቅር መስዋዕትነትና ጀግንነት ነው፡፡” ይላሉ፡፡ እነዚህኑ ቀለማት ከሃይማኖት አንtsaር የሚመለከቱ ግለሰቦች ደግሞ የኖህን ታሪክና “ቀስተ ደመና”ን የኢትዮጵያ የቃል-ኪዳን ምድርነት መነሻ በማድረግ አረንጓዴው የአብ፣ ቢጫው የመንፈስ ቅዱስ ቀዩ ደግሞ የወልድ ምልክቶች ናቸው ሲሉም አድምጫለሁ፡፡ እዚሁ ላይም የመፅሐፍ ቅዱስ አናቅፅን በመጥቀስ አስረጅ ያቀርቡበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፈጣሪ ስለመሰጠቱና የተለየ ቅድስና በመስጠት፤ የተስፋው ቃል ህዝቦች ስለመሆናችንና “ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች” የሚለውን በመያዝ ከጥሪዋጋ የሚሄድ ዓርማ (የተዘረጉ እጆች) እንዲኖር ያሳስባሉ፡፡

በእርግጥ የኢትዮጵያን ባለሶስት ቀለም ሰንደቅ ዓላማ ሰባት ያህል ቀለሞች ካሉት ቀስተ ደመና (Bow of the cloud) ጋር የሚያመሳስሉ ሰዎች የመኖራቸውን ያህል ዛሬም ድረስ ራስ-ተፈራውያን በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማነት የሚያውቁትና “የራስ-ተፈራውያን ሰንደቅ” እየተባለ የሚታወቀው የይሁዳ አንበሳን ከመስቀሉጋ ዘውድ የጫነውን ስለመሆኑ ማስታወስ ይኖርብኛል፡፡ አንድ ወሳኙ ነገር አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ ዓላማ ያለ ብሔራዊ ዓርማው ሃይማኖታዊ ትርጉም (Sentiment) ይሰጠናል የሚሉ ወገኖቻችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበሩና ለሃይማኖታዊ ክብረ-በዓላቱ ሲባል ህጉ በልዩነት (Exceptionally) እንዲያስቀምጥ ተጤቆ አሁን ቤተ-ክርስቲያኒቷ አርማዋን ማስቀመጧ ትክክል መብትም ነው፡፡

የኢትዮጵያ “ሰንደቅ ዓላማ” ፖለቲካ ዳራ

ሀገራችን ኢትዮጵያ በየወቅቱ በተለያዩ ስያሜዎች የምትጠራና የምትታወቅ ብትሆንም በዓለም ላይ ቀዳሚ ስልጣኔ ከነበራቸውና ገናና ከነበሩ መንግስታት ጎራ የምትደመር ናት፡፡ የሩቁን አፋዊና ትውፊታዊ ትርክት ለጊዜው አቆይተነው የቅርብ ጊዜውን ስንመለከት ዘመናዊ መንግስታዊ ስርዓት ያላትን ኢትዮጵያ የመፍጠሩ ቴዎድሮሳዊ ህልም በዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ዕውን ሆኖ ይታየናል፡፡ ይህቺ ኢትዮጵያ በዳግማዊ ምኒሊክ አሁናዊውን ቅርts እንድትይዝ ሲደረግም ከዲፕሎማሲው ጀምሮ እስከ የማስገበሩ ጦርነት ድረስ ያሉ መንገዶች ሁሉ ተተግብረዋል፡፡ አንዳንድ ምሁራን ይህንን የማስገበርና የማዋሃድ (Unification) ጦርነት “ወረራ” የሚሉበት ምክንያትም የማማከሉና ዘመናዊ ስርዓተ መንግስትን የመፍጠሩ ጥንስስ እንዲሰምር የየራሳቸው አስተዳደራዊና መሰል ስርዓቶች ውስጥ የነበሩ ህዝቦችን ያካለሉ በመሆናቸው ሲሆን በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያና በኦሮሚያ ችግር መፍጠሩ አይዘነጋም፡፡

በታሪክ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ ብቻ ሆኖ ያውቃል፣ ኢትዮጵያ ህገ-ኦሪትን ስትቀበል ቢጫ ተጨምሮበት ሰንደቁ አረንጓዴና ቢጫ ሆኗል፡፡ የክርስትና ሃይማኖትን እስክትቀበልና ቀዩ እስኪጨመር ድረስም ይኸው ሰንደቅ ዓላማ ፀንቶ ለረዥም ጊዜ ቆይቷል፡፡ የተገላቢጦሽ ሆኖና ሶስቱ ቀለማት ቦታ ተቀያይረውም ያውቃሉ፡፡ አሁን ያለበትን የቀለማት አደራደር ያገኘው በ-19-ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መባቻ ሲሆን ይህ ጊዜም የአውሮጳውያኑ ተስፋፊዎች ቅኝ ግዛትን ያበረቱበት ወቅት ስለነበር ሰንደቅ ዓላማችን የነፃነትና የኩራት ምልክት በመሆን የአገረ ቦሊቪያ ጉዳ እንዳለ ሆኖ ለብዙ የአፍሪካ ሃገራት (As a Pan-African Colours) መነሻ ሆኗል፡፡

እንደሌሎች አገር ወካይ ትዕምርቶች ሁሉ “ኢትዮጵያ” ብለን እየገለፅናት ባለችው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነታችን ላይም የጋራ መግባባት ባይኖረንም አሁን ያለችው ኢትዮጵያ በሁለት ወገን  ተወጥራለች፡፡ በመካከል ሽብልቅ ሆኖ “በአሰባሳቢ ማንነት” የያዘን ሰንደቅም አለ፡፡ የግራና ቀኙ ሆይሆይታዎች (Mobs) ቢበረክቱና ይልቁንም የቀኝ ኃይሎች ልዩነትን ባይታገሱም የኢትዮጵያ ህግ የሚያውቀውና በዓለም-አቀፍ መድረኮች የምንወከልበት ነው፡፡ ብዝኃነታችንን አጥንቶ እርግጠኛውን ቁጥር የነገረን ባይኖርም ከሰማንያ እንደምንልቅ እንዲሁም በፌዴሬሽን ም/ቤት ተወካይ ያላቸው ከስልሳ ስለመብለጣቸው ሰምተናል፡፡

ኢትዮጵያውያን የአንዲት እናት ሀገር ዜጎችና ህዝቦች ብንሆንም አንድነት ማለት “አንድ አይነትነት” ማለት አይደለምና ከዚያ በመለስ የተለያዩ ማንነቶች ያሉን ህዝቦችም ነን፡፡ ይህ አይነተ ብዙነት ወደ ውህደት ሲመጣ ያምራልና ነው በብዝኃነታችን ውስጥ የሚገለፀውን ልዩነታችንን እንደ የአንድነታችን ስጋት ሳይሆን እንደ ተፈጥሯዊ ውበታችን የምንቀበለው፡፡ የሃይማኖት፣ የቋንቋ የብሔር፣ የማህበራዊ መስተጋብርና የባህልን ጨምሮ በርካታ ብዝኃነቶች አሉን፡፡ የብዝኃነት ልዩነት የለንም ብለን በደፈናው ማለባበሱና የሌለንን ወጥነት መናፈቁ ይጠቅመናል ብዬም አላምንም፡፡ እነዚህን ልዩነቶቻችንን ከወታደራዊው አስተዳደር ውጪ ያሉት የከዚህ በፊቶቹ ሥርዓታትም ሆኑ የኢህአዴግ አመራር እንዳደረገው መናከሻችን ሳይሆን እንዴት ውበትና መገለጫዎቻችን እናድርጋቸው የሚለው ላይ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

በዚህ ረገድ የኢህአዴግ ሰዎች ብዝኃነትን ዕውቅና የሰጡበት መንገድ የዘመናትን ጥያቄ የመለሰ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ኢህአዴጋውያን ይህንን እውነታ ያስረዱበት መንገድና ለአደገኛው የከፋፍሎ መግዛት ፖለቲካዊ ግብ ማዋላቸው ትክክል ስላልነበር የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ አዳክመውታል በሚለውም እስማማለሁ፡፡ ኢትዮጵያውያን በቃልም በተግባርም ከምንለያይባቸው ጉዳዮች አንዱና የችግራችን ሁሉ መጠቅለያ ነጥብ “ኢትዮጵያዊነት” ላ ያለን መረዳትና የዚሁ መረዳታችን “መገለጫ” የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን ቢሆንም ከሆይሆይታና የኔ ብቻ ይደመጥልኝ ከሚለው አስተሳሰብ ወጥተን የሰለጠነ ንግግር ማድረግም አልቻልንም፡፡

ኢትዮጵያ የምንላት “ኢትዮጵያ” የትኛዋ ኢትዮጵያ ናት?! ገጣሚው ከዓመታት በፊት እንዳጣየቀው “ኢትዮጵያዊ” የምንለው ኢትዮጵያዊስ የትኛው ኢትዮጵያዊ ነው?! ይህቺ ኢትዮጵያስ መገለፅ የሚኖርባት በየትኛው ሰንደቅ ዓላማ ነው?! የሚሉትን ጥያቄዎች መመለስ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ስንታገለው የኖርነው መንግሥታዊ አንባ-ገነንነት ከመዋቅሩ ወጥቶ ህብረተሰባችን ላይ እየታየና አንዱ ሊያየው የማይፈልገውን ሰንደቅ ሌላው እንዳይዘው እየተጫጫንን ነው፡፡ ሰኔ 16 ቀን 2010 “ዴሞክራሲን እናወድስ” በሚል ፍካሬ በአዲስ አበባ አብዮት (መስቀል) አደባባይ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ተጠብቆ የነበረ አንድ ክስተት ዕውን ሆኗል፡፡ ይኸውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተለያዩ ሰንደቅ ዓላማዎችን ይዘው በአንድ ቦታ ላይ የታዩ ሲሆን ክስተቱ ግን መዝለቅ አልቻለምና ከወራት በኋላ የፖለቲካ ማህበራትን ወደአገር መግባት ተከትሎ ደም ላፋሰሱ ግጭቶች ምክንያት ሆኗል፡፡

ከዚህ ታሪካዊ የዴሞክራሲ ድጋፍ ሰልፍ ላይም ቢሆን የዴሞክራሲ ትርጉሙ ያልዘለቃቸው አንዱ የሌላውን ሰንደቅ ዓላማና አርማ ለማስጣል ግብግብ እስከመፍጠር ደርሰውም ነበር፡፡ የህገ-መንግስታችንን መግቢያ አራተኛውን ፓራግራፍ ያነበበ ማኛውም ሰው “መጪው የጋራ ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል…” የሚለውን የታሪክና የፖለቲካ እውነታ ያስታረቀና የዛሬ መሰረታችንን በመጣል የነገ ብሩህ መድረሻችንን የተለመውን አገላለts አይስተውም፡፡ በታሪክ አሁን “ንፁሁ/ልሙጡ” እየተባለ የሚገለፀው የቀድሞ ሰንደቃችን ከውጪ ለነፃነት ምልክት እንነበረው ሁሉ ከውስጥ የጭቆናና ከፊሉን ኢትዮጵያዊ የማግለል ምልክት እንደነበርም መዘንጋት የለበትም፡፡ ለአብነትም የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ እንደሙስሊም “ባለመስቀሉ የይሁዳ አንበሳ” ያረፈበትም ሆነ ብሔራዊው ዓርማ የሌለበት ሰንደቅ ዓላማ ያለመሸማቀቅ እንድዘምርላቸው አያደርጉኝም፡፡

መሰረታዊ ቀለማቱን በተመለከተ አባታችን ሱልጣን አሊ ሚራህ ሐንፈሬ በአንድ ወቅት እንደገለtsuት “እንኳን እኛ ግመሎቻችንም ያውቁታል”ና ማንም የteleyaye ትርጓሜ ቢሰጣቸውም በዚሁ መቀጠሉ አይቀርም:: yihem chrash adis mefxer new enji yalebn meseretawiwochunm anqebem yemilu wegenoch menorachewun ayasresanm:: የሚሻለውም ይhnnu masqexel ነውna ይነስም ይብዛ ወቅታዊ የህዝብ ውክልና የነበራቸው የህገ-መንግስቱ አርቃቂዎች የሀገራችንን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንtseባርቅ ብሔራዊ ዓርማ (ትዕምርት) endinorbet yemifeqd dngagen አkattewaል፡፡

በወቅቱ ሰንደቅ ዓላማችን መሀል ያረፈውን ዓርማ የሰራው ዕውቁ ገጣሚና ሰዓሊ መስፍን ሀብተ ማርያም ነው፡፡ ስለትዕምርቱ ዝርዝር የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2009 ከስድስተኛው አንቀts ጀምሮ ያሉትን ድንጋጌዎች ማየት የሚቻል ቢሆንም ለእኔ ደስ ያለኝን አገላለጽ ከሸገር አፍ.ኤም ጋዜጠኛው ዘከሪያ ሙሐመድ የፌስቡክ ገጽ በመዋስ እንዲህ ላስቀምጠው፡-  “በዓርማው ላይ ለእኔ የሚታየኝ ዓርማው ከአንድ ወጥ ሪባን የተገመደ ኮከብ ነው። ሪባኑ አንዱ በሌላው ላይ እና ስር፣ ሌላውም በአንዱ ላይ እና ስር ያልፋሉ። የትኛውም የበላይ ብቻ አይደለም። የትኛዉምም የበታች ብቻ አይደለም። የተጋመደ ኅልውና ነው ያላቸው። የተሳሰረ። የተሰናሰለ። መስፍኔ ይህን ኮከብ የሚያስገርም የዕኩልነት ተምሳሌት አድርጎ ነው የሳለው። ከዚህ በዕኩልነት የታነፀ ኮከብ ዉስጥ ብርሃን ሲፈነጥቅ ነው የሚያሳየው። ይህ እኔ ተራው ሰው ዓርማውን በጥሞና ከማየት የተረዳሁት ትርጓሜ ነው። የስነ ጥበብ ባለሙያዎች ከዚህም የጠለቀ ትርጉም ይሰጡታል።” ይለናል ዘከሪያ፡፡

ስለ “ሰንደቅ ዓላማችን” ህግጋቱስ ምን ይላሉ?!

ሰንደቅ ዓላማ ከነtsaነት ምልክትነት የዘለለ “መንፈሳዊ” ይዘት የለውም፡፡ bebzha haymanotoch ager wusx ሰንደቅ ዓላማው kebaleመስቀል አንበሳጋ ዘመናትn ሲቆይ ያልtekefa wegen yilquንm “ቀስተ ዳመናው ላይ አንበሳው ከሌለ፣ የኢትዮጵያ ባንዲራ ትርጉሙ የታለ!” ብሎ bemezfen የህዝበ-ኢትዮጵያ ግማሽ quxr የyazeውን ህዝበ-ሙስሊም ያገለለ ሰንደቅ ዓላማ meናፈቅ ayxeqመን፡፡ “የአንባሻ ምልክት” bibalm ስንበላው ያደግነው የትግራይ አንባሻ ለትዕምርትነት ከጠቀመንና በአንድነት ካጋመደን ችግሩ ምንድን ነው?! አሁን አሁን ደግሞ የሰይጣናውያን እምነት ምልክት ነው የሚለውም በዝቷል ነገ ከነገ ወዲያ ምን እንደሚባል ባyitaweቅም፡፡ ህገ-መንግስtachn በሶስtegnaw አንቀts “የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ” በሚለው ርዕስ ስር ተከታዩን ደንግጎ እናገኛለን፡-

1- የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ፣ ከታች ቀይ ሆኖ በመሐሉ ብሔራዊ አርማ ይኖረዋል፡፡ ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ፡፡

2- ከሰንደቅ ዓላማው ላይ የሚቀመጠው ብሔራዊ አርማ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንtsባርቅ ይሆናል፡፡

3- የፌዴራሉ አባሎች የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ዝርዝሩን በየራሳቸው ምክር ቤት ይወስናሉ፡፡

ያለንበት የብዝኃነት እውነታna የሥርዓተ (ቅርtse) መንግስቱ ለስሁት ዓላማ የዋለ ቢሆንም ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያችን ችግር ፍቱን መድሃኒት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ስርዓት ውስጥ ደግሞ የፌዴራል መንግስቱ አባላት የሆኑ ክልሎች (ክፍላተ-ሀገራት) በየምክር ቤቶቻቸው ውሳኔ ከፌዴራላዊው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ጎን ለጎን የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ higu አስገዳጅ ስላይደለ ላይኖራቸውም ይችላል፡፡ ለምን ኖራችሁ ለምንስ የላችሁም ማለቱም ተገቢ አይmeslegnም፡፡ ለእኔ የሚታየኝ ችግር በህገ-መንግስቱ የፌዴራሉ አባሎች ተብለው የተገለጹትና addis yemifexeru ክልሎች ድንጋጌwun kaleeማጤን የፌዴራሉ አርማ ዓርማዬ ይሆናል አለማለtachewuም yimeslegnalል፡፡

ህግ በሌላ ህግ እስካልተሻረ ድረስ የtseና ነውና መከበር አለበት፡፡ ህgu ለምድራዊ ጉዳዮቻችን የህጎች ሁሉ የበላይ የሚሆነው ህገ-መንግስት ሲሆን ደግሞ ይበልጥ እንድናከብረውና እንድናስከብረው እንገደዳለን፡፡ የህገ-መንግስtu አንቀts-9 ህጉን የማክበርና የማስከበርን ኃላፊነትን ለሁላችንም ቢሰጥም በዋነኝነት የህግ አስከባሪና የፍትህ አካላት ሊያከብሩትና ሊያስከብሩት ቃል የገቡለት ነውና እርሱን ተከትለው የወጡ ህግጋትን ሁሉ አክብሮ የማስከበር ግዴታ አለባቸው፡፡ ህግና የህግ የበላይነት የህዝብ ሰላምና የሀገር አንድነት መጠበቂያ (ላልቶም ጠብቆም ቢነበብ!) ዋስትና ናቸው፡፡ በደፈናው ኢህአዴግ የነካውን ሁሉ ከመቃወም ይልቅ የትዕምርቱን ጠሊቅ ትርጉም በማስተንተን አማካዩን ለመፍጠር ለተኬደበት ርቀት ዕውቅና መስጠትም ይገባል፡፡

በተለያዩ ወቅቶች በስታዲየሞችና አደባባዮች፣ በኤምባሲዎችና ቆንስላዎች ቅጥር በመግባትና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በማውረድ፣ ክብሩን በማዋረድም የድሮውን እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ዓላማዎች ለመስቀል ስለመሞከራቸው በተደጋጋሚ ሰምተን ተመልክተንማል፡፡ አሁናዊው አዲስ ነገር የህጎቹ ተፈፃሚነት በህግ ሳይሻር በየአደባባዩ መዛበቻ መሆናቸው ነው፡፡ በአንድ ወቅት ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ መንግስታቸው የህግ የበላይነት ላይ በአግባቡ አለመስራቱን ሲገልፁ “ራሱን ለህግ የበላይነት ያስገዛ መንግስት ብቻ ነው ዜጎቹ ለህግ የበላይነት እንዲገዙ ለመጠየቅ ሞራላዊ መብት የሚኖረው!” ብለው ነበር፡፡ አውራ ዶሮ ራሱ ሳይነቃ ሌላውን እንደማያነቃው ሁሉ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ የመንግሥቱ የህግ አስከባሪና የፍትህ አካላት በቅድሚያ ለህግ የበላይነት ሳይነቁ ዝጎችን ሊያነቁ አይችሉም፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስትን መነሻ ድንጋጌዎች ተከትሎ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የሰንደቅ ዓላማና አርማ አዋጅም ሆነ ሌሎቹ ተያያዥ ህግጋት (Flag and Emblem Laws) እምብዛም ለህዝብ ለህዝብ አልተዋወቁምና ግንዛቤው አናሳ ነው፡፡ የአዋጅ ቁጥር 654/2009 ማሻሻያ አንቀፅ ስለ “ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን” ክብረ በዓል ሲያትት “በየአመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሰኞ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡” ይላልና ዘንድሮ ደብዘዝ ባለ መልኩ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታስ ውሏል ማለት እንችላለን፡፡

የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2009 ሰንደቅ ዓላማውንና ብሔራዊ አርማውን በተመለከተ የተከለከሉና የሚያስቀጡ ወይም ቅጣት የሚያስከትሉ ተግባራት ናቸው ተብለው ከተጠቀሱት ውስጥ ሰንደቅ ዓላማውን ለብቻው ማለትም ብሔራዊ ዓርማውን ሳያካትቱ መጠቀም፣ የማዋረድና መሰል ድርጊቶችን መፈtፀም በገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣና እንደየሁኔታውም እስከ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት ሊያስቀጣ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ የህጉን መቀጮ አቆይተነው ኢትዮጵያ ከታሪኳ በጎውን እንጂ ክፉውን አትወርስምና በሁለቱም ጫፍ ሆናችሁ የምትጓተቱ ወገኖቻችን ወደመታረቂያው መሀል ኑልንና ለሁላችንም የምትበቃንን፣ ሁላችንንም ያለምንም ቅሬታ በእኩል የምታቅፈውን፣ ሁላችንንም የምትገልፀውን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እናዋልዳት እላለሁ፡፡

የብሄር-ብሔረሰብ፣ የቋንቋና ሃይማኖታዊ ማንነትንና ፖለቲካውን በህግ ዕውቅና በመንፈግም ሆነ “ኑ እኛን ምሰሉ!” በማለት የምትፈጠር ኢትዮጵያ አትዘልቅም ብዬም አምናለሁና የጋራ ቤታችንን ለማፅናት ስንተጋ የሃሳብ ገበያው መርህ ሃሳቦች ሁሉ ይገለፁ፣ ለምርጫም ይቅረቡና የተሻለው ሃሳብ ያሸንፍ (The best ideas will win.) እስከሆነ ድረስ የከዚህ በፊቶቹ ዳሰሳዎችና ውሳኔ ህዝቦች እንደተጠበቁ ሆነው ህዝባዊ ውይይቶችና ውሳኔዎችን በማድረግ ውዝግቡን ማስቀረት እንደምንችል እተስፋለሁ፡፡

-ሠላም ለእናንተ ይሁን!-

_____________________________
ኢዜጋን በሶሺያል ሚድያ ይከታተሉ

ለኢትዮጵያ ዜና፣ ለመዝናኛ ቪድዮዎች፣  የሚከራዩና የሚሸጡ ቤቶች፣ ለክላሲፋይድስ ኢዜጋ ፌስ ቡክ ገፅ ይከታተሉን

ለአዳዲስ ዜናዎች እና ሌሎች አስቸኳይ መረጃዎች በ ኢዜጋ ትዊተር ይከታተሉን

ለ አዳዲስ ስራዎች እና የኢትዮጵያ ዜናዎች የ ኢዜጋ ሊንክደን ገፅ ይከታተሉን


  እትም



Contact News Editor

Name :
Email :
Phone :
Message :
ezega
ከላይ የሚታየው ጽሁፍ ያስገቡ :